በደቡብ ምስራቅ እዝ የረሃብ አድማ ያደረጉ ወታደሮች ሲታሰሩ በስሜን እዝ ሊደረግ የነበረው ግምገማ እንደሰረዝ ተወስኗል::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ከምድር ጦር መምሪያ የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በሰራዊቱ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ አለመግባባቶች እየተከሰቱ ሲሆን የሰራዊቱ አባላት ከተለያዩ ቦታዎች የሚያገኟቸው መረጃዎች የተነሳ በሚፈጠሩ ችግሮች የበላይ አዛዦች እና መኮንኖች እንዲሁም ተራ ወታደሮች ቅራኔ ውስጥ እየገቡ መሆኑ ታውቋል::የሰራዊቱ አባላት የህጋሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ የሚያቀርቡት ጥያቄ መልስ ማጣቱ በአንድ ብሄር የበላይነት በጭቆና ቀንበር ስር ጦሩ መተዳደሩ እና የሕገመንግስቱ ጉዳይ ከዚህ ቀደም የሚያጨቃጭቅ ቢሆንም የአሁኑ ግን ሃገሪቷ ያለችበት አጣብቂኝ የፈጠረው ጥያቄ ቅራኔዎች እየጋሉ እንዲሄዱ አድርጓል::

የኦሮሞ ተማሪዎችን እና ገበሬዎችን ለተቃውሞ አደባባይ መውጣት እና በወያኔ አገዛዝ ሃይሎች የተወሰደውን ግድያ የተቃወሙ 17 የደቡብ ምስራቅ እዝ አባላት የረሃብ አድማ ያደረጉ ቢሆንም ለእስር መዳረጋቸው ታውቋል::እነዚሁ የኦሮሞ ብሄር ወታደሮች የኦነግ አቀንቃኞች በሚል ታርጋ ተለጥፎባቸው ወደ ሃረር ወታደራዊ እስር ቤት መላካቸው ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ የተናገሩ ሲሆን በደቡብ ምስራቅ እዝ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ በሰራዊቱ አባላት እና በሃላፊዎቻቸው መካከል በሚከሰት አለመግባባት እና አለመተማመን የተነሳ ቁጥሩ በርካታ የሆነ የወታደራዊ ደህንነት ቡድን በየክፍሉ በወታደር ስም ተቀላቅሎ እንዲመደብ መደረጉ ይታወሳል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰሜን እዝ ሊደረግ የነበረ ግምገማ መሰረዙ ታውቋል::ተዋጉ ተብለው ቢላኩ መሳሪያቸውን አስቀምጠው እጃቸውን ይሰጣሉ የተባሉ ወታደሮች የሞሉበት የሰሜን እዝ እንዲሁም ከሰሜን እዝ ይልቅ ሕወሓት የትግራይ ሚሊሻን እና የቀድሞ ታጋዮችን እተማመናለሁ ስለሚል ሊደረግ የታሰበው ግምገማ መልሶ በተቃውሞ አገዛዙ ሊመታ ይችላል በሚል ፍራቻ እንደተሰረዘ ለመከላከያ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ተናግረዋል::የሰሜን እዝ የሚባለውን ዳግም ለማዋቀር ጥናት እየተካሄደ ሲሆን ከግምገማው ይልቅ በጥናቱ የሚገኘው ውጤት ቢተገበር የተሻለ ነው ሲሉ የሕወሓት ጄኔራሎች ተስማምተዋል::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