‹‹መንገዶች ሁሉ ወደ መስጊዶች ያመራሉ!›› በሚል መሪ ቃል ነገ ጁመዓ ታህሳስ 22/ 2008 የመጀመሪያ ክፍል የሆነውን መርሀ ግብራችንን በይፋ እንጀምራለን!!! ድምፃችን ይሰማ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


‹‹መንገዶች ሁሉ ወደ መስጊዶች ያመራሉ!›› በሚል መሪ ቃል ነገ ጁመዓ ታህሳስ 22/ 2008 የመጀመሪያ ክፍል የሆነውን መርሀ ግብራችንን በይፋ እንጀምራለን!!! ድምፃችን ይሰማ
‪#‎1460DaysOfPeacefulStruggle‬ ‪#‎EthioMuslimPeacefulStruggle‬

ለፍትህ ስንል ለአራት አመት በጽናት የቆምንበትን ትግላችንን የምንዘክርባቸውን መርሀ ግብሮች በተጠናከረ መልኩ እንተገብራለን!የመጀመሪያ ክፍል የሆነውን መርሀ ግብራችንን ‹‹መንገዶች ሁሉ ወደ መስጊዶች ያመራሉ!›› በሚል መሪ ቃል ነገ ጁመዓ ታህሳስ 22/ 2008 በይፋ እንጀምራለን!!!

ሐሙስ ታህሳስ 21/2008
መንግስት ‹‹ሁሉንም እኔው ካላማሰልኩት አይጠቅመኝም›› በሚል አጓጉል አባዜ የሚመራው አምባገነናዊ ስርዓት ቀደም ብሎ በሀረር በይፋ ያወጀውን እና ከዚያም ቀጥሎ በነበሩት ወራቶች እየተገበረው የነበረውን ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን በአህባሽ አስተምህሮት የማጥመቅ ሂደት ወደ ብቸኛ የሙስሊሙ መንፈሳዊ ተቋም ይዞ የመጣው ልክ የዛሬ አራት አመት ነበር። በዚህ እለት ነው መንግስት በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ላይ ላወጀው ብሄራዊ ጭቆና አስፈጻሚ አድርጎ በቁጥጥሩ ስር ያዋለው መጅሊስ ይህን ተቋም ከሙስሊሙ ህብረተሰብ መቀማቱን ያስታወቀበት ደብዳቤ አወልያ ግቢ የደረሰው። ይህ ደብዳቤ ያሰፈረውን እና ቀጥሎ የሚመጣውን ጸረ-ሙስሊም እና ጸረ-ኢስላም የመንግስት እርምጃ በመቃወም ከተነሱት የአወልያ ኮሌጅ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ትግሉን በመቀበል ሰፊው ሙስሊም ህብረተሰብ ይህን የመንግስትን በሃይማኖት ጣልቃ ገብነት የተቃወመ እና ፍትህን እና ፍትሃዊነትን በዋነኛነት ያነገበ ትግል በጽናት አቀጣጠለው።
በእነዚህ አራት ዓመታት ውስጥ በርካታ መከራ እና ስቃይን እየከፈልን ብንገኝም አላህ (ሱ.ወ) በሰጠን ጽናት አሁንም ለአፋኙ መንግስት እምቢ እንዳልን አለን! መብታችንን በዘላቂነት ማስከበር እስከምንችል ድረስም ዘላቂ እንደምንሆን ለራሳችን ቃል እንገባለን! ከፈጣሪያችንም ጋር ቃል እንጋባለን! ይህንንም በተለያዩ መርሀ ግብሮች በወሩ ውስጥ የምንገልጸው ይሆናል፤ ኢንሻአላህ!
‹‹የአራት አመት ጽናት የቀጣይ ትግላችን መሰረት›› በሚል መሪ ቃል የሚመራው እና ለአንድ ወር የሚዘልቀው መርሃ ግብራችን የመጀመሪያ ክፍል የሆነውን መርሃ ግብር ቀደም ብለን ማስተዋወቃችን ይታወሳል። በመሆኑም ነገ ጁሙዓ በይፋ እንጀምረዋለን። መንግስት በሙስሊሙ ላይ ከወሰዳቸው እምጃዎች መካከል መስጊዶቻችንን እና ሌሎች የእምነት ማዕከላቶቻችንን ከእኛ መንጠቅ አንዱ ነው። ይህ ምንጊዜም የሚሳካለት አይሆንም፤ አንፈቅድምም! በነገው እለት ለእስካሁኑ ጽናት ፈጣሪያችንን ስናመሰግን፣ በቀጣይ ለሚጠብቀን ትግል ጽኑ ቋሚዎች ለመሆን ቃል ስንገባ እና ለዚህም የሀያሉ አላህን (ሱ.ወ) እገዛ ስንከጅል ልባችንን፣ አይናችንን እና አግሮቻችንን ወደመስጅዶቻችን እንዲያመሩ በማድረግ ነው። በመሆኑም በነገው እለት መስጊዶቻችን በአማኞች ይጥለቀለቃሉ! መንገዶች ሁሉ ወደ መስጊዶች ያመራሉ!
ፈጣሪያችንን ተቆጥሮ ለማያልቀው ውለታው ስናመሰግነው፣ እንዲሁም እርሱ በመረጠልን መንገድ ላይ ዘውታሪዎች ለመሆን የእርሱን እገዛ ስንከጅል ንጹህ በሆነች ቀልብ፣ ንጹህ በሆነ ሰውነት እና ንጹህ በሆነ ቦታ መሆኑ ያለው ተመራጭነት የሚያጠያይቅ አይደለም። የመርሀ ግብራችን አካል የሆኑትን፣ – ማለትም ለፈጣሪያችን ምስጋና፣ ለቀጣይ ትግላችን ቃል መጋባት እና ለዚህም የአላህን እገዛ መከጀል – በነገው እለት ነባራዊ ሁኔታው በፈቀደልን መልኩ በግልም፣ በጋራም ሆነን በመተግበር መርሃ ግብራችንን እንጀምራለን። ይህን ይፋዊ የመርሃ ግብሩን አንድ ክፍል ተከትሎ በቀጣይ ቀናቶች የዚያራ መርሃ ግብራችንን የምንተገብር ይሆናል።
‹‹መንገዶች ሁሉ ወደ መስጊዶች ያመራሉ!››
ብሄራዊ ጭቆናን አንሽከምም!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማል!
አላሁ አክበር!

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)'s photo.