አቡነ ማትያስ ሰሞኑን የተፈጠረውን ሕዝባዊ ተቃውሞና ቁጣ ፍራቻ በህክምና ሽፋን አሜሪካ ተደብቀው ከረሙ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
- አቡነ ማትያስ ሰሞኑን የተፈጠረውን ሕዝባዊ ተቃውሞና ቁጣ ፍራቻ በህክምና ሽፋን አሜሪካ ተደብቀው ከረሙ
- ታምሜያለሁ ቢሉም በድብቅ የወያኔን ተልዕኮ ሲፈጽሙና የድለላ ስራ ሲሰሩ እንደነበር ተደርሶበታል
- ሹልክ ብለው እንደመጡ፣ ሹልክ ብለው ሊመለሱ ነው
የመናኞች መናኝ፣ የመነኮሳት መነኩሴ፣ የክርስቶስ ምሳሌ ነኝ ብለው በፓትርያርክነት የተቀመጡት አቡነ ማትያስ ሕዝባዊ ቁጣን ሸሽተው አሜሪካ ተደብቀው ከከረሙ በኋላ እ.አ.አ. ጃንዋሪ 3 ቀን 2016 ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ። አቡነ ማትያስ አሜሪካ የገቡት ሰኞ ዲሴምበር 7 ቀን 2015 ጠዋት በቨርጅንያ ግዛት ውስጥ በሚገኘው ዳላስ የአየር ማረፊያ በኩል መሆኑንና የተቀበሏቸውም አቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) ብቻቸውን እንደሆነ ተረጋግጧል። በወቅቱ ሁለቱም መነኮሳት የፓትርያርክነት ልብሳቸውን ይልበሱ አይልበሱ የታወቀ ነገር የለም። ስለ ልብሳቸው የተፃፈውን ለማንበብ ከፈለጉ የሚቀጥለውን የዚህን ዘገባ የመጨረሻውን ገጽ ይመልከቱ።ዘመቻ “አባ መላኩ” በዲሲ ር/አ/ደ/ሰ/ቅ/ ማርያም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ – አባ መላኩ ሠራዊታቸውን አሰለፉ
ፓትርያርኩ ለሕክምና ወደ አሜሪካ አመሩ ተብሎ ቢዘግብላቸውም አማኞች ብዙ ጥያቄዎች ሲያነሱ ሰንብቷል። ሐራ ተዋሄዶ የተባለው ደረ ገጽ የዜና ማሰራጫ እንደዘገበውና ከተለያዩ ምንጮችም እንዳጣራነው የበዓታ ለማርያምን በዓል በዲሲ መድኃኔዓለም ለማክበር መገኘታቸውን አረጋግጠናል። እ.አ.አ. እሁድ ዲሴምበር 13 ቀን 2015 የቀደሱት ወያኔ ስልጣን ሲይዝ እሳቸው የገነጠሉት ቤተክርስቲያን ዉስጥ እንደነበር ተረጋግጧል። አባ ማትያስ በነዋየ ቅድሳት ጉዳይ አሁን ቴምፕል ሂል፣ ሜሪ ላንድ ውስጥ የሚገኘውን አንጋፋውን የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን ምእመናንን በዓለማዊ ዳኛ ፊት ለሙግት በማቅረብ የመጀመሪያው ካህን ናቸው። በዚህም ተግባራቸው መካሰስ ይቅርና ለሞራል ልዕልና መወራረጃ በማድረግ ለኖረው ህዝበ ክርስቲያን ንዋየ ቅድሳቱን የእርስ በርስ መካሰሻ ያደርገው ዘንድ መጥፎ ምሳሌ ትተው በማለፍ አሁንም ጭቅጭቅና ንግርክ የበርካታ ቤተክርስቲያኖች እጣ ፋንታ ሆኗል። በተለይም አቡነ ማትያስ የቤተክርስቲያንን መመሪያ ጥሰው ሲያቆርቧቸው የነበሩትን የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን ህዝበ ክርስቲያንንና ወንድማቸውን አቡነ ይስሐቅን በዓለማዊ ፍርድ ቤት ከሰው የቆሙ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ መነኩሴ ናቸው የሚሉም አሉ።
