የዘር ፖለቲካ መዘዝ – ግርማ ካሳ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የዘር ፖለቲካ መዘዝ – ግርማ ካሳ

የአሜሪካን ዽምጽ ራዲዮ ዘገባ አደመጥኩ። ከ50 በላይ የሚሆኑ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ነጋዴዎች እንደተዘረፉና ጥቃት እንደደረሰባቸው ነው ዘገባው የሚገልጸው።በጣም አዝኛለሁ። ዜጎች ከዚህ ወይም ከዚያ ብሄረሰብ በመሆናቸው ብቻ ጥቃት ሲፈጸምባቸው መሰማቱ እንደ አገር አሁን ሕወሃት/ኢሕአዴግ እያራመደው ያለው የዘር ፖለቲክ ወደ መጥፎ አቅጣጫ እየወሰደን መሆኑን አመላካች ነው። ሰዉን ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ አማራ ..እይሉ ከፋፈሉት በቃ ዘር እየነጠልን መተያየት ጀመርን።

ሪፖርቱ እነዚህ ወገኖች በመንግስት ባለስልጣናት እንደተጎበኙ ይዘግባል። ም/ጠቅላይ ሚኒስተሩ አቶ ደመቀ መኮንን፣ የአማራው ክልል አስተዳዳሪ አቶ ደጉ አንዳርጋቸው፣ የቀድሞ የብአዴንን አመራር አቶ አዲሱ ለገሰን ያካተተ የአመራር ቡድን ነው እነዚህ ወገኖች የጎበኘው። ባለስልጣናቱ “መንግስት የሚያስፈልጋችሁን እርዳታ ያደርግላቹሃል፡ እናንተ ግን በርትታችሁ ለልማት ስሩ” ብለዋቸዋል።

በመንግስት ስልጣን ላይ ያሉ ከቤተ መንግስታቸው ወርደው፣ ከተገፋዉን፣ ከተበደለዉ፣ በግፍ ከሚፈናቀለዉና በዘሩ ወይንም በብሄረሰቡ ምክንያት ከሚጠቃዉ ጎን በዚህ ወቅት መቆማቸው ያስመሰግናቸዋል።

ሆኖም ኢትዮጵያ ዉስጥ እንክባካቤ ሊደረግላቸው፣ ሊጠየቁ አይዟችሁ ሊባሉ የሚገባቸው የትግራይ ተወላጆች ብቻ ግን አይደሉም። በጉሩ ፈርዳ ደቡብ ክልል በአቶ ሽፈራው ሽጉጤ ትእዛዝ ፣ አማርኛ ተናጋሪዎች የሆኑ እጅግ በጣም ብዙ ዜጎች በግፍና በጭካኔ አገራችሁ አይደለም ተብለው ተፈናቅለዋል። በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ፣ በኦሮሚያ በአምቦ አካባቢም “አገራችሁ አይደለም” በሚል ብዙዎች በአገራቸው እንደ እንግዳና መጤ ታይተው የዘር ማጽዳት ወንጀል ተፈጽሞናቸው። የሞቱም የቆሰሉም አሉ።

እነዚህ ሁሉ ግፎች ሲፈጸሙ ግን፣ አሁን እንደተደረገው የተፈናቀሉትን የጎበኘም፣ ያጽናናም፣ ያበረታታም፣ ድጋፍ ይደረግላቹሃል ያለም ባለስልጣን አልነበረም። እንኳን ያሉበት ቦታ ሄደው ሊጎበኟቸውና ሊቆረቁሩላቸው ቀርቶ፣ አዲስ አበባ መጥተው ብሶት ሲያሰሙ እንኳን ጆሮ የሰጣቸው የለም።

ጥቃት ወደደረሰባቸው የትግራይ ተወላጆች ተመልሼ አንድ ነገር ልበል። የትግራይ ሕዝብ ከጎንደር ሕዝብ ጋር የተዋለደ፣ ለዘመናት አብሮ የኖረ ህዝብ ነው። እንደዉም ስልጣን ላይ ያሉት፣ ትላንትና የመጡት፣ ጥቂት ሕወሃቶች፣ በሚፍጽሙት ግፍ፣ በጅምላ የትግራይ ልጆችን ሁሉ ተጠያቂ ማድረግ የለብንም። ይሄ ትልቅ ስህተትና በራሱ ዘረኝነት በሽታ ነው። ራሳችንን ከጥላቻ መጠበቅ መቻል አለብን። የሕወሃት ዘረኛ ፖለቲክ ለዘመናት አብሮን የኖረን፣ የተዋለደ ህዝብ እንዲጠላላ ማድረግ የለበትም።

እነዚህ የትግራይ ወገኖቻችን፣ ጥቃት በደረሰባቸው በመተማ አካባቢ፣ ከአንድ መቶ አመት በፊት የተደረገውን የሆነን አንድ ታሪክ አንቼ አቆማለሁ። ጅግናው አጼ ዮሐነስ ኢትዮጵያን፣ ጎንደርን ከደርቡሾች ለመከላከል፣ በመተማ ሰማእት ሆነው አልፈዋል። መተማ ለኢትዮጵያ አንድነት ደማቸውን ያፈሰሱት የ እኝህ ታላቅ የተንቤን ሰው አገር ናት።

የአሜሪካን ድምጽ ዘገባ ለማዳመጥ ወደዚህ ይሂዱ

http://www.mereja.com/amharic/477392

ከጉሩ ፈርዳ፣ ከኦሮሚያ..አገራችሁ አኡደለም ተብለው በጭካኔ ከተፈናቀሉ፣ የሚቆምላቸው፣ የሚደርስላቸው ካጡ በሺሆች ከሚቆጠሩ አማርኛ ተናጋሪዎች በጥቂቲ