የሰሞኑ የሕዝብ የለውጥ እንቅስቃሴ የደበቃቸው ዜጎች = በረሃብ የተጎዱ ወገኖቻችን 20 ሚሊዮን ገብተዋል::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የሰሞኑ የሕዝብ የለውጥ እንቅስቃሴ የደበቃቸው ዜጎች = በረሃብ የተጎዱ ወገኖቻችን 20 ሚሊዮን ገብተዋል::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Ethiopiafamine‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎USAID‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Drought‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በስራ አጋጣሚ ያገኘሁት በተለያየ ስብሰባዎች ላይ በአንድ ሳህን ሲለን ቡፌ ሲለን ኮክቴል ያነሳን የተመገብን ወዳጄ እንደሚለው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ረሃብ ድርቅ እና እርዳታን በተመለከተ ከሚያጠኑ ከሚያስተባብሩ የእርዳታ ድርጅቶች ውስጥ ከተገኙ መረጃዎች እስጥ አጥቅሶ እንደሚጠቁመው የረሃብተኝው ቁጥር 20 ሚሊዮን ከመድረሱም በላይ በረሃብ የተጎዳው ወገን ቀየውን ጥሎ እየተሰደደ ነው ከዚሁ ጋር በተያያዘ በመንግስት በኩል የሚከፋፈለው እርዳታ ለተራበ ሳይሆን ለጠገበ እየተሰጠ መሆኑን የአሜሪካ የእርዳታ ድርጅት የሰጠው እህል በምሳሌነት ዋቢ አድርጎ አጫውቶኛል:: ጥቂት ካድሬዎች እየከበሩበት ነው ሲሉ የእርዳታ ድርጅት ሰራተኞች ከከተቡት ማስታወሻ የተወሰደ ቃል ይጠቁማል::

Minilik Salsawi's photo.

በረሃብ የተጎዱ ወገኖቻችን ለመታደግ የሚያስችል ወጪ ለተቃውሞ የወጡ ዜጎችን ለመግደል ያዋለው የወያኔው አገዛዝ ባልፉት ሳምንታት የተነሱ እስካሁን ያልበረዱ የሕዝብ ተቃውሞዎች ረሃቡን እንደሸፈኑለት የሕዝቡንም አትኩሮት እንዳስቀየሱለት አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ::ቢሆንም ሕዝቡ አደባባይ የወጣው በብሶት መሆኑና ረሃቡን አንደናው የብሶት አካል መሆኑን የሚናገሩ ዜጎች አልጠፉም::የአገዛዙ ባለስልጣናት ላለፉት 50 አመታት ያልተከሰተ ረሃብ በኢትዮጵያ ውስጥ እንዳለ ሳይደብጉ ያገጠጠጠውን እውነት ወደም ብለው ቢክዱም አሁን አምነዋል::

ይህ ወያኔ ሊደብቀው ቢሞክር በአለም ደረጃ የተጋለጥው በሰሞኑ ሕዝባዊ ንቅናቄ በትንሹ የተዘነጋው ረሃብ እየተስፋፋ ነው:: እስከሚቀጥለው ሃምሌ 2016 ድረስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ 11.6 ሚሊዮን ሕዝብ እርዳታ የሚፈልግ ሲሆን እንዲሁም ከዚህ ከረሃቡ ጋር በተያያዘ 435 ሺህ አባወራዎች(ከነቤተሰቦቻቸው) በሚቀጥለው 3 ወራት ከቀያቸው ይፈናቀላሉ::በአሁን ሰአት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከገመተው ከ15 ሚሊዮን ሕዝብ አሃዝ በላይ የረሃብተኛው ቁጥር 20 ሚሊዮን መድረሱን በሃገር ውስጥ በጥናት ላይ የተሰማሩ የእርዳታ ድርጅት ሰዎች ይናገራሉ:: ሪፖርቱን እስከሰሩበት ድረስ የምግብ ዋስትና ሊያገኝ ከሚገባው ሕዝብ ውስጥ እስካሁን ያገነው 27 ከመቶው ብቻ እንደሆነ እና ይህም የሸፈኑት 23 በመቶ የምግብ እና እርሻ ድርጅት(ፋኦ) ሲሆን አራት ፐርሰንቱን ደሞ መንግስት እንደሆነ የሚናገሩት የጥርዳታ ድርጅት አጥኚ ቡድን አባላት መንግስት ከፓርቲው ጋር ለተቆራኙ ሰዎች ብቻ ቆሟል ሲሉ ይወቅሳሉ::ቀደም ብሎ ያስፈልጋል የተባለው የእርዳታ ገንዘብ እና ትሕል በ3 እጥፍ ፍላጎቱ ጨምሯል:: የረሃቡ ችግር እየተስፋፋ ነው የሚሉት ምንጮች እንደሚናገሩት ከሆነ መግስት ለዜጎቹ መቆም ካልቻለ አደጋው የከፋ እንደሚሆን ጠቁመዋል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