የጋለውን ብረት ሳይበርድ በጋራ ከመቀጥቀጥ ይልቅ እርስበራሳችን የምንቀጣቀጥ ካለፈ መማር ያልቻልን የራሳችን ጠላቶች ሆነናል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ምንሊክ ሳልሳዊ : – ከአንድ አይነት አስተሳሰብ እናስብ ከሚለው ድሃ አስተሳሰብ ወጥተን በአንድነት እንታገል ተባለ…. የለም …. ከተናጠል ትግል በጋራ ተባብረን እንስራ ተባለ … የለም … ከዚህ ሁሉ ይበልጥ የሳይበር ዘረኝነት በማህበራዊ ድረገጽ ተስፋፍቶ ይታያል::.. ብረት እንደጋል ይቀጠቀጣል እና የሕዝቡን ተቃውሞ በጋራ ቆመን በጋራ ጨቋኙን የሕወሓት አገዛዝ እንጥላለን ብለን (ስንረባረብ)መረባረብ ሲገባን እኔማናቸው ስማቸው በጎንዮች የዘረኝነት ጥዝጠዛውን ይዘው ህዝብን ከማስተባበር ይልቅ የጎሪጥ ተለያይቶ የጋራ ጠላቱን በሚመታበት ሰአት እርስ በራሱ እየተወራወረ እንዲፈነካከት ክፍተት እየተፈጠረ ይገኛል::
በማህበራዊ ድረገጽ ላይ እጅግ የበሰሉ እና የሰከኑ ሰዎችን ለማግኘት አዳጋች በሆነበት በዚህ ያል በሰሉ ባዶዎች ስሜታዊ ዘረኞች በሞሉበት የዲያስፖራው አለም እና ጥቂት የሃገር ውስጥ ቅምጥ ፖለቲከኞች እና የአገዛዙ አቀባባይ ካድሬዎች ድፍርስ የሆነ አተላ አስተሳሰባቸውን እያራገፉብን ይገኛሉ::የሕዝብን ተቃውሞ የለውጥ ሃይሉ በቁም ነገር ለነጻነት እና ለመብት መከበር የተከፈተ በር በማድረግ አስተባብሮ ድል ያመጣል በሚባልበት በዚህ ወሳኝ ወቅት ላይ ወደ ዘረኝነት ጡዘት በመለወጥ እርስ በርሱ እየተጠባጠበበት ይገኛል::ለወያኔው ቡድን የፖለቲካ ጥቅም ከመሆኑ በተጨማሪ ጉዳዩን በኣጽንኦት የሚከታተሉ የሕዝብ ልጆች ለማንኛውም አካል ታማኝነት እንዳያገኝ ወደ ዝምታው እንደሚዘልቁ ማወቁ ደግ ነው::
እየተራመደ የሚገኘው የሳይበር ዘረኝነት ለወያኔ እድሜ ከማስረዘም ውጪ እና መረጃዎችን ከማደፍረስ ውጪ ምንም የሚጠቅመው ጥቅም የለም::አንዱ ሌላኛውን ለመስደብ ሲያቆበቁብ አሊያ ሲተች ልጥላኛው አካል ደሞ በተናጋሪው አካል ላይ ያለው ተኣማኒነት ይጎልበትና ከትግሉ ፊቱን ያዞራል::ይህን ጊዜ መከፋፈል እና ክፍተት ስለሚፈጠር ለጠላት ሃይል ጥርጊያ እንደማበጀት መሆኑን ልናውቅ ይገባል::ዘላለማችንን ዘረኝነትን እንደፈተፈትን ካለፈው መማር ያልቻልን የራሳችን ጠላቶች መሆንን ማቅም አለብን:: #ምንሊክሳልሳዊ