ተዓምር እንሰራለን ያለው ዘራፊው የወያኔ አገዛዝ የሕዝብ ተቃውሞ አስደንግጦታል::ወያኔ አልተሳካለትም::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ከተቃውሞ ጀርባ አሉ የሚባሉ ተጠርጣሪ የኦሕዴድ ባለስልጣናት ስልካቸው ተዘግቶ ከቤታቸው እንዳይወጡ እየተደረገ ነው::በቤተሰቦቻቸው ላይ ከባድ ክትትል ይደረጋል::ወያኔ ግራ ገብቶታል::ተቃውሞው እየበረታ መምጣቱን ተከትሎ ግራ የገባው ወያኔ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ያሉ የሌላ ብሄር ተወላጆች ላይ ለመዝመት ያደረገው ሙከራ ያልተሳካለት ሲሆን ይብሱኑ ሕዝቡ በአንድነት አደባባይ ወጥቶ አገዛዙን በመቃወም ድምጹን ማሰማቱን ለወያኔ የእግር እስት ሆኖቦታል::አዲስ አበባ በአስቸኳይ የሰበሰባቸው የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ባለስልጣናት ሌሎች ብሄሮች ከክልላችሁ አስወጡ የሚል መመሪያ ቢሰጣቸውም ሕዝቡ አይሰማንም ሌላ መፍትሄ ይፈለግ ሲሉ ለደህንነት ሹሞቹ ተናግረዋል::ከአዲስ አበባ ወደ ስሜን ኢትዮጵያ እንዲሆም ወደ ወለጋ የሚያስገቡ መንገዶች ወደ ጅማ የሚወስደው መንገድ ተዘግቶ ትራንስፖርት ተሰተጓጉሏል::
ከአገዛዙ ቁጥጥር ውጪ የሆነው ተቃውሞው በዚሁ ቀጥሎ መከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ ሳይዘልቅ ሩጫ ላይ የሆነው ወያኔ ከቤሻንጉል ጉምዝ እና ከጋምቤላ እንዲሁም ከደቡብ ክልል ተመልምለው የተመረቁ አዳዲስ የፌድራል ፖሊስ አባላት ለመመደብ የተዘጋጀው አገዛዙ ሰራዊቱ ውስጥ ያለው አለመተማመን ዝምታን አስመርጦታል::ወያኔ በየዩንቨርስቲው እና በየክልል ከተሞች የላካቸው የኦሕዴድ ባለስልጣት አልተሳካላቸውም:ወርቅነህ ገበየሁ የሚመራውን ስብሰባ የወዲወላቡ ተማሪዎች ረግጠው ባዶ አደራሽ አስታቅፈውት ወጥተዋል::በሌሎች ክልሎች ለውይይት ባለስልጣናት ይመጣሉ ቢባሉም ተማሪዎች ከውይይት ይልቅ ተቃውሞውን መርጠዋል ሲል የደህንነት ቢሮ ሪፖርት ያመለክታል::ተቃውሞውን በሃይል ለመምታት ቢሞክርም ያልተሳካለት አገዛዙ ሕዝቡ ባለው መንግስት ላይ ተስፋ መቁረጡን በገሃድ መስእዋት በመሆን አሳይቷል:: #ምንሊክሳልሳዊ