በጎንደር ክፍለሃገር የሰሜኑ ክፍል ውጥረቱ አይሏል::በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው:: (ምንሊክ ሳልሳዊ)
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በጎንደር ክፍለሃገር የሰሜኑ ክፍል ውጥረቱ አይሏል::በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው::
#Ethiopia #Oromoprotests #Gonder #EPRDF #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በጎንደር ክፍለሃገር የሰሜኑ ክፍል ባለፉት ሳምንታት ሞቅ ቀዝቀዝ ሲል የነበረ የወያኔ አገዛዝ እና የሕዝቡ ግጭት ወደ ለየለት መስመር መቀየሩን እና ሕዝቡም ቤትና ንብረቱን ጥሎ ዱር ቤቴ ማለት እንደጀመረ ታውቋል::የግዛት እና የማንነት ጥያቄ ፈንቅሎ ያስነሳው ሕዝብ የወያኔን አገዛዝ በቃን ከትከሻዬ ውረድልኝ ማለቱን ከአከባቢው የሚወጡ ዘገባዎች ይጠቁማሉ::ሕዝቡ በራሱ አነሳሽነት እና በአንድነት ብመሆን በወልቃይት ጠገዴ በመተማ ሸዲ ጭልጋ ቋራ እና ሸንፋ በዙሪያ ባሉ የድንበር አከባቢዎች በወያኔ ታጣቂዎች ላይ ጥቃት ማድረሱ ሲታወቅ የቅማንትን ሕዝብ ክለላ በማድረግ ትግሪኛ ተናጋሪ የሕወሓት ታጣቂዎች ሊያደርሱት የነበረ አደጋ ማክሸፉን ሕዝቡ እየተናገረ ይገኛል::
ይህንንን ግጭት አያይዞ ወያኔ የሱዳን ወታደሮችን ወደ ጎንደር ክፍለሃገር ድንበሩን ዘልቀው እንዲገቡ ያደረገ ሲሆን ለግዛቱ አንድነት የማይተኛው ጀግናው የጎንደር ሕዝብ እንዳጠቃቸው እና እንደማረካቸው ታውቋል::የተያዙትን ሱዳናዊ ወታደሮች ለማስለቀቅ የወያኔ ወታደሮች ጥቃት ቢሰነዝሩም እንዳልተሳካላቸው ተሰምቷል::ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአከባቢው የትራንስፖርት አገልግሎት እንደተቋረጠ ታውቋል:: በዳንሻ አካባቢ ከሳምንት በፊት ታጣቂ የመንግስት አካላት በአካባቢዉ ካሉ አማጺያንና ከተቃዋሚዎች ጋር እንዲዋጉ የተሰጣቸዉን ትእዛዝ አንቀበልም ማለታቸዉ ታዉቋል። ከአካባቢዉ ምንጮች ለመረዳት እንደተቻለዉ በመንግስት ደሞዝተኞች ዉስጥ ያሉት ታጣቂዎች “መንግስት ይመጣል፤ መንግስት ይሔዳል። እኛ ግን ከወንድሞቻችን ጋር አብረን መኖራችን ይቀጥላል። ደም የመቃባት ፍላጎት የለንም። መንግስት ከፈለገ ጦሩን አስፍሮ እራሱ ሊዋጋ ይገባል። መሳሪያችንን እንድናስረክብ ከተጠየቅን መሳሪያችንን እናስረክባለን!” ማለታቸዉ ታዉቋል።
በኦሮሚያ ክልል የሚደረጉ ተቃውሞዎች ዛሬም ቀጥለው የዋሉ ሲሆን በወለጋ በባሌ ቀጥለው ሲውሉ በአሰቦት የሚገኙ ነዋሪዎች ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ የሚወስደውን የባቡር ሃዲድ መዝጋታቸው ታውቋል::በመላው ኦሮሚያ ክልል የመንገድ መዝጋቱ ስራ የተሳካ እንደሆነ የገለጹት የየአከባቢው ነዋሪዎች ካለማቋረጥ ተቃውሞው እንደሚቀጥል ገልጸዋል::እንዲሁም ከአዲስ አበባ ደንቢዶሎ ወለጋ የሚያስገቡ መስመሮች በአማራ ቁጬ ቀበልጥ ተዘግቷል:: በወለጋ ነጆ እና ባቦጋቤ በሃረርጌ ኮምቦልቻም ተቃውሞ እየተካሄደ እንደሆነ ተሰምቷል:: ወያኔ በተለያዩ አከባቢዎች በአማራ እና ኦሮሞ ነዋሪእኦች መካከል ሊያስነሳ ያሰበው ግጭት ባለመሳካቱ ሰርጎ ገብ ጸጉረ ልውጦችን በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች እያዘለቀ በማስገባት ደም ለማፋሰስ ሙከራ ከማድረጉም በላይ ጭለማን ተገን በማድረግ ማንነታቸው ያልታወቁ የአከባቢው ነዋሪ ያልሆኑ ሕዝቡን ከቀየው በማፈናቀል በመግደል ቤት በማቃጠል ስራ ላይ መሰማራታቸው ታውቋል:: #ምንሊክሳልሳዊ