ስለ አቡነ ማትያስ ወደ አሜሪካ መምጣት የተለያዩ አካላትናን ለቤተክርስቲያን ቅርበት ያላቸውን ምዕመናንን አነጋግረን ያገናቸው ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው።
• አንድ ፓትሪያርክ ከኢትዮጵያ ወደ ዉጭ አገር ሲንቀሳቀሱ እንደ አንድ ተራ ሰው ድምፅ ሳያሰሙ የመጡት እውነት ለህክምና ከሆነ ሌላው ቢቀር ተከታዮቻቸው እንዴት አውሮፕላን ማረፊያ ሄደው አልተቀበሏቸውም? እንደሰማነው በጣም ታምው በቃሬዛ አልመጡም።
• ለመሆኑ ከአገር ቤት አሜሪካን አገር ሊያስመጣ የሚችል የህክምና አስፈላጊነት ነበረባቸውን? ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው እዛው ኢትዮጵያ መታከም ይችሉ ነበር ነው የሚለው።
• ሕክምናው ያስፈልጋቸዋልና አሜሪካ ይመጣሉ ቢባልም እንደሳቸው ያለ የፓትርያርክ ስልጣን ያለው አባት በአሁኑ ወቅት ከ 20 ሚሊዮን በላይ የሚደርሰው የኢትዮጵያ ሕዝብ በርሀብ አለንጋ እየተገረፈ ባለበትና ርሃቡም የሰው ህይወት እየቀጠፈ ባለበት አስጨናቂ ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያዉያንን ማበረታታትና ማፅናናት አልነበረባቸውምን? የመናኞች መናኝ፣ የመነኮሳት መነኩሴ፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ መሆን የሚገባቸው አባት በዚህ ሁኔት መጡ ሲባል እጅግ የሚያስደነግጥ ነው።
• ከዚህም ባሻገር በአገሪቱ ዉስጥ እየተደረገ ያለው የህዝብ ተቃውሞና ቁጣ በጥይት፣ በወታደር ዱላና በእስር መከራ የሚወርድበትን፣ እንዲሁም የሚገደለውን ወገን ማጽናናትና መርዳት ሲጠበቅባቸው እንዱሁም አገዛዙን በመገጸጽ የህዝብን እልቂትን ማብረደት አልነበረባቸውምን?
• ምናልባት የዋሽንግተን ዲሲ ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያምን ቤተክርስቲያን በእጃቸው ለማስገባት ያቀዱትን ሥራ ከግብ ለማድረስ የሳቸውን መኖር የፈልጉት አዲሱ አበበና ግብር አበሮቹ እንዲመጡ ተማጽነዋቸው ነበር ወይ? በርግጥ ወያኔ ይህ ይጠቅመኛል ካላለ በስተቀር ወደ አሜሪካ ሊለቃቸው እንደማይፈልግ በርግጠኛነት መናገር ይቻላል የሚሉም አሉ።
• የአቶ አዲሱ አበበና የአቡነ ፋኑኤል ቡድን ባቀነባበረው እቅድ መሰረት ወያኔም ፈቅዶ ያደረጉት ነው የሚሉም ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። እንደሚታወቀው ወያኔ ሌላን ወገን ለማታለልና የሚፈልገውን ለማድረግ የማያደርገው ነገር የለም። ለሌላው ሕዝብ የአገር መሪ፣ አምባሳደር፣ ጳጳስ፣ ፓትርያርኩ ሁሉ ሰውን በተሸከሙት የይምሰል ስልጣን ተጠቅመው እንደሚያታልሉ በአሁኑ ወቅት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልፅ የሆነ ጉዳይ ነው።
• አቡነ ማትያስ የመጡት ለህክምና በዓታ ለማርያም በዓልን በዲሲ መድኃኔዓለም ለማክበር ብቻ ነውን?
