በቦረና ዞን በሚዮ ወረዳ መንግስት በተፈጠረበት ስጋት ሰዎችን እየደበደበና እያሰረ መሆኑንና በገሪ ና በቦረና መካከል ግጭት ለመፍጠር በማሰብም አንድ የገሪ ሰው መግደሉም ታወቀ ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን በሚዮ ወረዳ ሂዲ ሎላ ከተማ የመንግስት ሃይሎች በአካባቢው ይነሳል ብለው የፈሩትን የህዝብ ተቃውሞ ከእንጭጩ ለመቅጨት በማሰብ ነዋሪዎችን ቤት ለቤት እየዞሩ ህዝቡን ለተቃውሞ እያዘጋጃችሁና እያነሳሳችሁ ነው በሚል ነዋሪዎችን እየደበደቡና እያሰሩ መሆኑን ምንጮቻችን ዘገቡ ።

እንደምንጮቻችን ዘገባ ለህልውናዬ አስፈላጊ ነው ብሎ ካሰበ ምንም ነገር ከመፈፀም ወደ ኃላ የማይለው ገዢው መንግስት : የህዝቡን የትግል ስሜትና መብትን የማስከበር እንቅስቃሴ አቅጣጫ ለማሳት በማሰብ በ ገሪ ና በቦረና መካከል ግጭት ለመፍጠር እድል ይፈጥራል በሚል አንድ ድንበር ጠባቂ ገሪን በሞየሌ ወረዳ መግደላቸው ታውቋል ።

በኦሮሚያ ክልል የተፋፋመው መብትን የማስከበር እንቅስቃሴ በቦረና ዞን እንዳይቀጣጠል መፍትሄው በ ቦረና ኦሮሞ ና በገሪ ኦሮሞ መካከል ግጭት በመፍጠር የህዝቡን አቅጣጫ ማስቀየር ነው የሚለውን እቅድ ነድፈው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ምንጮቻችን ዘግበዋል ።

በሚዮ ወረዳ ማህበተሰቡን እየበጠበጡ እየደበደቡ እና እያሰሩ ያሉት የመንግስት የካቢኔ አባላትና ሃላፊዎች ሲሆኑ እነሱም
1) ጀምበሬ አበራ (የሚዮ ወረዳ አስተዳደር )
2) አብዱብ ጉሮ ( በሚዮ ወረዳ የኦፒዲኦ የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ)
3) ዓብዱልዓዚዝ (የኦፒዲኦ የገጠር ክፍል የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ) መሆናቸው ታውቋል ።

በአካባቢው እስካሁን ድረስ ከሰላሳ በላይ ሰዎች የተያዙና ከሃምሳ ሰዎች በላይም መደብደባቸውን ምንጮቻችን ጠቅሰዋል ።

በተያያዘ ዜናም የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዛሬው እለትም ከባድ ተቃውሞ ማድረጋቸው ታውቋል ።

የዩኒቨርሲቲው አስተዳደሮች ተማሪዎችን እያስፈራሩና እርምጃ እየወሰዱ ባሉበት ሁኔታ ነው ተማሪዎቹ የዩኒቨርሲቲውን ህገወጥ እርምጃ ከምንም ባለመቁጠር በዛሬው እለትም ተቃውሞዋቸውን ያሰሙት : በተመሳሳይ ሁኔታ በሀረር ጭሮ ከተማ የሚገኙ ተማሪዎች ባለፈው ሳምንት የታሰሩ ተማሪዎች እስካልተፈቱ ድረስ አንማርም በማለት የትምህርት ቤቱን ቅጥር ግቢ ለቀው መውጣታቸው የታወቀ ሲሆን በሰሜን ሸዋም በቱሉ ሚልኪ ጃርሶ ወረዳ ነዋሪዎች ደማቅ ተቃውሞ ማሰማታቸው ታውቋል ።

source – ራዲዮ ዳንዲ ሃቃ