በሸዋ በባሌ እና ወለጋ ክፍለሃገራት የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በሸዋ በባሌ እና ወለጋ ክፍለሃገራት የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል::
#Ethiopia #Oromoprotests #AddisAbabaMasterPlan #MinilikSalsawi #Oromo
በወለጋ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች የታጠቁ የወያኔ ወታደሮች ግቢያችንን ለቀው ይውጡልን ሲሉ ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን ጥያቄያቸውን ተሰሚነት ባለማግኘቱ ተጨማሪ ወታደሮች በግቢው ውስጥ ገብተው ተማሪዎችን ሲያባርሩ ሲደበድቡ እና ሲይዙ ተስተውሏል:: በርካታ ተማሪዎች ክፍኛ መጎዳታቸውን እና አንቡላንሶች ሲመላለሱ ነበር ተማሪዎች የዩንቨርስቲውን ግቢ በመልቀቅ ወደየቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ ይገኛሉ:: ተቃውሞ በሚካሄድባቸው አከባቢዎች ኦሮሚኛ ተናጋሪ ያልሆኑ እና ስለ አከባቢው ምንም አይነት እውቀቱ የሌላቸው ወታደሮች በየአከባቢው እየሰፈሩ ይገኛሉ::
እንዲሁም በሰሜን ሸዋ ሂዳቡ አቦቴ ከተማ ተማሪዎች ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ::በዚሁ ሰሜን ሸዋ ቱሉ ሚልኪ የወያኔ ወታደሮች የእርዳታ ድርጅቶችን መኪና በመጠቀም ቤት ክለቤት እየዞሩ ወጣቱ በማፈስ ላይ ይገኛሉ::በተጨማሪም በባሌ አጋርፋ ዳግም ተቃውሞ ተቀስቅሷል::በሰበታ መምሕር እና ደራሲ የሆነው ለሚ ግርማ በወያኔ ደህንነቶች የታፈነ ሲሆን ያለበት ቦታ እንደማይታወቅ ቤተሰቦቹ ተናግረዋል::ተቃውሞውን ወያኔ በቁጥጥር ስር አአዋልኩት ቢልም ከቀድሞው በበለጠ ሁኔታ ተፋፍሞ ቀጥሏል::#ምንሊክሳልሳዊ
