አጋንንት እና ሽፍታ የተባለ ሕዝብ ነጻነቱን ያወጀ`ለት ወዮልህ !!!እውነታው ይህ ነው !!
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
አጋንንት እና ሽፍታ የተባለ ሕዝብ ነጻነቱን ያወጀ`ለት ወዮልህ !!!እውነታው ይህ ነው !!
#Ethiopia #Oromoprotests #Gonder #Ethiopiaprotests #EPRDF
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ደርግ ወንበዴ ሽፍታ የናት ጡት ነካሽ ወዘተ ሲላቸው የነበሩ የዛኔ (ነጻ አውጪ ነን)ብለው በምእራባውያን እርዳታ የቀዝቃዛው ጦርነት በጅቷቸው ለአራት ኪሎ ቤተመንግስት የበቁት ወያኔ እና ቡችሎቹ ትላንትና በፈለፈሉት እና የስልጣን ጥማቸው ታውቆ አሻንጉሊት በሆኑ እንደ ሃይለማርያም ባሉ በራሳቸው በማይተማመኑ ሰዎች የኢትዮጵያን ሕዝብ ሽፍታ ብለው ያሰድባሉ:;አንድ መንግስት ለሕዝቡ ከበሬታ ካሌለው እድሜው ዓጭር መሆኑ ራሱ ወያኔ በራሱ እያየው ነው::ትላንትና መንገድ እየመራ አዲስ አበባ ቤተመንግስት ያደረሳቸውን የጎንደር ሕዝብ ሽፍታ ወንበዴ ለማለት የደፈሩበት ምክንያት እስካሁን ማብርሪያ አልሰጡም::መሬትህ ተወስዷል እንካ እየተባለ የተቆሰቆሰው የሱዳን መንግስት እንኳን የጎንደርን ሕዝብ ሽፍታ ብሎ አልተዳፈረም::
ሕወሓት ከአማራው ክልል ሕዝብ ጋር ባትዋሃድ ኖሮ ለዚህ ስልጣን አትበቃም ነበር:: ለ15 አመታት ትግራይን እጻ አወጣለሁ ብሎ የሸፈተው ሕወሓት አንድም ድል ቀንቶት አያውቅም::በተከታታይ ሶስት አመታት ግን ከ1980 በኋላ በአማራው ገበሬ ታዝሎ ለስልጣን እንደበቃ ራሳቸው ሕወሓቶች በየካቲት 1983 ደርግን በማንኮታኮት መንገድ ላይ ባሉበት ወቅት የመሰከሩት ነው::ከአዲስ አበባ ከፍተኛ ተቋማት እና ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተመልምለው ለሕቡእ ስልጠና ወደ ጫካ ለወረዱ የአዲስ አበብ ተማሪዎች ቃል በቃል የአማራው ሕዝብ ደርግን ለመጣል ግንባር ቀደም ሚና እንደተጫወተ ሕወሓቶች መስክረዋል:: በተለይ ደሞ የጎንደር ሕዝብ::እነ ሓይለማርያም ደሳለኝ በማያውቁት መጥተው የተመከሩትን በሉ የተባሉትን እንደ ገደል ማሚቶ ያስተጋባሉ::
እነሃይለ ማርያም ደሳለኝ እና በስልጣን ውለታ ሕወሓት ያሰራቸው ቡችሎች ይህን ለነጻነቱ ለሃገሩ ዳር ድንበር እና ለመብቱ መስጥዋት የሆነን ሕዝብ ሽፍታ ብለው መሳደባቸው በሉ ከሚለው አካል የተሰጣቸው መመሪያ ቢሆንም በራሳቸው አለመተማመናቸው ወንጀለኝኦች እንደሆኑ ልንነግራቸው ይገባል::የኦሮሞን ሕዝብ ጋኔን አጋንንት የአማራውን ሕዝብ ሽፍታ ወንበዴ እየተባለ ነገ ደሞ የልጥላው ሕዝብ በተራው ተለጣፊ የስድብ ስሞን እንደሚሰጡት የተረጋገጠ ነው::የሕወሓት የገደል ማሚቱ ሃይለማርያም ደሳለኝ ዛሬ ሽፍታ ብሎ የሰደበው ሕዝብ እንደ ጌታቸው ረዳ ያሉ የጫት ትሎች ጋኔን አጋንንት ብለው የሰደቡት ታላቁ የኦሮሞ ሕዝብ በጋራ ሆነው የወያኔን ባለስልጣናት ከነተልላኪዎቻቸው በቅርቡ ለፍርድ እንደሚያቀርቡ ላረጋግጥላቸው እወዳለሁ::ማንም ከተጠያቂነት አያመልጥም::ሽፍታ የተባለ ሕዝብ ነጻነቱት ያወጀ`ለት ወዮልህ !!!እውነታው ይህ ነው !! #MinilikSalsawi
