የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ቅሬታ አሰሙ – VOA
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ባልደረቦች የሆኑ ከመቶ በላይ ረዳት መምህራን ከሁለት ዓመታት በፊት ለጠየቁት የሥራ ዕድገት መልስ እስካሁን እንዳልተሰጣቸው እየተናገሩ ነው፡፡ ቅሬታ አቅራቢዎቹ “ለከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ዕድገት እንዳንወዳደር ተደርገናል፤ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን የቤት ኪራይ አበልና ሌሎችም ጥቅማጥቅሞችን ተከልክለናል” ብለዋል፡፡
የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የሥርዓተ-ትምህርት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አብዱልቃድር ከድር ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “ረዳት መምህራኑ የትምህርት ደረጃ ዕድገት በውድድር እንዲሆን ሕግ ስለሚያዝ እንጂ መብታቸውን አልተከለከሉም” ብለዋል፡፡
የቤት ኪራይ አበል መከልከላቸውን አስመልክቶ መምህራኑ ላነሱት ጥያቄ ሲመልሱ “ማግኘት እንደማይችሉ በሕግ ስለተደነገገ ነው” ብለዋል፡፡ ለተጨማሪ የግርማይ ገብሩን ዘገባ ያዳምጡ → listen