ከአዲስ አበባው ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ መንግስት የወሰደውን እርምጃ በመቃወም የኢትዮዺያ ሙስሊሞች አንድነት ማህበር መግለጫ አወጣ ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)'s photo.

ከአዲስ አበባው ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ መንግስት የወሰደውን እርምጃ በመቃወም የኢትዮዺያ ሙስሊሞች አንድነት ማህበር መግለጫ አወጣ ።

በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ መቀመጫውን ያደረገው የኢትዮዺያ ሙስሊሞች አንድነት ማህበር ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ የኢህአዴግ መንግስት በዜጎች ላይ እየወሰደ ያለውን የኃይል እርምጃ በመቃወም መግለጫ ማውጣቱ ታወቀ

ማህበሩ በመግለጫው በሀገራችን ኢትዮዺያ የመብት ገፈፋ እንዲቆም፣ ዜጎች በሀገራቸው በነፃነትና በእኩልነት የሚኖሩባት ሀገር ትሆን ዘንድና የእምነት ነፃነት እንዲከበር ሙስሊሙ ኀብረተሰብ ላለፋት አራት አመታት ያደረገውን ትግልና የመንግስትን ፍፁም ኢፍትሃዊ እርምጃ አስታውሷል።

በአሁኑ ሰዓትም ገዢው መንግስት ማስተር ፕላን ብሎ ዜጎችን ከቀያቸው የሚያፈናቅልና ለባሰ ድህነት የሚዳርግ : በአንፃሩም ጥቂቶች የሚከብሩበት መርሃ ግብር መንደፋንና : ይህንን እኩይ ተግባር በሰላማዊ መንገድ በተቃወሙት ላይ የተወሰደውን ህገ ወጥ እርምጃ ጠቅሷል

ይህ እየተወሰደ ያለው አረመኔያዊ እርምጃ የማይቆም ከሆነ ሀገራችን ፈፅሞ ወደ ማትቋቋመው ችግር ውስጥ መግባቷ አይቀሬ መሆኑን አሳስቦም ለዚህ ችግር መፍትሄ ይሆናሉ ያላቸውን አራት ነጥቦች አስቀምጧል ።

የማህበሩን መግለጫ ሙሉ ቃል ከስር ተመልከቱት