ልዩ-ትግሬ ( Tigre-exceptional ) ሄኖክ የሺጥላ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ልዩ-ትግሬ ( Tigre-exceptional ) ሄኖክ የሺጥላ
የ- ነጭ ዘረኞች አውቃለሁ ። ሰዎች ዘረኝነታቸው ከንቀት እና ከጥላቻ ነው የሚመጣው ይላሉ ። እኔ ግን እንዲሁ ሳስበው ምንጩ በትክክል ይህ ነው ማለት ባልችልም ፣ ምክንያቱ ግን ፍርሃት እና ስግግብግብነት የፈጠረው ነው የሚመስለኝ ። አንድ ነጭ አንድን ጥቁር በዘሩ የሚጠላው እነሱ እንደሚሉን ጥቁር ጦጣ ወይም ዝንጀሮ ሥለሚመስል ብቻ አይመስለኝም ። ምክንያቱ ያ ቢሆን ኖሮ ፣ አንድ ነጭ ጀርመናዊ ፣ ሌላ 6 ሚሊዮን ነጭ አይሁዳውያንን ባላጠፋ ነበር ። የዘረኝነቱ ምክንያት ፣ የቀለም መለያየት ቢሆን ኖሮ ፣ ልዩነቶቹ በሙሉ በነጭ እና በጥቁር መሃከል ብቻ ሆኖ በቀረ ነበር ። ይሄ ሲሆን ግን አላየንም ። ጉዳዩ ግን ሌላ ይመስላል ።
በዚህ በአማሪካ ስለተፈጠረው የ “exceptional whiteness ” ( ወይም ልዩ ነጭነት ) ታሪክ ወደ- ሗላ መለስ ብለን ብንቃኘው ፣ የመሬት ከበርቴው መሬቱን ለማልማት የሚያስፈልገው የጉልበት መጠን እየጨመረ መጣ ፥ በወቅቱ የባላባት ወይም ባለ ርስት አገልጋዮች ፥ በሕግ ለተቆረጠ ወይም ለተወሰኑ ጊዜያቶች ብቻ ( for a legally defined time) ነበር የሚያገለግሏቸው ። ስለዚህ ቀናቸውን የጨረሱ አገልጋዮቻቸውን መልቀቅ ምርጫ የማይሰጥ ሁኔታ ሆነ ። በተመሳሳይ ሁኔታ በአማሪካ ይኖር የነበረው ድሃ- ገበሬ (peasant) ፣ በአውሮፓ ይኖር ከነበረው ድሃ ገበሬ አንጻር ፣ በቀላሉ ጸጥ-ለጥ አድርጎ መግዛት የሚቻልም አልሆነም ነበር ። የአማሪካ ድሃ ገበሬዎች፣ ጥቁርም ሆነ ነጩ ባንድነት በተከታታይ አመጽ ያስነሱ ፣ ብሎም ያነሱ ነበር። ይህ ጉዳይ ያሳሰባቸው የቨርጂኒያ የወቅቱ የፖለቲካ ዘዋሪዎች ፣ ለዚህ ችግር መፍትሄ የሚሆን መልስ ሲያስቡ ይህንን ልዩ ነጭነት (exceptional whiteness) የሚለውን ነገር አምጠው ወለዱ ።
ለነጮች ከሌሎች የተሻለ ፥ የተለየ ግን ደሞ የተወሰነ መብቶችን ሰጡ ። ለነጮች መብት መስጠት ብቻ ሳይሆን ፣ ከጥቁሮች ላይ የነበራቸውን መብት ወሰዱ ( ቀሙ !) ። እኤአ በ 1860′ ዎቹ ነጭነት የዘር ቋንቋ ሆኖ ብቅ አለ ። በዛም ሳያበቃ በ 1691 ነጭነት በቨርጂኒያ ሕግ ሆነ ። ይህንን ተከትሎ በአማሪካኖች ጭንቅላት፣ ነጭነት እና ጥቁርነት ፣ ከዚህ በፊት ከነበረው በተለየ መልኩ የ_ ልዩነት መንፈስ ሆኖ ተወለደ ። “ሜትሮ” እንደሚለው ከሆነ ” የ 18ኛው ክፍለ ዘመን ነጮች ፣ ቋሚ ባሮች የማይሆኑትን ያህል ( ጥቂት ቢሆኑም የነጭ ባሪያም ስለነበረ ነው ) ፣ ጥቁሮች ባንጻሩ ነጻነታቸው የማይከበር ብቻ ሳይሆን ስለ ነጻነት የማሰብ መብት እንኳ እንዲኖራቸው የማይፈቀድላቸው ሆኑ ” ።
