ጎጃም እና ጎንደር ክፍላተሃገራት የተቀናጀ ዘረፋ እና አፈሳ በወያኔ እየተካሄደ መሆኑ ተሰማ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ጎጃም እና ጎንደር ክፍላተሃገራት የተቀናጀ ዘረፋ እና አፈሳ በወያኔ እየተካሄደ መሆኑ ተሰማ::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Gonder‬ ‪#‎Gojjam‬ ‪#‎EthiopianArmy‬ ‪#‎MiilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የመከላከያ ሰራዊቱ በሃገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ የማብራሪያ ጥያቄ በማንሳቱ ግምገማ እንዲገባ የተደረገ መሆኑ የተሰማ ሲሆን ከባድ ውጥረት ለረዥም ጊዜያት ያየለባቸው ጎንደር እና ጎጃም ክፍለሃገራት የኦሮሞ ተማሪዎችን እና ገበሬዎች የቀሰቀሱትን የመብት ጥያቄ ተከትሎ በአከባቢው ከፍተኛ ውጥረት ይነሳል በሚል ከፍተኛ ስጋት ያደረበት ወያኔ በጎንደር እና ጎጃም አፈሳ የጀመረ ሲሆን በድንበር ከተሞች በስራ ላይ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆችን ንብረት እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የአማራ ተወላጆችን ንብረት ባደራጀው የማፊያ ቡድኖች በማዘረፍ እና በማቃጠል ላይ መሆኑ ታውቋል::

ወትሮውም ከፍተኛ የተቃውሞ ድምጽ የሚሰማበት ጎንደር በከተማው እስር ቤቱን በአገዛዙ ሃይሎች መቃጠል ተከትሎ የወያኔ ካድሬዎች የቅማንትን ነዋሪዎች ከቀሪው የጎንደር ሕዝብ ለመለየት ያደረጉት ሙከራ አንስተኛ ግጭቶች ተነስተው የነበረ ቢሆንም ሕዝቡ ያለውን እውነት በመረዳቱ ፊቱን ወደ አምባገነኑ አገዛዝ መልሶ ከወያኔ ጭፍሮች ጋር ተፋጦ ይገኛል::አሁንም ወያኔ ለማጨፋጨፍ የሚጠቀምበት የቅማንት ሰዎችን ስለሆነ ይህንኑ አጀንዳ ይዞ ጎጃም አቸፈር በመሄድ አዲስ ግጭት ለመፍጠር እየሰራ መሆኑ ተደርሶበታል:: ይህንን ግጭት ለማሳካት ደፋ ቀና የሚለው ወያኔ በጎጃም ባህርዳርና ደብረማርቆስ የሚገኙ ወጣቶችን በማፈስ ላይ ሲሆን ለትምሕርት በክልሉ ዩንቨርስቲዎች የተመደቡ ተማሪዎችን አማሮች ሊያጠፏቹህ ስለሆነ ራሳችሁን አዘጋጁ በሚል አደገና የሃሰት ፕሮፓጋንዳ እየነዛ እንደሆነ ከባህርዳር የተገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል::