ሕወሓት ራሱ በፈጠረው የጎሳ ፖለቲካ እሳት ራሱ ይቃጠላል::ሕወሓት ተረት ተረት የሚሆንበት ቀን ደርሷል:: ‪


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ሕወሓት ራሱ በፈጠረው የጎሳ ፖለቲካ እሳት ራሱ ይቃጠላል::ሕወሓት ተረት ተረት የሚሆንበት ቀን ደርሷል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎TPLF‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Unity‬

Minilik Salsawi – የኢትዮጵያን ሕዝብ በጎሳ እና በጎጥ ከፋፍሎ ለመግዛት የሞከረው ሕወሓት በተደጋጋሚ የሕዝቡ አንድነት እሳት እየሆነበት መጥቷል::ለስልጣኑ መስረዘሚያ የተለያዩ መርዘኛ የግጭት ስልቶችን በመጠቀም ሕዝቡን ከፋፍሎ አናቁሮ እና አጋድሎ ሌላው ሲባላ ወያኔ ሃገርን ሲበዘብዝ እና ሲመዘብር 25 አመታት ሊያስቆጥር ነው::ይህ መርገምት ከይሲ የማፊያ ቡድን ዘላለም አለሙን እያባላ እና እየበዘበዘ ለመኖር ቢያልምም ሕዝቡ ከሱ ቀድሞ በመንቃት ወደ አደባባይ ወጥቶ በቃኸኝ እያለው ይገኛል::

ኦሮሞ ከአማራ አማርን ከትግሬ አንዱን ከአንዱ ለማናከስ የዘየደው ዘዴ እሳት ሆኖ እየለበለበው የሚገኘው ራሱ የጎሳ ፈጣሪውን ሕወሓትን መሆኑ በገሃድ እያየነው ነው::ራሱ የለኮሰው እሳት ራሱን እና ጭፍሮቹን አቃጥሎ ሊያጠፋቸው እንደ ሰደድ እየተመመ ነው::ወያኔ የሚባል የማፊያ ቡድን ወደ ተረት ተረት ሊቀየር የቀረው ጊዜ እጅግ ትንሽ ነው::ባለ ረጃጅም እጆቹ ዘራፊው የማፊያ ቡድን ወያኔ እጆቹ አጥረው መደበቂያው ስብሰባ ከሆነ ሰነባብቷል::በአሁኑ ዘመን ሃገርን በዝብዞ ሕዝብን በድሎ እና ገድሎ ሸሽቼ እደበቃለሁ በሰላም እኖራለሁ ማለት ዘበት ነው::እያንዳንዱ የሕወሓት አባል ከየገባበት ጉድጓድ ተጎትቶ እንደ ሳዳም እና ጋዳፊ የአምባገነኖች እና አሽከሮቻቸው እጣ ይደርሰዋል::

የጎሳ ፈጣሪ የሆነው ሕወሓት በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን የደረሰበትን መደናገጥ ማየት በቂ ነው::ከውስጥ እስከ ውጪው ሃገር ኢትዮጵያውያን በጋራ ድምጻቸውን ማሰማታቸው ጎሳ ወይም ጎጥ ዘር ወይም ብሄር ሳይለያቸው የፖለቲካ አመለካከት ሳያግዳቸው ለተገደለው ለታሰረው ለተራበው ወገን በጋራ በአንድነት መቆማቸውን የተመለከተው ወታኔ በራሱ ስርጎ ገቦች ጨለማን ለብሶ ቢሞክርም አልተሳካለትም ::ወንጀለኛ ማነው ገዳይ ማነው ሲባል ጣቶች ሁሉ የሚጠቁሙት ወደ ሕወሓት ነው::ሕዝቡ በአንድነት የጋራ ጠላቴ ሕወሓት ነው ብሏል::የጎሳ ፖለቲካው ለሃገሪቱ ፖለቲካም ይሁን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የሌለው ዜጎች በሃገራቸው ተዘዋውረው መስራት እንዳይችሉ ስለሚያደርግ የመኖር ሕልውናን የሚፈታተን ዝጥጎች ረዥም አመታቶች ከኖሩበት ሃብት ንብረት ካፈሩበት ቀየ እንዲፈናቀሉ የሚያደርግ የወያኔ እኩይ ፖሊሲ ስለሆነ ይህንን እኩይ ፖሊሲ ለማጥፋት ፈጣሪውን ወያኔን ማጥፋት ግድ ስለሚል ሕወሓትን ከስሩ ነቅሎ በማጥፋት ራሳችንን ነጻ ማውጣት የእያንዳንዳችን ታሪካዊ ግዴታ ነው::ሕወሓት ራሱ በፈጠረው የጎሳ ፖለቲካ እሳት ራሱ ይቃጠላል::ሕወሓት ተረት ተረት የሚሆንበት ቀን ደርሷል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