ጥቁር ዘመን ( ሄኖክ የሺጥላ )
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ጥቁር ዘመን ( ሄኖክ የሺጥላ )
ባንድ ወቅት ፣ ታሪክ እና የእምነት መጥሃፍቶች እንደሚነግሩን ከሆነ ፣ ጥቁርነት የውበት እና የትልቅነት መለኪያ ነበር ። “ጥቁር ብሆንም ቆንጆ ነኝ” የሚል ቃል መጽሐፈ ምሳሌ ላይ ተከትቦ ማንበቤን አስታውሳለሁ ። አንዳንዶች ጥቁር ሲል < ቤ/ክርስቲያኗን> ነው ይላሉ ። ለኔ የገባኝ ግን እንደተጻፈው ነው ። ምንም ብዙ ሳልመሳጠር ። በጥንታዊ ግብጥ ( ምስርም ) እንዲሁ ጥቁርነት ዋጋ ያለው ቀለም እንደነበር ጃን ኒቨርድን White on Black: Images of Africa and Blacks in Western PopularCulture በሚለው መጥሐፉ ላይ the color of fertility dark as the silt of the Nile ( የለምነት ቀለም ፣ ጥቁር የናይል ልም-አፈር ) በማለት ይገልጸዋል ። በጥንታውያን ሮማውያን ታሪክ ፣ ጥቁር የውበት መለኪያ እንደሆነ የሚያሳዩ ብዙ መረጃዎች ይገኛሉ ። ለምሳሌ በአማልክት ታሪኮቻቸው ካሲዮፒያ ልጅ አንድሮሜዳ ኢትዮጵያዊ ስትሆን ፣ እናቷ ካሲዮፒያ ፣ የኔን የልጄን አንድሮሜዳን የመሰለ ውበት፣ የመሰለ ቁንጅና በግሪክ የለም ፣ ጁኖም ቢሆን-ራሱ በማለቷ ፣ ለባህር ጭራቅ ታስራ እንድትሰጥ ተወስኖ እናት እና አባቷ ( ካሲዮፒያ ና ሴፊየስ ) የገዛ ልጃቸውን ባህር ዳር ላይ እንዲያስሩ ይፈረድባቸውል ። ግን አንድሮሜዳ እውነትም ቆንጆ ስለነበረች ፣ ፐርስየስ የተባለው ሌላው የግሪክ አማልክት በሰማይ ላይ በአክናፍ ሲጋልብ ፣ በውበቷ ይማረክና ከታሰረችበት ይፈታታል ይላል ታሪኩ ። ( Cassiopeia was the beautiful wife of Cepheus, king of Ethiopia, and the mother of Andromeda. She is most famous in connection with the myth of her daughter, Andromeda. The queen made the mistake of bragging she was more lovely than the Nereids, or even than Juno herself. The goddesses were, needless to say, rather insulted, and went to Neptune, god of the sea, to complain. Neptune promptly sent a sea monster (possibly Cetus?) to ravage the coast. The king and queen were ordered to sacrifice their daughter to appease Neptune’s wrath, and would have done so had Perseus not arrived to kill the monster in the nick of time. As a reward, the hero was wedded to the lovely Andromeda.) ይህ ታሪክ ( ተረት በሉት ከፈለጋችሁ ) ፣ ጥንት የሰው ልጆችን ውበት የሚለያየው ቀለም እንዳልነበር አስረጅ ነው ።
