ሐጎስ ገዢ መደብ ሲባል ለምን እንናደዳለን? ኤርሚያስ ቶኩማ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ሐጎስ ገዢ መደብ ሲባል ለምን እንናደዳለን? === ኤርሚያስ ቶኩማ ===
አንዳንዴ ልንክዳቸው የማንችላቸው ጉዳዮች አሉ ከዚህም መከካል ዋነኛው የህወሀቶች በኢንቨስትመንት እና በፖለቲካው ላይ ያላቸው ሰፊ እጅ ነው። ኢህአዴግ ድርጅቱን ያዋቀረው መሠረታዊ ድርጅቶቹ እንደወከሉት የህዝብ ብዛት ቢሆን ከሱማሌው ሶህዴፓ እኩል አጋር ድርጅት እንጂ የኢህአዴግ ልብና እስትንፋስ መሆን አይችልም ነበር። በመላ ሐገሪቱ ከላይኛው የሥልጣን እርከን ጀምሮ እስከታችኛው የወረዳ ፅህፈት ቤት ድረስ የሕወሐት ካድሬዎች አመራር ሆነው ተቀምጠዋል። በጣም የሚገርመኝ ወለጋ ወይም ደብረታቦር የሚገኝ ወረዳ ውስጥ የሕወሐት ሰው በምን መመዘኛ ነው የወረዳው ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሚሆነው? ክልሎቹ ሠው አጥተው ነው ወይስ በሐገሪቱ ያለውን ማንኛውም ዜጋ ተዟዙሮ የመስራት መብቱን ለማሳየት ነው?
መካድ የለብንም አርባምንጭ ላይ ገበሬ አፈናቅሎ ለአዜብ መስፍን የሙዝ እርሻ መስጠት በየትኛውም መመዘኛ ትክክል ሊሆን አይችልም።
በየትኛው መመዘኛ ነው ከአንድ ብሔር የወጡ ግለሰቦች ዘጠና ከመቶ የሚሆነውን የመንግሥት ስልጣን ሲይዙ ትክክል ሊሆን የሚችለው?
በኢኮኖሚውም ያለው ሁኔታ ተመሳሳይ ነው አሁን በልማት ምክንያት ፈርሶ እንደሆነ ባላውቅም ደግሞም አይፈርስም ከመገናኛ ወደጉርድ ሾላ ስትሄዱ የሚገኙትን የብረት አከፋፋዮች ማስታወቂያ በአእምሯቹህ ውስጥ አስቡት “ገብረ ተንሣይ የብረት ማከፋፈያ” “ሕሩይ የሲሚንቶ ማከፋፈያ” በርሄ፣ ለታይ እያለ ይቀጥላል ከእነዚህ ውስጥ ቶላ ወይም ከበደ የሚል ስም ልታገኙ አትችሉም ካገኛችሁም በእርግጠኝነት ከበደና ቶላ ጉልበት ሠራተኞቹ ናቸው እንዴት ነው ይህ ትክክል ሊሆን የሚችለው?
እውነት እናውራማ ከተባለ ኦሮሚያ ባንክ እራሱ ጭምብሉን ቢያወልቅ እውነት የኦሮሚያ ልጆች የተቆጣጠሩት ነው? ኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ከስሮ ወደንግድ ባንክ ሲጠቃለል ንብ፣ ወጋገን እና አንበሳ ባንክ በየትኛው ደንበኛቸው ነው ከኪሳራ ያመለጡት?
እውነታው ይሄ ሆኖ ሳለ ሐጎስ እየበላ ቶላና ከበደ በረሐብ ሊሞቱ አይገባም ስላልን ለምን ዘረኛ እንባላለን?
መፍትሔው ህወሀትን የሚቃወመውን እየጠበቁ ዘረኛ ማለት ሳይሆን ህወሐት የትግራይ ህዝብን በሌላው ህዝብ ጥርስ ውስጥ እንዲገባ እያደረገው ነው ስለሆነም እኛ የትግራይ ልሂቃን ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር በጋራ በመቆም የሕወሐት አገዛዝን እንቃወማለን በማለት አጋርነትን ማሳየት ነው አጋርነት ሲባል እንደገብሩ አሥራት ጊዜ ሲጎድል አይቶ ለግል ጥቅም ሲባል ህወሀትን መቃወም ሣይሆን እየሆነ ያለው ነገር በሀገርና በታሪክ ላይ ሊያደርስ የሚችለውን አደጋ በመመልከት ሐጎስ ጮማ እየበላ ከበደና ቶላ ጥሬ ሊያርባቸው አይገባም ከሚል ቅንነት መሆን ይኖርበታል።
#ኤርሚያስ_ቶኩማ