ነአምን ወጣ ገብረመድህን ገባ የወያኔ ካድሬዎች የሳምንቱ ትልቅ ግኝት


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


እኔ ወያኔ በማንኛውም የትግል ዘዴ ከስልጣን ቢወገድ ደስታዬ ነው! የግንቦት-7ቱ ኤርትራ ገብተው የመታገል ኣማራጩና ኣካሄዱ ግን ሊዋጥልኝ ኣልቻለም! ደምህትን‬ ኣይተው ከሆነ የሞላ ኣስገዶም ‪‎ደምሒት‬ ከሁኔታዎች ጋር አቋሙ እያቀያየረ ይምጣ እንጂ የወያኔዎች ድብቅ ዓላማ አንግቦ ነው ወደ ጫካ የወጣው!

 

የኤርትራው አምባገነን የዕድሜ ይፍታ ንግስናው ዘበኛ እንዲሆንና አንተ ዲቃላ ዓጋመ ነህ የሚሉት ኤርትራውያን ኣስሮ እንዲያሰቃይለት ወደ ኤርትራ እንዲገባ ፈቀደለት! ያኔ ለክፉ ግዜ ብላ የመለስ ወያኔ ያቋቆመችው ልኡክ(ሞላ) ደግሞ ባድሜ ለመስጠትም ውል ኣይኖረውም ኣይባልም! ያ ደግሞ ግንቦት-7 ይቀበሉታል የሚል እምነት የለኝም! ስለዚ ህወሓት ከምትመራው ሰርዊት ጋር ሆነህ ህወሓትን ማሸነፍ ኣይቻልም! https://encrypted-tbn2.gstatic.com/images?q=tbn:ANd9GcRuggmhgRQA02_HxWl8NsSmeWH5jrH0SH6oWN_bUTJa1PITJY8y

 

ሌላው ይቅርና ኣማካሪዎቻቸውም እነሱ መሆናቸው ነው የሚገርመው! የኤርትራ ቁጥር ሁለት መሪ የመከላከያ ሚንስተሩ ጀነራል ኤፍሬም ሰብሓት ባለቤቱ የኢሳያስ አፈወርቅ ልዩ ፀሓፊ ነች! እቺ ሴትዮ አበራሽ ነጋ ትብላለች የህወሓቱ የአቦይ ስብሓት ነጋ እህት ነች! ምን እደሚደረግና ማን ምን እንዳለ ጠንቅቃ ታውቃለች! ታድያ የኣውራምባው ካድሬ ኤርትራ ውስጥ ካለው የህወሓት ክንፍ ሰምቶ ነአምን ወጣ ኢሳያስን አስቀየመ ብሎ ቢፅፍ ምን ይደንቃል? ለዚህ ነው ኣማካሪዎቻቹም ህወሓት ናቸው የምለው!

 

ስለዚ የትግል ኣቅጣቻቹ ብታስተካክሉ የራሳቹና በተስፋ የሚደግፋቹ ኢትዮጵያዊ ጉልበትና ገንዘብ ባይባክን እንደ ኦነጎች ሙሉ በሙሉ አገር ውስጥ ያለውን ትግል በተቻላቹ ሁሉ ብትደግፉ እላለሁ:: === ከነቋሪው ===