በረሃብ የተጎዳው ወገን ቁጥር በእርዳታ ድርጅቶች ዳታ 13 ሚሊዮን ደረሰ:: ቀየውን ጥሎ የሚሰደደው በርክቷል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በረሃብ የተጎዳው ወገን ቁጥር በእርዳታ ድርጅቶች ዳታ 13 ሚሊዮን ደረሰ:: ቀየውን ጥሎ የሚሰደደው በርክቷል::
#Ethiopia #EthiopiaFamine #NGO #MinilikSalsawi #Drought #FAO
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በተለያዩ የሰሜን እና ምስራቅ ኢትዮጵያ ክፍላተሃገራት የተሰማሩ ከተለያዩ የአለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች የተገኙ ዳታዎች እንደሚያመለክቱት በድርቅ የተጎዳው እና በረሃብ አለንጋ እየተገረፈ ያለው ሕዝብ ቁጥር 13 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት መሰረት በጥር 2016 አስረ አምስት (15 )ሚሊዮን እንደሚገባ ተረጋግጧል::የእርዳታ ድርጅቶቹ ሰራተኞች እንደጠቆሙት በምስራቅ ኢትዮጵያ ሃረርጌ ውስጥ ብቻ ካለፈው ወር ከነበረው የረሃብ ተጎጂ ወገን ቀር በዚህ ዲሴምበር 2015 65% ከፍ ብሌል::የተረጂዎች ቁጥር እና የምግብ አቅርቦቱ እንዳይጨምር የመንግስት ባለስልጣናት ጫና ይፈጥራሉ ያሉት ሰራተኞቹ ሕዝቡ ቀየውን ትቶ ወደ ከተሞች እየዘለቀ መሆኑን ይናገራሉ::
በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ እና በአገው ልዩ ዞን እንዲሁም በአዲስ ዘመን አከባቢ ያለው ሁኔታ ከሌሎች የባሰ ሲሆን ከምስራቅ በለሳ እና ከአገው ምድር ሰቆጣ ቀያቸውን ጥልው በረሃብ ምክንያት የተሰደዱ በጎንደር አዲስ ዘመን ተሰፈሩ መሆኑ ሲታወቅ በትግራይ እንዲሁ እስካሁን እርዳታ ያላገኙ አከባቢዎች እንዳሉ ተጠቁሟል:: በአዲስ ዘመን ያሉ የብኣዴን ባለስልጣናት ከሰቆጣ እና በለሳ ተሰደው የሄዱትን ወገኖች መንግስት በያላችሁበት በጀት እየመደበ ስለሆነ በሚል ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ በማስገደድ ላይ መሆናቸው ታውቋል::ባለፈው ሳምንት በትግራይ በእንደርታ ወረዳ ለሚገኙ በድርቅ ለተጎዱ ተብሎ የመጣው ኣንድ እስካንያ መከኒ ከነተጎታቹ የእርዳታ እህል በወረዳው ባለስልጣናትና ነገዴዎች በመመሳጠር የተራገፈ ኣስመስለው በሌላ መኪና ገልብጠው ጭነው ሲወስዱ የኲሓ ህዝብ እጀ ከፈንጅ ይዞ ለፖሊስ ማስረከባቸው ይታወሳል::#ምንሊክሳልሳዊ
