የሰማያዊ ፓርቲ 4ኛ አመት ምስረታ ! ይድነቃቸው ከበደ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የሰማያዊ ፓርቲ ምስረታ !  =  ይድነቃቸው ከበደ

ሰማያዊ ፓርቲ ታሕሳስ 22 ቀን 2004 ዓ.ም በይፍ የተመሰረተበት ቀን ነው፡፡የፓርቲያችን የ4 ዓመት ጉዞ እና በሂደት ያጋጣሙ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ፣ለፓርቲያችን የወደፊት እንቅስቃሴ በጎ አሰተዋጾ እንደሚኖረው እምነቴ ከፍ ያለ ነው፡፡ ፓርቲችን ከተመሰረት 4 ዓመት ይሁነው እንጂ፣ በአገራችን ወቅታዊ የፓለቲካ እንቅስቃሴ፣ በግንባር ቀደምትነት ስማቸው ከሚጠራ ፓርቲዎች ውስጥ አንዱ ለመሆን ችሎአል፡፡
ፓርቲያችን በተለይ ከለፈው አንድ ዓመት ጀምሮ እስካሁን ባላው ጊዜ ፣የፓርቲያችን አመራር እና አባላት እንዱሁም ደጋፊዎቻችን ፣ በአስከፊነቱ ተወዳዳሪ በማይገኝለት የህውሓት/ኢህአዴግ የማጎሪያ እስር ቤት ውስጥ እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡የፓርቲያችን ልሳን የነገረ-ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጌታቸው ሽፈራው የአገዛዙ ሥርዓት ገፈት ቀማሽ ሆኖአል፡፡


ከምንም በላይ ደግሞ የሕግ ባለሙያው እና የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተባባሪ የነበረው ወጣት ሳሙኤል አወቅ ፣የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ሆኖ መንግሥትን በመቃወሙ ብቻ ፣እጅግ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተደብድቦ ሕይወቱን እንዲያጣ ተደርጓል፡፡የሳሙኤል አወቀ ንጹ ደም በፈሰሰበት ቦታ ፣እጃቸው በደም የጨቀየ ነብሰ ገዳዮች ፣የጊዜ ጉዳይ እንጂ ፍርዳቸውን ያገኙበታል!!!
ሰማያዊ ፓርቲ በአገራችን ተካሂዶ የነበረውን የይስሙላ ምርጫ ፣እውነትም ምርጫው የውሸት መሆኑን በይፋ ያጋለጠ ፓርቲ ነው፡፡ፓርቲያችን ከ450 በላይ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪዎችን ያስመዘገበ ቢሆንም፤የህውሓት/ኢህአዴግ አምባገነን መንግሥት ዓይን ባወጣ መልኩ፣ በምርጫ ቦርድ አማካኝነት 200 የሚሆኑ የሰማያዊ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪዎች እንዲሰረዙ ተደርጓል፡፡ይህን ሕገወጥ ተግባር በሕግ ለመዳኘት ፓርቲያችን ጉዳዮን ፍርድ ቤት ይዞ የሄደ ቢሆንም ፣ከፍርድ ቤት ፍትህን ማግኘት አልተቻለም፡፡ይህም በመሆኑ ፓርቲያችን የህውሓት/ኢህአዴግ መንግሥት ምን ያህል አምባገነን እንደሆነ ለአለም ህብረተሰብ ከነ-ቆሻሻ ተግባሩ ለማጋለጥ ችሎአል፡፡
ኢትዮጵያዊነት መለያው የሆነው ፓርቲያችን ፣በምርጫ ቅስቀሳ እና የምረጡኝ ዘመቻ ወቅት ፣የመንግሥትን ጫና በመቋቋም፣ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ አማራጭ አገር የማስተዳደር እቅድ ለኢትዮጵያዊን እንዲደርስ አድጓአል፡፡በምርጫ ክርክር ወቅትም ባደረጋቸው ክርክሮች ሁሉ፣ የፓርቲያን ተወካዮች የፓርቲውን አማራጭ ሃሳብ በእውቀት ላይ የተመሠረት ክርክር አድርገው በአሸናፊነት ተወጥተውታል፡፡

የፓርቲያችን የ4 ዓመት እንቅስቃሴ እና እሱን ተክለው ለመጡ ማናቸውም ነገሮች፣ በአጭሩ ተገልጾ የሚያበቃ ነገር አይደለም፡፡ሆኖም ግን የፓርቲያችን 4ኛ ዓመት ምስራት ሲታሰብ፣ ከሂዳታችን ከብዙ እጅግ በጣም ጢቂቱን ለማስታወስ ያኸል ነው፡፡ከምንም በላይ ደግሞ አሁን ላይ በሥልጣን የሚገኘው አምባገነን መንግሥት ፣እረጅም ታሪክ እና አኩሪ ሕዝብ ያላትን ኢትዮጵያ ፣የማስተዳደር አቅሙም ሆኖ ፍላጎት የሌለው በመሆኑ ፤ሥልጣኑን ለሕዝብ እንዲያስረክብ፣አማራጭ የሰላማዊ የትግል ዘዴዎችን በመጠቀም፣ፓርቲያችን ሲታገል አራት ዓመታትን አስቆጥሯል፣ወደፊትም የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት እሁን እስከሚሆን ድረስ ትግሉ የሚጠይቀውን መሰዋትነት በመክፈል ከአምባገነን አገዛዝ ወደ ዴሚክራሲ የሚደረገው ትግል ይቀጥላል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ ባሁን ወቅት በአገራችን አማራጭ ፓርቲ ብቻ ሣይሆን ተመራጭ ፓርቲ ለመሆን ችሎአል!!!ይህም የሆነው እስከ ሕይወት መሰዋትነት ለመከፈል በቆረጡ የፓርቲው አመራርና አባላት አማካኝነት ነው፡፡ለእንዲ-አይነቱ ትግል ሁሌም ደጀን የሚቆመው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለፓርቲው እድገት ያበረከተው አስተዋጾ መተኪያ የማይገኝለት ነው፡፡ሰማያዊ ፓርቲ ባደረጋቸው ጉዞ፣ በውጪ አገር የሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊን በገንዘብ እና በሃሳብ እንዲሁም በወንድማማችንት ስሜት ፣ከጎናችን በመቆም ያሳዮት ድጋፍ በታሪክ ሁሌም የሚታወስ ነው፡፡
የፓርቲያችን 4ኛ አመት ምስረታ በሚታሰብበት ወቅት፣ በህውሓት/ኢህአዴግ የማጎሪያ እስር ቤት ውስጥ እየተሰቃዮ የሚገኙ ጓዶቻችን ፣ስቃያቸው ከትላንት ዛሬ ትግላችንን ከፍ አድርገን በጽናት እንድንቆም ያደርገናል፡፡የእኛ ትግል ደግሞ ለእነሱ ብርታት ይሆናል!!! አሁንም ትግሉ ይቀጥላል፤ሕዝብ ያሸንፋል!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!