በኢደል አደሀ ( በአረፋ በዓል) ላይ ፊዳከ የሚል ቲሸርት ለብሳችሗል በሚል ክስ የተመሰረተባቸው 15 ወጣት ሙስሊሞች በነፃ እንዲሰናበቱ መደረጉ ተሰማ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በኢደል አደሀ ( በአረፋ በዓል) ላይ ፊዳከ የሚል ቲሸርት ለብሳችሗል በሚል ክስ የተመሰረተባቸው 15 ወጣት ሙስሊሞች በነፃ እንዲሰናበቱ መደረጉ ተሰማ

ፊዳከ የሚል ቲሸርት ለብሳችሗል ድምፃችን ይሰማ ብላችሗል በሚል አስገራሚ ክስ የተመሰረተባቸውና ላለፉት 3 ወራቶች ሙስሊም በመሆናቸው ብቻ እንደወንጀል ተቆጥሮ በወንበዴው መንግስት ሲንገላቱ የነበሩት የአዲስ አበባ ወጣቶች እነዚህ ናቸው
በነ አድናን ኑሩ አብደላ የክስ መዝገብ የተካተቱት 15 የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ባለፈው መስከረም 13/1/2008 በተመሰረተባቸው ሃሰተኛ ክስ ፊዳከ የሚል ቲሸርት ለብሳችሗል ፣ ድምፃችን ይሰማ አሏሁ አክበር ኮሚቴው ይፈታ ብላችሗል በሚል ተከሰው ፍርድ ቤት ቀርበው ላለፉት ከ3 ወራቶች በላይ ክርክር ሲያደርጉ ቆይተው በዛሬው እለት ያቀረቡት የመከላከያ ምስክር በቂ ነው በማለት የካንጋሮው ፍርድ ቤት በነፃ እንዲሰናበቱ ሲል ወስኗል