በጊንጪ ትምህርት ቤቶች ዝግ ናቸው፤ የንግድ ቤቶች ለሣምንታት ከተዘጉ በኋላ እየተከፈቱ ነው – VOA


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Main roads of Wolliso in western Ethiopia are blocked off by protesters - 10 Dec 2015
ኦሮሚያ ክልል የሚካሄደው ተቃውሞ ሁለተኛ ወሩን ያዘ። የኦሮሞ ሕዝብ የዋና ከተማይቱን የአዲስ አበባን ወደ አካባቢዋ አዋሳኝ የክልሉ ግዛቶች መስፋፋት የሚቃወም ሲሆን ሌሎች ጥያቄዎችም አሉት። ከእነዚህም አንዱ መንግሥት ሥልጣን ከልክሎናል የሚል እንደሆነ ጠቅሳ የቪኦኤዋ ማርተ ፋን ደር ቮልፍ ተቃውሞው በኅዳር መግቢያ ከተጀመረባት ጊንጪ ከተማ ዘግባለች።

በጊንጪ ትምህርት ቤቶች ዝግ ናቸው፤ የንግድ ቤቶች ለሣምንታት ከተዘጉ በኋላ እየተከፈቱ ነው፡፡ ሆኖም ከአዲስ አበባ 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ትንሿ ከተማ ውጥረት ሰፍኖ ሰንብቷል። ፖሊሶች በዋናው ጎዳና ላይ ይዘዋወራሉ፤ ጋዜጠኛን የሚያነጋግሩ ሰዎች ማንነታቸው እንዳይገለፅ ይጠይቃሉ፡፡ አንዲት ለሁከቱ የዐይን እማኝ የነበረች የሻይ ቤት ሠራተኛ ንግድ ቤቱ ቢከፈትም በጊንጪ ግን አሁንም ውጥረት እንዳለ ተናግራለች፡፡ ዝርዝሩን ያዳምጡ → listen