በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች ከጥር 6 እስከ ጥር 8 – 2008 የሚካሄድ ሕዝባዊ ተቃውሞ !!


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች ከጥር 6 እስከ ጥር 8 – 2008 የሚካሄድ ሕዝባዊ ተቃውሞ !!

Minilik Salsawi's photo.

#‎Ethiopia‬ ‪#‎AddisAbaba‬ ‪#‎FreedomVoice‬

=========== ተቃውሞዉ የሚገለፀዉ በኡኡታና በኳኳታ ይሆናል ። ==========
በተጠቀሱት ቀናቶች ሁላችንም በያለንበት ቦታ በመሆን የአገዛዝ ስርዓቱ በህዝብና በሃገር ላይ እየፈፀም ያለውን ወንጀል ፣ ህጋዊ ጥያቄ ባቀረቡ ዜጎች ላይ አየተወሰደ ያለዉን እስራት ና ግድያ ፣ የሃገራችን ድንበር ለሱዳን መንግስት ተቆርሶ መሰጠቱን እንቃወማለን ።

ኡኡታ ፦ ሁላችንም በያለንበት ( በመኖርያ ደጃፍ ፤ ጊቢ ዉስጥ ፣ በስራ ቦታ ፣ በመንገድ ላይ …..ወዘተ ኡኡታ ማሰማት )

ኳኳታ ፦ በአቅራቢያችን ድምፅ ማሰማት የሚችሉ ማንኛዉንም ነገሮች ማስጮህ ( ማብሰያ መመገቢያ ቁሳቁስ ፣ የቆርቆሮ የብረት አጥርና በር ፣ ተሽከርካሪዎች ፣ የተለያዮ ሰራዎች ማከናወኛ መሳሪያዎች ፣ በመንገድ በግርግዳ ተለጣፊ ወይም ተንጠልጣይ ማወስታወቂያዎች፣ የብረት ምሶሶዏችና ድልድዮች…….ወዘተ በመደብደብ በማጋጨት ማስጮህ )

እነዚህ ተግባራቶች በተመሳሳይ ሰዓት ከተለያየ ስፍራ ለመፈፀም የሚያመቹ ፣ አንድ ላይ መሰብሰብን የግድ የማይሉ ሲሆኑ ጨቋኙን የወያኔ ስርዓት ለማስዐገድ አንቅፋት የሆኑብንን ፍርሃትና መለያያትን በቀላሉ የምንሰብርባቸዉ እንዲሁም የእምቢተኝነት መግለጫዏች ናቸዉ።

የጊዜ ሰሌዳና ተግባር ፦
ጥር 6 ዐርብ ጠዋት 4 ሰዓት ከሰዓት በኃላ 7 ሰዓት ምሽት 2 ሰዓት ጀምሮ ከ 10-15 ደቂቃ ኡኡታ ….ኡኡታ
( የቀኑ መርሃ ግብር ከጁምዐ ሶላት በፊትና ሶላት ከተጠናቀቀ በኃላ ይሆናል )

ጥር 7 ቅዳሜ ጠዋት 4 ሰዓት ከሰዓት በኃላ 7 ምሽት 2
ሰዓት ጀምሮ ከ10-15 ደቂቃ ኳኳታ…..ኳኳታ

ጥር 8 እሁድ ጠዋት 4 ሰዓት ከሰዓት በኃላ 7
ሰዓት ጀምሮ ከ10-15 ደቂቃ ኡኡታ….ኡኡታ
( የቀኑ መርሃ ግብር የቤተክርስቲያኖች ፀሎት ከተጠናቀቀ በኃላ ይሆናል )

ጥር 8 እሁድ ምሽት ከ2 ሰዓት ጀምሮ ከ10-15 ኡኡታና ኳኳታ … ኡኡታ ኳኳታ በመቀላቀል እምቢተኝነታችንን ገልፀን የመጀመሪያዉ ዙር የተቃዉሞ መረሃ ግብራችን ይጠናቀቃል።

አስተባባሪ ኮሚቴው ።

==================== አንድ ነፃነቱን የሚወድ ኢትዮጵያዊ =================

‪#‎በቀን_አንድ_ብር_ይጣል‬

ይህ ዘመቻ በቀን አንድ ብር እየጣልን ‪#‎ለአንድ_ወር‬ ይቆያል::የብር ተቃዉሞ በቀን 1 ብር ላይ ሁለታችን የተቃዉሞ ድምፃችን እናሰማ::

ሁሉም ነፃነት የናፈቀዉ በቀን አንድ ብር ላይ የሚከተሉትን በእስክሪብቶ ወይም በሀይላይት ማርከር የሚከተሉትን እየፃፈ ህዝብ በሚበዛባቸዉ ሁሉ እየጣለ ይዉጣ::

1. ወያኔ እንዲያቆም የምንፈልመልገዉን የተሰማንን በአጭሩ

2. መፃፍ ያለባቸዉ

#‪#‎ወያኔ‬ የአባቶቻችን ርስት ለሱዳን እንዳትሞክረዉ ዋ!
#‪#‎በኦሮሞና‬ አማራ ሶማሌ ወገኖቻችን ላይ ግፍክን አቁም ዋ! ዋ!
#‪#‎መሬታችን‬ ላይ እጅህን አንሳ!! በቃን ስልጣንህን ለህዝብ አስረክብ!! ዋ! ዋ!
#‪#‎ፖሊስ‬ ካድሬና ወታደር ወደቤተስብህ አብረህ ለነፃነት ቁም::

ዘረኛዉ ወያኔ በቃን:: የሚሉ ፅንሰ ሀሳቦችን እንጠቀም::
በምንችለዉ አቅም እንደየአቅማችን እናሳጥረዉ::
አንድ ብሩን ፅፈን ካዘጋጀን በሁዋላ ህዝብ የሚሰበሰብበት ቦታ ወስደን እንጣለዉ::
ይህን ተቃዉሞ ለቀጣይ ሰላሳ ቀናት… እንከዉን:: ነፃነታችን እስክናገኝ በተለያየ መልኩ ተቃዉሟችን ይቀጥላል::
ብሩን ጥሎ መሄድ ብቻ:: ብር ነዉና ማንም ያነሰዋል:: በነገራችን ላይ በወረቀት የብርን ኮፒ ፕሪንት መጠቀምም ይቻላል::
የሚጣልባቸዉ ቦታወች ህዝብ ቢያንስ ከአስር በላይ ከሚገኝባቸዉ እስከ ገበያ ሆስፒታሎች የማምለኪያ ቦታወች:: ገደብ የለዉም::
ተቃዉሞዉ ከሰኞ ጠዋት ከ25/04/2008 ጀምሮ ለአንድ ወር::