የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም የተጀመረው ተቃውሞ ተፋፍሞ ቀጥሏል


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስተማሪወችም መንግስት በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖችና ወረዳዎች የፈፀማቸውን ግድያዎች በምልክት መቃወማቸው ታወቀ ።

በትላንትናው እለት መንግስት አዳአ በርጋ ሙገር ከተማ በወሰደው እርምጀሰ ከሐያ ሰዎች በላይ መግደሉንና ብዛት ያላቸውንም ማቁሰሉን : ተጎጂዎችም በኢንጪኔ ሆስፒታል እንደሚገኙ ታውቋል። በዛሬው እለት በቀለም ወለጋ ዞን አምፊሌ ወረዳ ሸበል ከተማም ተቃውሞ መደረጉ ታውቋል ።

መንግስት ተቃውሞ በአዲስ አበባ እንዳይቀሰቀስ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ኬላ ላይ ፍተሻውን ቢያጠናክርም ፣ ቤት ለቤት ፍተሻ ቢያደርግም ይህን ሁሉ አልፎ በዛሬው እለት ተቃውሞው በስድስት ኪሎ መፈንዳቱ ታውቋል ።ሁለት ሴት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ታፍነው በመወሰዳቸው እና የዩኒቨርሲቲው ዲንም ተማሪዎቹ የት እንደተወሰዱ በተማሪዎች ሲጠየቁ የማውቀው ነገር የለም በማለታቸው ነው ተቃውሞው የተቀሰቀሰው ።

ከዚህ በተጨማሪም ከሀገር ውጪ በተለያዩ ሀገራት በኢንዶኖዢያ በዱባይ በበርሊን የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆች መንግስት እየሰራ ያለውን ህገ ወጥ ተግባር በመቃወም ሰልፍ መውጣታቸው ምንጮቻችን ከስፍራው ዘግበዋል።

በመከተል ሙከረማ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆ መንግስት እየወሰ ያለውን ህ ወጥ በመቃወም በዛሬው ተቃውሞአቸውን በምልክት መግለፃቸው ተሰማ

RDH