በሰሜን ጎንደር የጭልጋ የቋራ እና የመተማ ሕዝብ እርቀ ሰላም ባለው ወያኔ ላይ ተቃውሞውን ቀጥሏል::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በሰሜን ጎንደር የጭልጋ የቋራ እና የመተማ ሕዝብ እርቀ ሰላም ባለው ወያኔ ላይ ተቃውሞውን ቀጥሏል::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Gonder‬ ‪#‎Ethiopiaprotests‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎EPRDF‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ወያኔ በሚከተለው የጎሳ ፖለቲካ በሕዝቦች መሃል ግጭትን እየፈጠረ እንደሆነ እና ታሪካዊ የኢትዮጵያ መሬቶች ለሱዳን ለመስጠት መስማማቱን በመቃወም የሚደረጉ ተቃውሞዎች የቀጠሉ ሲሆን ወያኔ ሕዝቡን ይቅርታ ለመጠየቅ በጭልጋ ወረዳና አይከል ከተማ በመተማና ቋራ ወረዳዎች እርቀ ሰላም በማለት ሕዝቡን በይቅርታ ስም ለማታለል ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለት የአከባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል::ሕዝቡን ታቦት አስወጥቶ እርቀ ሰላም እያለ ለማጭበርበር እየሞከረ ይገኛል::ሕዝቡ ነቅቻለሁ በቃኝ ብሏል::

እናንተ ሕዝቡን ለማረጋጋት የምትሞክሩት ሲጨንቃችሁ እና መግቢያ ስታጡ ነው እንጂ የሕዝብ ጉዳይ ሳስቧችሁ አይደለም ሕዝቡ ተረጋጋሁ መልስ አገኛለሁ ብሉ የተለመደ ኑሮውን ሲቀጥል እናንተ ደሞ ተንኮላችሁን ትቀጥላላችሁ አያት ቅድመአያቶቻችን ያስረከቡንን መሬት እና ታሪካችንን ለሱዳን ልትሰጡብን ነው አብሮ ተባብሮ ተከባብሮ ሲኖር የነበረ ሕዝብ ቅማንት ወልቃይት አማራ ብላቹ ከፋፍላችሁ ለማባላት እየሞከራችሁ ነው::ሰርጎ ገቦችን አምጥታችሁ ወንጀል በመፈጸም በሕዝብ መሃከል ደም መፋሰስ እንዲፈጠር ታደርጋላችሁ በማለት ሕዝቡ ንቅተናል ሲል ተናግሯል::

ወያኔ በሰሜን ጎንደር ያሰበው ያልተሳካለት ሲሆን ሕዝቡ በንቃት እየታገለው መሆኑ ታውቋል::በሰሜን ጎንደር በጭልጋ እና መተማ እንዲሁም ቋራ ወረዳዎች ተከስቶ ነበረዉን ግጭት በሰላማዊ መንገድ በእርቅ ስነ ስርአት ለመፍታት በተጠራ ስብሰባ ላይ የሃገር ሽማግሌዎችና የአካባቢዉ ነዋሪዎች ወያኔን ቁም ስቅሉን እያሳዩት ይገኛሉ::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi's photo.