ለምሳሌ የሁለተኛ ዓለም ጦርነትን ተከትሎ ፣ የጦር ጡረተኖችን የሚመለከቱ ፣ የቤት ብድር እና መሰል ጉዳዮች ላይ ፣ ከፋፋይ የሆኑ የፌድራል መዋቅሮች እና ሕጎች ተቀረጹ ። ይህ ዛሬም ድረስ ላለው በነጭ እና በጥቁሮች መሃከል ስለተፈጠረው የሀብት ልዩነት ምክንያት ሆነ። ልዩነቶቹ ከመግዘፋቸው ብዛት ፣ ወነጀለኛ ነጭ እና ከወንጀል ነጻ የሆነ ጥቁር ለስራ ቅጥር እኩል የሚወዳደሩበት ” የዝምታ ሕግ ” ተፈጠረ ።
ይህ ዘረኝነት የአማሪካንን ምጣኔ ሀብት ክፉኛ ቢጎዳውም ( በአሁኑስ ሰዓት ጥቁሮችን በማስገልል ምክንያት በመጣ ኪሳራ ፣ አማሪካ በግምት ወደ አንድ ትሪሊዮን ዶላር ታጣለች ተብሎ ይገመታል )፣ ዘረኝነቱ ቀጠለ ። ጥቁሮች የመማር እድሉን አግኝተው ፣ የተሻለ እና ስኬታማ ለመሆን በሚያደርጉት ጥረት ላይ ተስፋ ቢስነትን ለመዶል አዲስ አስተሳሰብ ተወለደ ። ይህም ያልተማረው ፣ መሀይሙ ፣ ምናልባትም ” ደንቆረው ነጭ ” ፣ እጅግ በጣም ከተማረው እና ከረቀቀው ነጭ የተሻለ ተደርጎ ይታይ ጀመር ። (the “lowest” white person was elevated over the most accomplished, intelligent, and successful person of color)።
የነጮች ፍጹም የተለዩ መሆን ፣ ወይም ናቸው ብሎ ማስብ እና ማስነገር ፣ በራሳቸው በነጮቹ ውስጥ አዲስ የበላይ ማንነት ስሜትን ፈጠረ ይህ “white exceptionalism ” ከፖለቲከኞቹ ወደ ብዙሀኑ ነጭ በቀላሉ ሰረጸ ” ይህም የትልቅነት ስሜት ፣ ራሱን የሚያነጻጽርበት ትንሽነት ያስፈልገው ስለነበር ፣ ጥቁሮችን ” የበታች ናቸው!” የሚለውን የከፋፍለህ ግዛ ሴራ ያለ አንዳች ማቅማማት ተቀበለ ። በመቀበልም ብቻ አላቆመም ፣ አስፈጻሚም ሆነ ።
ይህንን ሃሳብ ፈላስፋዎቹ ቻርልስ ሚልስ እና የታሪክ ምሁሩ ኤድሞንድ ሞርጋን ሲያብራሩት
” የነጮች ነጻ አውጪ አዋጅ ፣ የነጭነት የዲሞክራሲ ተግባራትንና እና ጽንሰ ሃሳብ፣ ከሚተገብርላቸው ነጮች ጋ አቆራኝቶ የያዘው ( አጣብቆ የያዘው ሙጫ ) ፣ የጸረ -ጥቁር ርዮት እና “አብዮት” ማዘሉ ሳይሆን ፣ ይህ የነጮች ነጻነት እውን የሚሆነው ጥቁሮችን እና ሌላ ነጭ ያልሆኑ ሌሎችን በማስገበር ነው ” የሚል ይዘት ስለነበረው ነው ይላሉ ። ስለዚህ ነጮቹ ይህንን ሃሳብ ያለ ማቅማማት የተቀበሉት ፣ በባዶ ትልቅ ወይም የተለዩ ሰዎች አድርጎ ስላስቀመጣቸው ብቻ ሳይሆን ፣ በሚታይ ደረጃ ፣ ጥቁሮችን ጨቁና እና ባርያ አድርጎ ከመኖር ከሚገኘው ሀብትም በተወሰነ ደረጃ ተቋዳሽም ስላደረጓቸም እንጂ !
