የመድረክ መሪው ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ለአንድነት ትግሉ እንቅፋት ከመሆናቸውም በላይ የኦሮሞ ሕዝብን ተቃውሞ ለመሸፋፈን እየሞከሩ ሲሉ የመድረክ አባላት ወነጀሉ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰናል// አሁን ላለንበት አሳሳቢ ሁኔታ– ትግሉ የነጻነት፣ የዲሞክራሲና የፍትህ ሆኖ ባለበት በተናጠል የሚደረገው ትግል ከመቼውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ለጥቃት እየዳረገን ባለበት ዛሬም ትናንት ተስፋ አላቸው ብለን ስንጠራቸው የነበሩት መድረክች ሰማያዊ ፓርቲን በማሳሳት ስለትብብር በተለመደው መንገድ ለማወጅ እመከሩ ነው የሚል መረጃ እየደረሰን ነው፡፡

https://encrypted-tbn2.gstatic.com/images?q=tbn:ANd9GcRlPZpmoCD-KIoKvD6xAbVTYd_ulw3wwCIsvqU95USSbevSXj2U

በዚህ መረጃ ላይ ተመስርተን ባደረግነው ክትትልና ባገኘነው ተጨባጭ መረጃ መሰረት ላለፉት 25 ዓመታት በተደረጉ አብሮ መስራት ጥረቶች ሁሉ አመራሩን ካልተቆጣጠሩ ሲያፈርሱ ሲያንስም ሲያደናቅፉ የነበሩት ፕ/ር በየነ ጥሮስ አሁንም ይህንኑ የሥልጣን ጥያቄ በማንሳት ጥረቱ እንዳይሳካ እያደረጉ መሆኑንና ጠንካራ ታጋዮችም ተስፋ እየቆረጡ እንደሆነ ማረጋገጥ ችለናል፡፡ የተገኙት ተጨባጭ መረጃዎችም–

 

1. በየመድረክ 4ቱ አባል ድርጅቶች /ኢሶዴ፤ደቡብ ኅብረት ፓርቲ፣ኦፌኮ፣ ዐረና፣ ሲኣን/ በአንድ ልብ እንደ መድረክ ለመስራት ካለመቻል አልፈው ተወጣጥረው ያሉበት ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡

ለዚህም አንዱና ዋናው ማስረጃ መድረክ በኦሮሚያ ከማስተር ፕላኑ በተያያዘ በተደረገው እንቅስቃሴ የኦፌኮን ጥያቄ ለመጋራትና ለማስተናገድ አልፎም በጋር ለመስራት ዳተኛ በመሆኑ ኦፌኮ ለብቻው ለመጮህ የተገደደበት፣ እንዲሁም ዘግይቶም ቢሆን መድረክ በሰጠው መግለጫ ላይ የሟቾችንና ተጎጂዎችን ቁጥር ኦፌኮ ከሰጠው ቁጥር አሳንሶ ማቅረቡ እና ኦፌኮ የመድረክን አጋርነት ሲነፈግ ከሰማያዊ ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት መፈጸሙ ናቸው፡፡

2. ከላይ በመድረክ አባል ድርጅቶች በተፈጠረው መሳሳብ ሁለት ጎራ በግልጽ የወጣበት እውነታ ታይቷል፡፡ ኦፌኮና ሲኣን በአንድ ወገን ሲሆኑ ኢሶዴ-ደቡብ ኅብረት ፓርቲ እና ዐረና በሌላው ጥግ ተሰልፈዋል፡፡በዚህ የጎራ አሰላለፍ ኢሶዴ-ደቡብ ኅብረት ፓርቲ ከዐረና ጋር ውህደት በመፈጸም ከኢህአዴግ ጋር በመተባበር ላጠፋህ አልመለስም የሚል መልዕክት እያስተላለፈ መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች ያስረዳሉ፡፡

3. ፕ/ር በየነ በዚህ ሳያበቁ የኦፌኮን አመራር ለመከፋፈል ጭምር ያደረጉት ጥረት ተሳክቶላቸዋል፡፡ በዚህም አቶ ገብሩ ገ/ምሪምን ከዶ/ር መረራ ጋር ካለመተማመን አልፎ ወደማይተማመኑበት ደረጃ አድርሰው እተጠቀሙባቸው መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ዶ/ር መረራና ፕ/ር በየነ ሁለቱም አንዱ ለሌላው የማያልፉበት (ከሁለቱ በቀር ማንም የማውቀው )መስመር ስላሰመሩ ዶ/ር መረራ በፕ/ር በየነ ላይ ያላቸውን ቅሬታ በግልጽ ለሚቀርቧቸው ሁሉ ቢናገሩም ደፍረው ሊታገሏቸው ያለመቻላቸውንና ከርሳቸው መለየት አደጋ እንዳለው መግለጻቸውን በማስረጃነት ያቀርባሉ፡፡እነዚሁ ወገኖች ፕ/ር በየነና ዶ/ር መረራ የሚጋሩት የጋራ አስተሳሰብ መኖሩን ከተሰመረው መስመር ጋር ያያይዙታል፡፡ ይህም ሁለቱም እስርን በጣም መፍራታቸው ነው፡፡ ለዚህም ዶ/ር መረራ በግልጽ ፍርኃታቸውን መግለጻቸውን፣ ፕ/ር በየነም ከዚህ በፊት ስለመታሰር ሲነሳ ‹‹ ማንም እንደ በግ ወስዶ አያስረኝም ›› ማለታቸውን ከገዢው ፓርቲ ጋር አያይዘው በመረጃነት ያቀርባሉ፡፡

