ፍኖተ ሰላምና ቡሬ ከተሞች በአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቅናቄ የትግል ጥሪ ወረቀቶች ተጥለቅልቀው አድረዋል።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።

በምዕራብ ጎጃም አስተዳደር ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ፍኖተ ሰላምና ቡሬ ከተሞች በአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቅናቄ የትግል ጥሪ ወረቀቶች ተጥለቅልቀው አድረዋል። የአማራን ህዝብ ለነፃነት ትግሉ የሚያነሳሱና ሌሎች የተቃውሞ ወረቀቶች ተበትነውና ተለጥፈው አድረዋል። በተለይ በአማራና በኦሮሚያ እየደረሰ ያለውን ፋሽስታዊ ጭፍጨፋና የድንበሩን መካለል የሚያወግዙ ፅሁፎች ይገኙበታል።