እዚህ ጋ መረዳት ያለብን ነገር ፣ ሁሉም ነጮች በእኩል ደረጃ ነጭነታቸው ያመጣውን ሲሳይ አይጠቀሙበትም ። የመደብ ልዩነቱ ፣ በነጮች መሃከል እንዳለ ሆኖ ነው ፣ የ ልዩ የነጭነት ጉዳይ የሚመጣው ። ለነጮቹ ፣ ከመደብ ልዩነቱ ይልቅ ፣ የተሻልኩ ነኝ የሚለው ግንዛቤ እና ግንዛቤው ያመጣው ባዶ ስነ ልቦናዊ ምንዳው ፣ በመደብ ልዩነት ካጡት ሁሉ የተሻለ ስለነበር።
ስለዚህ ልዩ- ነጭነት እና የበላይ ነጭነት፣ በጥንቃቄ በነጭ ሙህራኖች እና የፖለቲካ ቆማሪያን የተፈበረከ የፖለቲካ ዘዴ ነው ማለት እንችላለን ። ይህንን የ ፖለቲካ ዘዴ ድሃው ነጭ ያለ ብዙ ችግር ነበር የተቀበለው ።
ይህ እና ሌላ መሰል የ የፖለቲካ ሴራዎች ቤኔጮችና በሌሎች መሀከል ያለውን ልዩነት ለማስፋት የነጭ ፖለቲከኞች ኣሌ የማይባል ሚና ተጫውተዋል። ለምሳሌ በ 17ኛው ክፍለ ዘመን ( በ 1676 በናትናኤል ቤከን ) የተመራውን የ “Bacon’s Rebellion” እየተባለ የሚጠራው የከሸፈበት መንገድ አንዱ ነው ። ይህ የቨርጂኒያ ሰፋሪዎች ፣ የውቅቱን የፈርጂንያ ሃገረ-ገዥ ( ዊልያም በርክሌይ)’ን እና ከበርቴ ባለ ርስቶን በመቃወም ያካሄዱት ተቃውሞ ነው ። በዚህ ተቃውሞ ፣ በቅጥር ውል ውስጥ የወደቁ (indentured servants) ፣ ጥቁር እና ነጭ “ላብ- አደሮች” በአንድነት በመሆን ያካሄዱት አመጽ ነበር ። የወቅቱ የ ቨርጂንያ ሀገረ ገዢዎች እና ከበርቴ ባለ ርስቶቹ ይህንን ሕዝባዊ አመጽ ለመግታት የተጠቀሙበት የከፋፍለህ ግዛ መንገድ ሲሆን ፣ ለዚህም አላማቸው እንደ መፍትሄ አድርገው ያቀረቡት ሃሳብ ለአገልጋይ ነጭ ላብ አደሮች፣ የስራ ጊዜያቸውን ሲጨርሱ መሬት ፣ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ፣ እና ገንዘብ ሰጧቸው ። ይህ የመሳሪያ ፣ ኩርማን መሬት እና ገንዘብ ድጎማ ያገኘው ድሃ የነጭ ገበሬ ፣ ራሱን እንዲህ አይነት አንዳች ድጎማ ካላገኘው ጥቁር ገበሬ የተሻለ አድርጎ ማየት ጀመረ ፣ በመቀጠልም በችግር እና ችጋር የተጎዳው ጥቁር ገበሬ የሚያነሳውን ማናቸው አይነት ጥያቄ እና ተቃውሞ ፣ ከ ባለጸጋው ነጭ የበለጠ ስለተደረገለት ስጦታ ሲል ሽንጡን ገትሮ ይቃወም ጀመር ። ለዚህም አንዱ ማሳያ የ ኬኬኬ ( KKK ) መፈጠር ነው ። በተነገራቸው ትልቅነት ትልቅ የሆኑት ችግኝ ዘረኛ ነጮች ፣ ከራሳቸው በላይ ማየት ስላቃታቸው ፣ ልዩ ነጭነትን እንደ አንድ ትልቅ እውነት አምኖ ከመቀበል አልፎ ፣ ሰባኪ እና ስተማሪ ሆኑ ። ይህንንም ለማመልከት ይመስላል
ቶም ዋትሰን በጆርጅያ በ 1892 የሚከተለውን ንግግር ያድረገው
“You are made to hate each other because on that hatred is rested the keystone of the arch of financial despotism which enslaves you both. You are deceived and blinded because you do not see how this race antagonism perpetuates a monetary system that beggars you both.