• የዋልድባ ገዳም መሬት ለሱዳን ሊሰጥ ሳምንታት በቀሩበት ወቅት እንዴት ነው እሳቸው አሜሪካ የመጡት? አሁንም ድሮም እንደማንኛውም ተራ ግለሰብ ነው ነው እንዴ እራሳቸውን የሚያዩት? ከአሁን በፊት የተፃፈባቸው ሁሉ ይህንን የሚያረጋግጥ ነው የሚሆነው።
አቡነ ማትያስ በተለያየ አካባቢ ያጋጠማቸውን ተከታትለን ለማጣራት እንደቻልነው ምንም እንኳን ተደብቀው በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ቢሽሎኮሎኩም ከተቃውሞ ማምለጥ አልቻሉም። በርግጥ ጠንከር ያለ ተቃውሞ ያልገጠማቸው እሳቸው ምንም ማድረግ የማይችሉና ቤተክርስቲያኗን የሚያዝባት ኑብረ ዕድ ኤልያስ የተባለው ግለሰብ ስለሆነ አባ ማትያስ ከወያኔ ጋር ከሚሰሩ ተለጣፊ ድርጅቶች የተሻለ አቅም ስሌላቸው ነው ብዙ ተቃውሞ ያልደረሳቸው የሚል አስተያየትም እየተሰተ ነው። ለምሳሌ ሚኖሶታ ሲሄዱ ይገባሉ ከተባሉበት 2 ሰዓት በኋላ ከአውሮፕላን ማረፊያ ሳይወጡ አድፍጠው ከቆዩ በኋላ ቢያዘገዩዋቸውም በ 2 ፖሊሶች ታጅበው ጭለማን ተገን አድርገው ሲደርሱ የነበረውን ተቃውሞ የሚቀጥለውን ሰንሰለት ተጭነው ማየት ይቻላል። (አቡነ ማትያስ የገጠማቸው ተቃሞ )።
አቡነ ማትያስ ሚኒሶታ ደርሰው የሚናገሩት ሁሉ ድንጋጤ የተሞላበት እንደነበር ለማወቅ ችለናል።ሚኒያፖሊስ ተገንጥሎ የወጣው የመድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን አውደ ምሕረት ላይ ቆመው የተናገሩት እጅግ ይገርማል፣ያሳፍራል።
”ከናንተው የተለዩት ሰባኪ አስመጡ ብላችሁ ተቃጥላችሁ ነበር። ጳጳስ መጣላቸው ብላችሁ ተቃጥላችሁ ነበር። አሁን ግን እግዚአብሔር ፓትርያርክ አመጣላችሁ። ደስ ይበላችሁ።” የሚል ነበር። ይታያችሁ እንግዲህ ፓትርያርክ እራሳቸው ሲሆኑ ከሁሉ በላይ መስሎ መታየትና ማሰብ እንዲሁም እራስን መከመር ክርስቲያን ያሰኛልን? በተመሳሳይ መልኩ በዴንቨር ኮሎራዶ ተቃውሞ እንደገጠማቸውም ተጠቁሟል።
አቡነ ማቲያስ በእርግጥ እስከ አሁን ድረስ እንደ አቡነ ጳውሎስ ከወያኔ ጋር ያላቸው ፍቅር አስክሯቸው ወንጀል በግላጭ መፈጸም መጀመራቸው ባይሰማም ማለትም አቡነ ጳውሎስ በግፍ ደማቸውን አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንዳስፈሰሱት እንደ ባሕታዊ ፈቃደ ሥላሴ ነፍስ በቀጥታ ባያስጠፉም በተለይ የወልድባ ገዳም መነኮሳት ላይ የሚፈጸመውን ግፍና መከራ እንዲሁም ገዳሙ ላይ እየደረሰ ያለውን ውድመት ለማስቆም አለመቻላቸው የወያኔ አሸርጋጅ አንጂ የቤተክርስቲያንና የምዕመናን ተንከባካቢ አለመሆናቸውን የሚያረጋግጥ ነው። የአቡነ ማትያስን እንደሰው ገርነትና መልካም መሆናቸውን በሰፊው የሚመሰክሩት ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ የፃፏቸው ሁለት ፅሁፎች ይጠቀሳሉ። እንዲህ ያለ ፓትርያርክ አይተን አናውቅም ተብሎ የተፃፈባቸው እውነትም የመንበረ ፕትርክናውን የማይመጥኑ “ጭንጋፍ (ምቱር) ፓትርያርክ” የሚለውን በተግባር እየፈፀሙ ያሉ ይመስላሉ።