የአሜሪካ ፕረዚደንት ባራክ ኦባማ አለቀሱ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Asfaw Gedamu's photo.

በአሜሪካ የመሳርያ ባለቤትነት በህግ የተከበረ በመሆኑ የመሳርያ ቁጥጥር ማድረግ እንደ ወንጀል ይቆጠራል፡፡ በመሆኑም በየዓመቱ 30 ሺህ የሚያክሉ ዜጎች ይገደላሉ፡፡ከሶስት ዓመት በፊት በኒውታውን፣ ኮነክቲከት ላይ ከ20 በላይ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች በገፍ ሲገደሉ ሕጉን ለማሻሻል ወይም የመሳርያ ቁጥጥር እንዲደረግ የሚያስችል ህግ እንዲፀድቅ ጥረት ያደረጉት ኦባማ የአሜሪካው ኮንግረስ ሽሮባቸዋል፡፡

የኮንግረስ መቀመጫዎች በአብዛኛው በሪፓበሊካኖች የተያዘ ነው፡፡አብዛኞቹ ሪፓብሊካኖች ደሞ የሓብታቸው ምንጭ ከጦር መሳርያ ሽያጭ የተገኘ እንደሆነ ይነገራል፡፡ለዛም ነው የጦር መሳርያ ቁጥጥር እንዳይደረግ አበክረው የሚቃወሙት፡፡ይህ የኮንግረሶች ግትር አቋም አላላውስ ብሎ ስላበሳጫቸው ነው እንግዲህ ፕረዚደንቱ በዋይት ሃውስ ያደረጉት ንግግር በእንባ ያጀቡት፡፡

ይህ ነገር ከሃገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ለማነፃፀር ብንሞክር
1. 18 ሚሊዮን ዜጎጅ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል፡፡

2. በኦሮምያ ክልል በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በመንግስት የፀጥታ ሓይሎች ተገድሏል እየተገደሉም ነው፡፡

3. በጎንደር አከባቢ በተነሳው ግጭትም ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

4. የፍትሕ ስርዓቱ በደላሎች እጅ ስለሆነ ፍትሕ የለም፤ ሙስና ነግሰዋል፡፡ (መንግስት ያመነው ነው)

5. የመብራት፣ የውሃ፣ የመኖርያና የትራንስፖረት እጥረት ህዝቡን አላላውስ ብሎታል…በምሬት እየየ እያለ ይገኛል፡፡

የእነዚህ መክንያቶች ድምር በአመሪካ አልፎ አልፎ ከሚከሰተው የአጥፍቶ መጥፋት፣ የጅምላ ግድያና የአሸባሪዎች ጥቃጥ ቢበልጥ እንጂ አያንስም፡፡ገዢዎቻችን ግን ይቅርል ሊያለቅሱ ይሳደባሉ፤ ነጋ ጠባ ይዝታሉ…ይሸልላሉ፡፡

ልብ ላለውና ህሊናው ላልታወረ መሪ ግን ለቅሶ ይቅርና ራስን እስከማጥፋት ያደርሳል፡፡

The executive actions include (A):

1.Background checks for all gun sellers, overturning current exemptions to some online and gun show sellers

2.States providing information on people disqualified from buying guns due to mental illness or domestic violence

3.Increased workforce for the FBI to process background checks, hiring more than 230 new examiners

4.Congress being asked to invest $500m (£339m) to improve access to mental healthcare in the US

5.The departments of defence, justice and homeland security exploring “smart gun technology” to improve gun safety

A. (http://www.bbc.com/news/world-us-canada-35236630)

Asfaw Gedamu's photo.
Asfaw Gedamu's photo.