እንኳን እርሳቸው፣ ነባሮቹ የብአዴን መሪዎች እነበረከትና አዲሱ እንኳ ከኤርትራና ሱዳን ጉዳይ የተገለሉ ነበሩ:: ያሬድ ጥበቡ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሱዳን ኢትዮጵያን ወሰን ጉዳይ በታላቅ ጥንቃቄ ቢያዩትና፣ ምክርቤቱ ውስጥ የሰጡት አይነት የኢትዮጵያን አራሾች በድንበር ገፊነትና፣ በሽፍትነት የመሳል ምስክርነት ቢቆጠቡ ተመራጭ ነው ። አለመግባባቱ ወደፊት ወደአለምአቀፍ አርቢትሬሽን ቢላክ ይህ ቪዲዮ የሱዳኖችን የይገባኛል ጥያቄ የሚያጠናክርና ኢትዮጵያን የሚጎዳ በመሆኑ፣ ከዚህ መሰል ምስክርነት ቢቆጠቡ ተገቢ ነው ።
በሁለተኛ ደረጃ፣ አቶ ኃይለማርያም ለኢህአዴግ መጤ መሆናቸውን መረዳት አለባቸው ። እንኳን እርሳቸው፣ ነባሮቹ የብአዴን መሪዎች እነበረከትና አዲሱ እንኳ ከኤርትራና ሱዳን ጉዳይ የተገለሉ ነበሩ። በወያኔ ፖሊትቢሮ ብቻ የተያዘ የውስጥ ጉዳይ ነበር ። በወያኔ 40ኛ አመት በአል ላይ መቀሌ ላይ ንግግር ያደረገው ሱዳናዊ፣ ” እኔም ወያኔ ነኝ” ብሎ ከፈከረ በኋላ፣ መለሰ ለመጨረሻው ከደርግ ጋር ድርድር ወደ ለንደን ከማቅናቱ በፊት፣ ካርቱም ላይ ፕሬዚደንቱ ቢሮ መሬት ላይ ፈርሸው ስላደረጓቸው ውይይቶች የነበረውን ትዝታ አካፍሏል ።
በዚያ ወቅት፣ የጋራ ጠላታቸው የሆነውን የአማራ ህዝብ ለማዳከም መለስ የገባው ቃል ሊኖር ይችላል ። ምናልባትም አዲሱን መንግስት በማቋቋም ስም ወያኔ ከሱዳን የበላው መሃያ ሊኖርም ይችላል። ብዙ ያልተፈተሹና የማናውቃቸው ጉዳዮች ስላሉ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያለኝ ምክር፣ እጃቸውን ከዚህ ጉዳይ ውስጥ ማውጣትና፣ የወሰን ድርድር ለማድረግ የሚያሰገድድ ሁኔታ ፈፅሞ ባለመኖሩ፣ ጉዳዩ ባለበት እንዲቀጥል መተው የተሻለ ነው ብዬ አስባለሁ ። ሃገራቸውን የሚጎዳ ነገር ውስጥ እጃቸውን ባያስገቡ ይመረጣል ።