” እርስ በእርሳችሁ እንድትጠላሉ ተደርጋችሗል ፣ ምክንያቱም ያ ጥላቻ ራሱን ያሳረፈው በንዋይ ፍጹም የበላይነት ላይ ነው ፣ ይህ የንዋይ የበላይነት ሁለታችሁንም ባርያ አድርጓችሗል ። ይህ የዘር ቅራኔ፣ በውስጡ በያዘው የንዋይ ሕይወት ሁለታችሁም ለማኞች መሆናችሁን እስኪያዘነጋችሁ ድረስ ተታላችሗል ፣ ታውራችሗል ። ይላል !
ይህንን የአማሪካንን የከፋፍለህ ግዛ ታሪክ ስናጤን ፣ ዛሬ በሀገራችን ኢትዮጵያ እየሆነ ያለው ፣ እጅግ በሚገርም ሁናቴ ፣ የዚህ የቨርጂንያ ከበርቴዎች እና ፖለቲከኞችን ሴራ ቅጅ ይመስላል ። በብሶት ፣ በተንኮል ( ተንኮል ስል የ- ሀውዜንን ድብቅ የህወሓት ሴራ አስቡልኝ ) እና በመሰል መንገዶች ፣ ከትግራይ መንደሮች ታጋዮችን የመለመለው ሽፍታው ቡድን ፣ በደደቢት በርሃ ውስጥ ቁጭ ብሎ ሲያልም የነበረውን እና ፣ <የሸዋ ነገስታት ያለ ተቀናቃኝ የራሳቸው አደረጉት > ብሎ ሲሰብክ እና ሲያነሳሳባት የነበረው ሃሳቡን ከተማ ሲገባ እውን ለማድረግ ፣ አንድ ብቸኛ አማራጩ ፣ የትግራይን ሕዝብ የተለየ ፣ ጀግና እና ደፋር ፣ በቀድሞ ስርዓት የተበደለ እና በደሉን መመለስ የሚችል አድርጎ መቅረጽ ነበር ። ይህ ያለ ከልካይ በገፍ የተነገረውን የብቻ ጀግንነት አቧራ በጠገበ ጆሮው ያደመጠው የትግራይ ገበሬ ፣ እንደ ልዩ-ነጮቹ ፣ እሱም ያሉትን ተቀብሎ ልዩ-ትግሬ ሆነ ( ወይም ነኝ አለ )። እምነቱ መሰረት ይይዝ ዘንድ ፣ እየመዘዙ እያወጡ የሀብትና የንብረት ባለቤት አደረጉት ። ትግራይ በጦርነት የተጎዳች < ክልል > ስለሆነች በሚል ሽፋን የተለየ የሚመስል የትምህርት እንድል እንያገኝ አደረጉት ፣ ጎጃም ላይ ፣ ጎንደር ላይ ፣ አንቦ ላይ ፣ ድሬዳዋ ላይ ፣ አዲስ አበባ ላይ ፣ ጋንቤላ ላይ ፣ ሱማሌ ላይ ፣ ያለ አንዳች ገደብ መስራት እንዲችል ከመፍቀድም አልፈው ፣ በባዶ መሬት ፣ ካርታ እያሳየ ከባንክ ብድር እንዲበደር ይህ “ልዩ -ትግሬ” ይመቻችለት ጀመር ። የተደረገለት ፣ ስለተደረገለት እና ስላየው ለውጥ ሲል ፣ ወያኔን መደገፍ ጀመረ ። በትግራይ ወረዳዎች ፣ ዛሬም አቧራ በጠገበ ጆሮው ፣ እልህ ባልቀመሰ አንጀቱ ወያኔን የሚደግፈው የትግራይ ገበሬስ ምን አይቶ ነው የሚደግፋቸው ለሚለው ጥያቄ መልሱ ” ልዩ-ትግሬነቱ ” ( being an exceptional Tigere ) በራሱ የመንፈስ ምግብ ስለሆነው ፣ ሲሰማ የነበረው ትልቅነቱ፣ ደርግን በማሸነፍ የተረጋገጠ ስለሆነ ፣ ባይበላም ፣ ባይመቸውም ፣ መሬቱ ጦሙን ቢያድርም ፣ ልዩ-ትግሬ መሆኑ በራሱ በቂ ነውና ፣ ህወሓትን ለመደገፍ ሌላ ምክንያት አላስፈለገውም ። መገንዘብ ያለብን ፥ ልክ እንደ ልዩ ነጮቹ የመደብ ልዩነቱ እዚህም በደንብ ይታያል ። ኣድዋ ከኣጋሜ ጋ ኣንድ ኣይደለም ፥ ኣክሱሙ ከሽህሬው እያለ ይቀጥላል። ያም ሆኖ ልዩ ትግሬኔቱ ገዢ ሃሳብ ስለሆነ ፥ ሁሉንም እኩል ያደርጋቸዋል !
