የ “Ethio Telecom” ቅፈላዎች – ኧረ ወየው! የት ሄጄ ልደበቅ? -Yohanes Molla
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ዛሬ ከ8079 “Reewire ጥያቄዎች በመላክ ማራኪ ሽልማቶች የሚያሸንፉበት እድል ይሰጣል። ከReewire መልእክት መቀበል ከፈለጉ “እሺ” ብለው ለ8079 በነጻ ይላኩ። ኢትዮ ቴሌኮም” የሚል መልዕክት ተቀበልኩኝ። (አስተካክዬ በአማርኛ ፊደላት ገለበጥኩት እንጂ፥ የደረሰኝ መልእክት – “Reewire Tiyakewoch bemelak maraki shilmatoch yemiyashenifubet idel yyesetal. KeReewire melekt mekebel kefelegu Eshi Belew le8079 Benetsa Yilaku. Ethio Telecom. የሚል ነበር።
ነገሩን ከስሩ ልይዘው ፈልጌ “Eshi” ብዬ ስመልስ፥ “Congratulations! You have become a party to the Quiz! Take an active part in the Quiz answering questions from 8815 and win unique prizes including a brand new car!” የሚል መልስ ወዲያው ተከትሎ ደግሞ 3 አማራጮች ያሉት ጥያቄ መጣ። በአንድ ጥያቄ መልስ ስንት እንደሚቆረጥ ማወቅ ስለፈለግኩኝ፥ ጥያቄውን ሳላነበው “1”ን መርጬ ላኩኝ። 2 ብር ቆረጠ።
ከ1 ወር ከሃያ ቀን በፊት፥ አርብ ኖቬምበር 6 ቀን ደግሞ ከ8840 “ETT ጥያቄዎች በመመለስ ማራኪ ሽልማቶች የሚያሸንፍ እድል ይሰጣል። ከETT መልእክት እንዲያገኙ ከፈለጉ “እሺ” ብለው ለ8840 በነጻ ይላኩ። ኢትዮ ቴሌኮም” የሚል መልእክት ተቀብዬ ነበር። (ያም መልእክት አስተካክዬ ሳልገለብጠው በፊት “ETT tiyakewoch bememels maraki shilematoch yemyashenef edil yisetal. keETT melekt endiyagegnu kefelegu ESHI belew le 8840 benetsa yilaku. Ethio Telecom” ነበር የሚለው።)
ያው የወሬ ጉጉቴ ያኔም “ESHI” የሚለውን መልስ አስልኮኝ “እንኳን ደህና መጡ! ጥያቄዎች ይመልሱና ለሽልማቱ ይጠጉ! >100,000 ብር ሁሌ እሁድ፣ >500,000 ብር ታላቅ ሽልማት የመጀመሪያ ጥያቄ እየመጣ ነው። 5ብር/መልስ 50 ነጥብ ያሸንፉ።” ብሎ ጥያቄውን ይቀጥላል። (ዋናው መልስ እንዲህ ነበር: “Enkuan dehena metu! Tiyaqewoch yimelesuna leshilematu yitegu! >100,000br hule ehud >500,000br talaq shilemat Yemejemeriya tiyaqe eyemeta nw… 5br/meles 50ntb yashenefu”) ያኔም መልስ ልኬ ስሞክረው፥ 5 ብሬን እምሽክ አደረገው።
(ነገሩን ደንበኞች በፈቃዳቸው ተጫውተው የሚሸለሙበት እንደሆነ ብናስብ እንኳን፥ እስከ ዛሬ ለሽፋን እንኳን፥ ምንም ዓይነት ሰው “ይሄን ተጫውቶ ተሸለመ” ሲባል ሰምተን አናውቅም። (ቀድሞ የነበረው፥ በየሳምንቱ እሁድ >100,000 ብር ማለቱን ልብ ይሏል።)
በግልጽ እንደሚታየው ከሁለቱም ቅፈላዎች መልእክት ስር “Ethio Telecom” የሚለው ስም በጉልህ ሰፍሯል። ለቅፈላ መርሀ ግብሩ አዲስ ባንሆንም፥ በዚህ ደረጃ በወረደ አቀፋፈል አንድ ትልቅ መስሪያ ቤትን ማሰብ ያሳፍራል። እንግዲህ እንዲህና እንዲያ ሆነን፥ ተደርጎብን ነው “የሩብ ዓመት ትርፌ” ተብሎ በሚሊየኖች ሲዘከዘክልን ጆሯችንን ደቅነን ሰምተን የምናጨበጭበው። እንዲህና እንዲያ ሲሆን እያየን ነው፥ “ዓለም አቀፍ የአገልግሎት ጥራት ተሸላሚ” ሲባል፥ “ፓ” ብለን አፋችንን ከፍተን የምንቀረው።
ኧረ ወየው! የት ሄጄ ልደበቅ?