4. በእስር ፍርኃት ሁለቱንም በለዘብተኛ አቋም የሚወቅሱት እነዚሁ ምንጮች ዶ/ር መረራ አምርረው ቢነሱም በተሰመረው መስመር ምክንያት ፕ/ር በየነን ገፍተው ለመሄድ በእጅጉ እንደሚቸገሩና ይህንንም በተደጋጋሚ የገለጹ ሲሆን ፕ/ር በየነ ግን ከዶ/ር መረራ በበለጠ ለዘብተኛ ቢሆኑም በዚህ ልክ ዶ/ር መረራን እንደማይፈሩዋቸው ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡

5. ከላይ በተገለጹት መረጃዎች ጋር በተያያዘ በአሁኑ ሰኣት የኦፌኮና ሲኣን አመራሮች ከፕ/ር በየነ ጋር ለመስራት እንደከበዳቸው፣ የዐረና አባላትም አስቸጋሪ ባህሪያቸውን ቢረዱም ከዐረና የማይኖሪቲ ስጋትና ዓላማ አንጻር በምንም መልኩ ቢሆን ከዶ/ር መረራ ፕ/ር በየነን መምረጣቸው ግልጽ ቢሆንም ከፕ/ር ስውርና ግልጽ አካሄድ በተቃራኒ የቆሙ የኦፌኮ አመራሮች ቅሬታቸውን ለፓርቲያቸው ከመግለጽ አልፈው ለአደጋ እንዳይጋለጡ ስጋት እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡ ለዚህም ሃሙስ / ታህሳስ 14/08/ መድረክ በሰጠው መግለጫ ላይ ላለመገኘት ወስነው ወደ አዳማ የሄዱት አቶ በቀለ ገርባ በበነጋው መታሰራቸውንና ለአቶ በቀለ ነጋኣ (በኦሮሚያ የማስተር ፕላን ተቃውሞ የኦፌኮ ተናጋሪና ሁኔታውን በቅርብ የሚከታተሉት) ላይ የተፈጸመውን ድብደባ፣ የተሰጠውን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያና በዚሁ መግለጫ አቶ በቀለ ነጋኣ ከህዝብ ጋር ተቀላቅለው መቀመጣቸውን፣ የመግለጫውን መድረክም ፕ/ር በየነ ከአቶ ገብሩ ገ/ማሪያም ጋር መቆጣጠራቸውን በመረጃነት ያቀርባሉ፡፡

እነዚህ ውስጥ አዋቂዎች በዚህ ተጨባጭ ሁኔታ የመድረክ አባላት አብሮ ለመስራት በራሱም ውስጥ አንድነት በሌለበት ከሰማያዊ ጋር አብሮ ለመስራት ለድርድር የፕ/ር በየነዎቹ አቶ ገብሩ ገ/ማሪያምና የራሳቸው ፓርቲ አባል አቶ ሉምባ ደምሴ በተወከሉበት ዉጤት መጠበቅ ጊዜ መፍጀትና ከንቱ ድካም ነው ፡፡ አንድ ጋት አያራምድም፡፡ ስለሆነም ሰማያዊ ከየፓርቲው የተበተኑ ታጋዮችንና (መኢአድ፣ ሰማያዊ፣ ሌሎች-ኦፌኮን ያገናዝቧል) ሌሎች ሃቀኛ ድርጅቶችን የሚያሰባስብ የፕሮግራም ማስተካከያ አድርጎ /ከልሶ ትግሉን የማስተባበርና ማቀናጀት ኃላፊነት ላይ ቢያተኩር ይሻላል ሲሉ ይመክራሉ፡፡ ፕ/ር በየነ ከሰማያዊ ጋር የተጀመረው ድርድር ዳር እንዳይደርስ ከወዲሁ የተበተነውን/የተከፋፈለውን ‹‹መኢአድ›› በማስፈራሪያነት ሰማያዊ ጋር ለመስራት ከተስማማን መኢአድም መምጣት አለበት በማለት አስቀድመው እየጮሁ መሆናቸውን ለጥረቱ አለመሳካት የትንበያ መነሻ አድርገው በማቅረብ ከፕ/ር በየነ ጋር ሆኖ የትም አይደረስም በማለት ያጠቃልላሉ፡፡