ታዲያ ይህ የትግሬ አማራን መጥላት የሚለው ነገርም መሰረቱ ያው እንደ ቨርጂኒያ ፖለቲከኞች ምክንያቱ ያው አንድ አይነት ነው ። ፍርሃት ነው ፣ ስግብግብነት ነው ። ከዚህ ሌላ ፣ ሌላ የተለየ ምክንያት ይኖረዋል ብዬ አላስብም ። ምን ማለቴ ነው ? ሕወሓቶች ታሪክን ወደ- ሗላ ዞር ብለው ስያጤኑትም ሆነ ፣ እነሱ እንሰራዋለን ብለው ስለሚያስቡት ልዩ-ትግሬነት ሲያስቡ ፣ እንደ አንድ ባላንጣ ሆኖ ከመንገዳቸው ሊያሰናክላቸው የሚችለው ነገር አማራ ሆኖ ነው ያገኙት ። ዘረኞች ስለነበሩና እና ስለሆኑ ፣ ነገርን ከዘውግ ውጭ ማየት የምያስል አእምሮ የላቸውም ። ስለዚህ ይህንን አላማቸውን ለማሳካት ፣ የቨርጂኒያ ፖለቲከኞች ፣ ለላብ አደሩ- ልዩ-ነጭ ኩርማን መሬት እና መሳሪያ እና ገንዘብ እንደሰጡት ሁሉ ፣ መጀመሪያ በሌሎች ብሔሮች ውስጥ “በብሄር ብሔረሰቦች መብት እና እኩልነት ስም ” በቀድሞ ስርዓት ወይም አማራ ላይ ያነጣጠረ ፣ አማራ አጥቂ እና ሌሎች ተጠቂ የሚል መንፈስ ፈጠሩ ፣ የአማራ መንፈስ ነው ብለው ከሚያስቡት ነገር ጋ የሚያጋጭ ነገርም አብረው ዘየዱ ። አንቀጽ 39 የዚህ ዘዴያቸው አንዱ መገለጫ ነው ። ይህ በሌሎች ብሔረሰቦች ውስጥ ፣ ከሀገር በታች አንሶ ፣ በመንደር እና በጎሳ ማሰብን ብቻ ሳይሆን ፣ የኔ መንደር-ብቻ ፣ የኔ ሰፈር-ብቻ የሚል መንፈስ እንዲፈጠር ምክንያት ሆነው ። ይህ ስሜት ፣ ለሌሎች ብሔሮች መስራት ባልጀመረበት ጊዜ ፣ አማራ ላይ ብቻ ያነጣጠረ የማፈናቀል እና የመንቀል ሥራ ተጀመረ ። በተበደልኩ ስሜት ፣ እና በኔ ክልል የስሜት ፖለቲካ የፋፋው ትግሬ ያልሆነው ሌላው ዘር አማራ ላይ በትግሬዎች ዘዴ ዘመተ ። ይህም በአማራዎች እና በሌሎች ብሔሮች መሃከል ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ እና ስር የሰደደ ቅራኔ እና ጥላቻን ወለደ ። ልዩ-ትግሬ ግን ፣ የፈለገበት ሄዶ ያርሳል ፣ የፈለገውን ሄዶ ያፍሳል ። ሄዶ ሄዶ ግን ፣ የተንኮላቸው እና የከፋፋይነታቸው አላማ ዝርፊያ ነው ፣ ንጥቂያ ነው ፣ ስግብግብነት ነው ፣ ሌብነት ነው ። ይህ እንዲገባው የማይፈልገው ልዩ ትግሬ ( ወይም ኢትዮጵያዊው ኬኬኬ ) የስርዓቱ የዝርፊያ ማስፈጸሚያ ብቻ ሳይሆን ፣ ጠበቃ ፣ተሟጋች ፣ ሲያስፈልግ ሟች ሆነ ። እኛ ይህንን የትግሬ ዘረኝነት እንለዋለን ። የስነልቦና ተመራማሪዎች ፣ ” የሌባ አይነ ደረቅ !” ይሉታል ። እንግዲህ ባጭሩ የገባንበት ማጥ ይህንን ይመስላል ።