አዲስ አበቤዎች ካልደፈረሰ አይጠራም::ፈሪውን ወያኔን ገፍትሮ ለመጣል አፋፍ ላይ ስለሆንን እንግፋው:: (ምንሊክ ሳልሳዊ)
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
አዲስ አበቤዎች ካልደፈረሰ አይጠራም::ፈሪውን ወያኔን ገፍትሮ ለመጣል አፋፍ ላይ ስለሆንን እንግፋው::
#Ethiopia #OromoProtests #AddisAbabaMasterplan #Miniliksalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ወያኔ እኔ ካሌለው የሃገር አንድነት ይፈርሳል የሚል አጉል የማይሆን ዲስኩር እያሰማ ይገኛል:: የትኛውን አንድነት ነው ወያኔ የገነባው?ከደርግ የወረሳት ኢትዮጵያን እኮ እንዳልነበረች እየገጣጠባት ነው::በጎሳ ፖለቲካ ሃገርን እያተራመሰ ያለው ወያኔ እንጂ ሕዝቡ አይደለም ሕዝቡ አብሮ የኖረ የተዋለደ የተጋባ ባህሉ እና ፍቅሩ ያስተሳሰረው ለኢትዮጵያዊነቱ ቀናእ የሆነ ከአያት ቅድመ አያቱ ጀምሮ ስለ ሃገሩ የሚቆረቆር መሆኑ ማንም አይክደውም::ይህን ሕዝብ ይለያያል ማለት የጥቂት ስልጣን ጥመኞች ምኞት እንጂ የብዙሃን ነጻነት ናፋቂዎች ምኞት አይደለም::ሕወሓት ኤርትራን ከማስገንጠል ጀምሮ በጎሳ የተሸነሸነች አገር እና አፈናቃይ ካድሬዎች ፈጣሪ የሆነ አሸባሪ ድርጅት ነው::ይህን ከይሲ አስተሳሰብ ይዞ ያለው ወያኔ ከተደመሰሰ አንድነት አደፍራሽ የጎሳ ግኝት ፈጣሪ እና ከፍፋይ ሕዝብ አፈናቃይ ካድሬዎችን ስለሚደመሰሱ ሃገር ሰላም ትሆናለች::
ለኢትዮጵያ እና ሕዝቧ ዋና አስፈላጊ ጉዳይ የሕወሓት መደምሰስ ብቻ ነው:;የሃገር እና ሕዝብ ጠላት አንድ እና አንድ ሕወሓት ነው::በማናቸውም የኢትዮጵያ ክልል ብንመለከት የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥርሱን የነከሰው በሕወሓት ላይ ነው::ጨለማ ለብሶ በሕዝብ ላይ ጥቁር ሽብር የሚያካሂደው ሕወሓት ነው::የሕወሓት እኩይ ተግባር ተዘርዝሮ የማያአልቅ አሸባሪ ዘራፊ እና ገዳይ ቡድን ስለሆነ ሊወገድ ይገባል::ጀግናው የኦሮሞ ሕዝብ ደግሞ ላለፉት 25 አመታት ዝምታን መርጦ ባሁን ወቅት ዝምታውን ሰብሬል:: ከስሩ ከጉያው የተመለመሉ ካድሬ ልጆቹ ሳይቀሩ ስለመብታቸው እና ስለ ነጻነታቸው ሲሉ ሕሊናቸውን ለሕዝብ ማስገዛት የጀመሩ ሲሆን በሕወሓት ፈጠራ ታሪኮች እየተታለለ በአጉል የፖለቲካ ቅዳሴ እየቆረብ ያለው የኦሕዴድ ካድሬ ሁሉ አሁን ላይ ነቅቷል::በአማራው ክልልም እንዲሁ የሰሜን ጎንደር ሕዝብ እምቢ ለነጻነቴ ብሎ ጦሩን ሰብቆ ተያይዞ ዱር ቤቴ ብሎ ገብቶ ወያኔን እያስጨነቀ ነው::ይህ ሁሉ የሕዝብን ነጻነት እና መብት መደፍጠጥ ያመጣው የጭቁኖች ብሶት ሲሆን ድሉም ቅርብ ነው:አዲስ አበቤዎች ካልደፈረሰ አይጠራም::ፈሪውን ወያኔን ገፍትሮ ለመጣል አፋፍ ላይ ስለሆንን እንግፋው::
=======================================================
“የኦሮሞ ወጣቶች እንቅስሴ በግልፅ የሚያሳየው በኦሮሞ ስም ስልጣን የወጣው ያልተመረጠና የኦሮሞ ወኪል እንዳልሆነ ነው!… አዲስ አበባ ከከበቧት የኦሮሞ መንደሮች ውጭ መኖር አትችልም!…የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ማሰማት አለባቸው! …በኢትዮጵያ አንድነት እንታገላለን የሚሉት ትልቅ ሀላፊነት አለባቸው! ለኦሮሞ መቆም አለባቸው!” አቶ ሌንጮ ለታ (በኢሳት)
=======================================================
