4 አመታት ለእምነት ነፃነት አቡ ዳውድ ኡስማን
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።

4 አመታት ለእምነት ነፃነት =
አቡ ዳውድ ኡስማን =
በእምነታን ላይ የተቃጣውን ጥቃት ለማውገዝ እና ለመከላከል አቅም በፈቀደው መልኩ በአላህ ላይ ተሰፋ አድርጎ መታገል ከተጀመረ 4 ድፍን አመታት እየተቆጠረ ይገኛል፡፡ ማንም ሙስሊም የሚያደርገው ትግል ለራሱ ሲል ብቻ ነው፡፡ በአላህ ዘንድ የሚጠየቀው ሸሪዓዊ መስመሩን ጠብቆ ባለመታገሉ እንጂ ድልን ባለማምጣቱ አይደለም፡፡ ድል ሰጪም ነሺም ከአርሹ በላይ ያለው የአለማቱ ጌታችን አላህ (ሱ.ወ) ብቻ ነው፡፡
የሰላማዊ ትግሉ የውጤት መሠረቱ በአላህ ላይ ያለን ፅኑ እምነት(ተውኩል) ፣ ወደ አላህ በምናደርገው ቀረቤታ እና ታዣዥነት፣ በሃቅ ላይ አንድነታችን በመጠበቃችን እና ህገ መንግስታዊ መሠረት ላለው የሃይማኖት ነፃነታችንና ለጋራ የእምነት ተቋማቶቻችን ባለቤትነት መከበር በግል እና በጋራ የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማድረግ ያለን ቁርጠኝነት ነው፡፡
ሁሉም ሰው አንድ ነገር ቢያውቅ መልካም ይመስለናል፡፡ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለድፍን 4 አመታት በሰላማዊ መንገድ መብታችንን ስንጠይቅ የማንንም መብት እና ነፃነት አልተጋፋንም፡ ፡ስለዚህም በማንም አካል መገፋትን አሜን ብለን አንቀበልም፡፡
ዱላን፣ እሥርን አልያም ሞትን ፈር ማንም የማንም ባርያ ለመሆን ፈቃደኛ ይሆናል ብላችሁ ባታስቡ መልካም ነው፡፡አራት አመታት ለኢስላም መታገል ማለት ምንም ማለት አይደለም፡፡ ኢስላም ከደማችን እና ከስጋችን በላይ ውድ መሆኑን ልታውቁ ይገባል፡፡
አላሁ አክበር
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