እንደውም የታላቂቷን ሮም መውደቅ ተከትሎ ፣ ሰዎችን የከፋፈላቸው ዋነኛው የልዩነት ሰርጥ ቀለም አልነበረም ፣ ሃይማኖት እንጂ! የታሪክ መዛግብት እንደሚያወሱት ከሆነ ፣ የሮማውያንን ውድቀት ተከትሎ የመጣው ( ከጥቂት ምዕተ አመቶች በሗላ —ወዲያው ባይሆንም ) የ ሞሪሾች ወይም ሙርስ መስፋፋት ነው ። መነሻቸው ያሁኗ ሞሮኮ ሲሆን እነዚህ ህዝቦች ፣ ነጭ፣ ጥቁር ፣ ቀይ ዳማ እና ወዘተ ቆዳ ቀለም ቅልቅል የያዙ ሰዎችን ያካተቱ ማህበረሰብ ሲሆኑ ፣ የእስልምና ሃይማኖትን የተቀበሉ ነበሩ ። እነዚህ ሰዎች ፣ ግዛታቸውን እና ወረራቸውን ፣ ከአፍሪካ እስከ ሩቅ ምስራቅ ፣ ከ መካከለኛው ምስራቅ እስከ ፈርንሳይ ደርስ በማስፋፋት ፣ ለ 800 ዓመት ገዝተዋል ። ይህ የአረብ ምሁራኖች ጥንታዊ አውሮፓን ከመርገጣቸው በፊት ያለውን ዘመን ( dark age ) ጥቁር ዘመን ይለዋል ። ሳይንስ ፣ ጥበብ ፣ ፍልስፍና እና እውቀት ሳይነቀሳቀስ ቀጥ ብሎ የቆመበትን ዘመን ይመስለኛል ። ሰዎች ከእንስሳ በከፋ የሰውነት ሕግ ውስጥ የነበሩበት ዘመን ። አዎ ጥቁሩ ዘመን ፣ የእድገት እና ብልጽግና ፍሬ መድረቅ የጀመረበት ፣ ፈላስፎች የተሰደዱበት ፣ አዋቂዋች የተዋረዱበት ፣ የህክምና ሊቆች በካራ የተበለቱበት ዘመን ነበር ። አዎ (the age of migrations, age of barbarism) የስደትና የባህል አልባነት ፣ የሥርዓት አልባነት ዘመን ። ጥቁር ዘመን !
ታዲያ ዛሬ -ስለ ሀገሬ ኢትዮጵያ ሳስብ ፣ እኛ ኢትዮጵያውያኖች እዛ የጨለማ ዘመን ላይ ያለን ይመስለኛል ። በወረራ እና በጉልበት ፣ የኔን ሃሳብ ተጠመቅ የሚል ስርዓት ያለበት ሀገር ሰው መሆኔን ሳስብ ፣ ከብዙ መቶ ዓመት በፊት የወደቀችውን ሮም ተከትሎ በአውሮፓ ተከስቶ የነበረው የ ጨለማ ዘመን ድባብ ዛሬ በኔው ሀገር ፣ በናት ምድሬ ማጀት ይታየኛል ።
ባንድ ወቅት ኢትዮጵያዊነት ጌጥ ነበረ ፣ እንደውም ግሪኮቹ አለምን ሲከፍሉ አንድኛዋ አህጉር ኢትዮጵያ ነበረች ። እነ ኦቭድ እና ሆመር ያንን ነበር የተናገሩት ። እነ ንጉስ ሜምኖን ጢሮስን ለመታደግ ከኢትዮጵያ ነበር የገሰገሱት ። አረ እንደው የዙዛን ከተማ አስገብረው ፣ ሃውልታቸውን አስቀርጸ ነበር ወደ ስፓርታ የከነፉት እና ከነ አኪልስ ጋ በሰይፍ የተፋለሙት ። አዎ ድሮ ታሪክ ነበረን ፣ ስም ነበርን ፣ ሀገር ነበርን ። ዛሬ ይሄ ሁሉ ነገር ተቀምተናል ። ድሮ ጥቁርነት ጌጥነት እንደነበረ እና ዛሬ እንደተዋረደ እና እንደረከሰ ሁሉ ኢትዮጵያዊነትም ያ ዕጣ ደርሶታል ። ግን ትልቅ ነበርን ፣ ትልቅም እንሆናለን የሚለውን ቃል ሳስብ ፣ ተስፋ ሁለም ኃይል ሆኖኝ እንድበረታ እሆናለሁ እንጂ !
የጨለማው ዘመን ያበቃል ።
ቅርብ ነው አይርቅም የኢትዮጵያ ትንሣዔ
ባንድነት ከገባን የፍቅር ሱባዔ !
ነው ያለው ሳልሳዊ ቴዎድሮስ !