ለታህሳስ 17 ቀን በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠርቷል


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የሰማያዊ ፓርቲ እና የአራት ደርጅቶች ስብስበ የሆነው መድረክ በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተዋል። ቀደም ሲል ኦፌኮ በአዳማና በለሌች የኦሮሚያ ቦታዎች ሰልፍ ጠርቶ እንደነበረና በባላስልጣናት ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ እውቅና እንደተነፈገ ይታወቃል።

ይህ የአሁኑ ሰልፍ ፣ በመድረክ ያሉትን እና ሰማያዊን ጨመሮ አምስት ደርጅቶች በጋራ የጠሩት ሰልፍ ሲሆን፣ የሚደረገዉን በአዲስ አበባ ነው።

ኦፈኮ የጠራው ሰልፍ ማስተር ፕላኑን በመቃወም የነበረ ሲሆን፣ የአሁኑ ሰልፍ ግን በማስተር ፕላኑ ዙሪያ ሳይሆን፣ ማስተር ፕላኑን በተቃወሙ ዜጎች ላይ የደረሰውን ግድያ የሚያወግዝ፣ ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት የታቀደዉን ለመቃወም፣ በሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ላይ እየተወሰደ ያለው እፈና እና እርምጃዎቸ እንዲቆሙ ለመጠየቅ ነው።

ሰልፍ መነሻውን ፒያሳ ራስ መኮንን ድልድይ ሆኖ፣ በቸርቺል ጎዳና አድርጎ መዳረሻው ቀድሞ ድላችን ሃዉልት አሁን ደግሞ ኢትዮ-ኩባ አደባባይ (ጥር አንበሳ አካባቢ) ነው የሚሆነው።

ሰልፉን በተመለከተ በሕጉ መሰረት ፓርቲዎች ማሳወቅ ብቻ እንደሚጠበቅባቸው ይታወቃል። የኢሕአደእግ ባለስልጣናትም ዜጎች ሰላማዊ በሆነ መንገድ ድምጻቸው ማሰማት መብት እንዳላቸው በተደጋጋሚ ሲናገሩ ተሰምተዋል።

ሆኖም ህዝብን ማስቆጣት ሱሱ የሆነው ኢሕአደእግ ፣ ሕግ መንግስቱን አክብረው፣ ዜጎች በሰላማዊ መንገድ ድምጻቸውን የማሰማት መብታቸውን በድጋሚ ይረግጣል የሚል ስጋት አለ።