ወያኔ ፈሪ ነው::የጊዜ ጀግና እንጂ የሰው ጀግና ያሌለው ሙልጭ ያለ ፈሪ አገዛዝ ..
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
እንደ ወያኔ አይነት ውርጃ ፈሪ አገዛዝ ንጹሃንን ያልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎችን ይገላል – ያስራል::
#Ethiopia #EPRDF #Oromoprotests #MinilikSalsawi #Change #Freedom
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ወያኔ ፈሪ ነው::የጊዜ ጀግና እንጂ የሰው ጀግና ያሌለው ሙልጭ ያለ ፈሪ አገዛዝ .. ወንድ እና ጀግና እኮ ሰላምን እና ሰላማዊ ጥያቄን ያከብራል::በመሃል ክፍላተሃገራት የተነሳውን የተማሪዎች ንቅናቄ ተከትሎ የወያኔው አገዛዝ ከግድያ ጀምሮ እስከ እስር እና ዛቻ ድረስ ቀጥሎበታል:: ወያኔ ጀግኖችን ይፈራል ወያኔ እውነትን ይፈራል ስለሚፈራ ደግሞ በመሳሪያ ሃይል ስር ተደብቆ ምንም ያሌላቸውን ንጹሃንን ያጠቃል::ወያኔ ደፋር እና ጀግና ቢሆን እኮ አደባባይ የወጣን ያልታጠቀ ሕዝብ ላይ የጥይት ውርጅብኝ አያወርድም::በስለጠነ አለም ላይ ላይ በባዶ እጃቸው አደባባይ ወጥተው ጥያቄ የጠየቁ ይሁኑ በተባ ብእራቸው ተቃውሞ ያሰሙ ሕዝቦችን መግደልና ማሰር የአገዛዙን ፍርሃት እና ውርጃነት ወለል አድርጎ ያሳያል::
የግድያው እና ከተቃውሞ ሰልፎች ላይ የታፈሱት ሲገርመ በየቤቱ እና በየመንገዱ እየጠበቁ በማፍያ ስራ በተካኑ ደህንነቶች የፖለቲካ አመራሮችን እና አክቲቭስቶችን ማፈንን አጥብቀን እንቃወማለን::አገዛዙ አገር መምራት ስላልቻለ ስልጣኑን ለቆ ለሕዝብ ማስረከብ ሲገባው ሰላማዊ ዜጎችን እያሳደዱ ማሰር እና መግደል ነገ ከተጠያቂነት እንደማያስመልጥ በድጋሚ ለመናገር እፈልጋለሁ::የጊዜ ጉዳይ እንጂ እንኳን ሕዝባዊ መሰረት ያጣው ወያኔ አይደለም ሕዝብን አፍኖ ከአፍሪካ ግዙፍ ሰራዊት የገነባው ደርግ በሕዝብ ተጋድሎ በኢትዮጵያ ውስጥ መንኮታኮቱን መዘንጋት የለብንም::ስለዚህ የወያኔ አገዛዝም ተንኮታኩቶ ተረት ተረት የሚሆንበት የዘረፉት ንብረትም በሕዝባዊ መንግስት የሚወረስበት በስተርጅና የወያኔ ጉጅሌዎችም እስር ቤት የሚጃጁበት ከሃገር የወጥውም ፍርዱን የሚያገኝበት ጊዜ ቅርብ ነው:;ወያኔ የጊዜ ጀግና እንጂ የሰው ጀግና አይደለም:: መፍትሄው አንድ እና አንድ ብቻ ነው::በጋራ ተባብረን በመታገል ወያኔን መደምሰስ አራት ነጥብ #ምንሊክሳልሳዊ