በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን ህዝቡ ትግሉን አፋፍሞ ለመቀጠል እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ታወቀ ።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በደቡብ ኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን በሞያሌ ፣ ቡሌ ሆራ፣ ደሬ ፣ ያቤሎ ፣ ዱግደዳዋ ፣ ተልተሌ ፣ አሬሮና በሌሎችም ወረዳዎችና ቀበሌዎች የሚገኙ መምህራን ፣ ተማሪዎች፣ ገበሬዎችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ትግሉ የሚፈልገውን አስፈላጊውን መሰዋዕትነት በመክፈል እስከ መጨረሻው ለመጓዝ መቁረጣቸውንና እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ገለፁ ።
የኦሮሞ ህዝብ ሴት ወንዱ ወጣት አዛውንቱ ለነፃነቱ እየታገለ ባለበት ሁኔታ እጅን አጣጥፎ መቀመጥ ከጨቋኞች ጎን እንደመቆም ይቆጠራል ያሉት ነዋሪዎቹ :
የኦሮሞ ህዝብ ታግሎና ደሙን አፍሶ በሚያመጣው ነፃነት አንገታችንን ቀና አድርገን መራመድን አንመኝም በማለት በመላው ሃገሪቱ የሚገኘው ማህበረሰባችን ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ጎን ለጎን በመጓዝ ታሪክ ለመስራት መዘጋጀታቸውን ለሪፐርተራችን ገልፀዋል ።
የገዢው መንግስት ባለስልጣናት የህዝብን ቁጣ ለማብረድ በማሰብ ኀብረተሰቡን ጠርተው ለማነጋገር ሙከራ ቢያደርጉም : የወንዱን ፣ የሴቱን ፣ የወጣት ፣ አዛውንቱን ደም እያፈሰሳችሁ ከእናንተ ጋር የምናደርገው ምንም አይነት ስብሰባ የለም በማለት : ለአምባገነኖቹ እምቢተኝነቱን እያሳየ መሆኑንና በአካባቢው የሚገኙ መምህራን ተማሪዎች ከህብረተሰቡ ጋር እየተነጋገሩና ለቀጣዩ ትግል እራሳቸውን እያዘጋጁና እስትራቴጂ እየነደፉ መሆኑን ምንጮቻችን አያይዘው ጠቅሰዋል ።
የመንግስት ባለሰልጣናቱ አንዱ አካባቢ አልሳካ ሲላቸው ፣ ወደሌላው አካባቢ በመሄድና ስብሰባ በመጥራት ፣ ህብረተሰቡን ለማስፈራራት እየጣሩ ሲሆን የህዝቡን ጠንካራ አቋምና ወኔውን ሲመለከቱ ባለስልጣናቱ መደናገጣቸውን መርበድበዳቸውን ምንጮቻችን አያይዘው ገልፀዋል ።
እንደ ምንጮቻችን ዘገባ
በቦረና ዞን በተልተሌ ወረዳ ፣ በሆርባቴ ፣ በመርመሮ ፣ በዲቤ ገያ ፣ እና በሌሎች ቀበሌዎች የሚገኙ ነዋሪዎችም የተማሪዎቻችን ደም በከንቱ ፈሶ አይቀርም የተማሪዎቻችንን ደም ያፈሰሱትን እስከ መጨረሻው እንታገላቸዋል እንፋረዳቸዋለን ማለታቸውን እንዲሁም በያቤሎ ፣ በሞያሌና በሜጋና በአሬሮ ያሉ ተማሪዎችና ገበሬዎች ተቃውሞውን አጠናክረው ለመቀጠል ዝግጅታቸውን እንደጨረሱ መረጃዎች ደርሶናል ።
ባለፋት ሳምንታት በቦረና ዞን በሂዲ ዶላ ወረዳ የአንደኛ ደረጃና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሆ ብለው በመውጣት ማስተር ፕላኑን መቃወማቸው የሚታወስ ሲሆን የት/ ቤቱ አሰተዳደር አቶ ልደቱ ደረጄ የሚባል ግለሰብ ይህን እንቅስቃሴ የመራኸው አንተ ነህ በሚል ከስራው መታገዱ ምንጮቻችን ዘግበዋል።
ይህን የሂድ ዶላ እንቅስቃሴ ተከትሎም : በቦረና ውስጥ እየተቀጣጠለ ያለው እንቅስቃሴ መንግስትን ያስደነገጠ ሲሆን :
በአሁኑ ሰአት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በዚህ ጨቋኝና አምባገነን ስርዓት የተማረረ በመሆኑ ይህን ስርአት ለመገርሰስ በቆራጥነትና በወኔ መነሳታቸውን ለምንጮቻችን ገልፀዋል
የአካባቢ ነዋሪዎች ለምንጮቻችን እንደገለፁት : ኦሮሚያ የተለያዩ ብሄር ብሔረሰቦች የሚኖሩባት ክልል መሆኗን ገልፀው ይህ እንቅስቃሴ የትኛውንም ብሄርና ማህበረሰብ የሚያሰጋ እንደልሆነና ምንም አይነት ፍርሀትና ስጋት ሊኖር እንደማይገባ አሳስበው
ጥያቄው መብትን የማስከበር ፣ ጥያቄና ሰላማዊ በመሆኑ ከህዝቡ ጎን በመቆም ትግሉን ሊቀላቀሉና ሊያግዙ ይገባል ብለዋል ።
በዚሁ በቦረና ዞን ቀደም ብሎ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች እንዲሁም የዱግደዳዋ ወረዳ ነዋሪዎች ማስተር ፕላኑን በመቃወም ከባድ ተቃውሞ ማድረጋቸው ይታወሳል ።
በስተመጨረሻ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች: መንግስት በዚህ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ አውግዘው የመንግስት ህገወጥ እርምጃ ህዝቡን ሰላማዊነቱን ጠብቆ እንዳይጓዝ እንዳያደርገው አሳስበዋል