የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ራዲዮና ቴሌቭዥን ድረገፅ በቦረንቲቻ HACK ተደረገ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ቦረንቲቻ የተባለው የኦሮሞ ሕዝብ በደል እና እስር የሚቃወመው የለውጥ አራማጅ ቡድን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ራዲዮና ቴሌቭዥን ድረገፅን መጥለፉን እና የሕዝብ ጥያቄዎችን በድህረገጹ ላይ መለጠፉን አስታውቋል::

በኦሮሞ ተማሪዎች እና ገበሬዎች የሚደረገው ተቃውሞ በተቀጣጠለበት በዚህ ውቅት ላይ ከውጪ የሚገኘው የዲያስፖራ ሃይል የሆነው በሳይበር በኩል ቦረንቲቻ የተባለው ቡድን የወያኔ አገዛዝን ድረገጾችን ሃክ በማድረግ ለኦሮሞ ትግል ያለውን አጋርነት በማረጋገጥ ላይ ሲገኝ በጠለፋቸው ድህረገጾች ላይ የሕዝብን ጥያቄዎች በመጻፍ ተቃውሞን እያሰማ ይገኛል::ቦረንቲቻ የሃኪንግ ቦድን ባለፉት ሳምንታት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና የሃገር መከላከያ ሚንስቴር ድረገፆች በተከታታይ ቀናት ጠልፏቸው ነበር::

Embedded image permalink