በደቡብ ኦሞ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙትን ተቃዋሚዎች ለማሰር የሃሰት በራሪ ወረቀት ለመበተን መዘጋቸታቸዉን የዉስጥ አዋቂ ምንጮች ገለጹ፡፡


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በደቡብ ኦሞ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙትን ተቃዋሚዎች ለማሰር የሃሰት በራሪ ወረቀት ለመበተን መዘጋቸታቸዉን የዉስጥ አዋቂ ምንጮች ገለጹ፡፡በተለያዩ የሀገራቺን ከተሞች ስለአርበኞች ግንቦት 7 የተበተኑ በራሪ ወረቀቶች አይነት በዞኑ ከተሞችም ሊበተን ይችላል ከሚል ስጋትና የህዝቡን አንሰማችሁም እንቅስቃሴ ለማፈን የተቃዉሞዉ መሪ ናቸዉ የሚሉዋቸዉን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችንና ንቁ አባላቱን እንዲሁም ድርጊታቸዉን በየስብሰባቸዉና በፍርድቤቶች በመቃወማቸዉና በመክሰሳቸዉ ፣ከያሉበት መረጃ ለኢሳትም ሆነ ለሌሎች የተለያዩ ሚዲያዎች ያደርሳሉ ብለዉ የሚጠረጥሩትን ለማሰር ሊጠቀሙበት መምከራቸዉን በውስጣቸዉ የሚገኙ ሀገር ወዳድ ወገኖቻችን ገልጸዉልናል፡፡


የደቡብ ኦሞ ህዝብ አንቅስዋሴ ከሌላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የለውጥ እንቅስቃሴ የተለ አይደለምና በማሰርም፣በመግደልም፣ከሀገር በማሰደድም፣ከስራ በማባረርም ሆነ ቤት በማፍረስና ንብረት በመዉረስ ወ.ዘ.ተ. ትግሉን ሊያስቆሙት ቀርቶ ለሰከንድ ሊያጓትቱት አለመቻላቸውን ከዚህ የ24 ዓመት የጭፍን ጉዞ መማር ለፈለገ ከበቂ በላይ ነዉ፡፡


ስለእዚህ ታጋይ ይሞታል ትግል አይሞትም! መፈክር እውን የሆነበት ዘመን ላይ በመሆናችን የማንንም አሸባሪነትና ተሸባሪነት መግለጫ የምንጠብቅበት ወይም ሊነገረን የሚገባን ወቅት ላይ ስለአለመሆናችን የማንም ማብራሪያ አስፈላጊ አይደለም፡፡ህዝበ ወያኔ ሀርነት ትግራይ(ህውሃት)ከጫካ ጀምሮ የራሱን ወገኖች ሳይቀር ለፖለቲካ ትርፍ እየገደለ የመጣ ሀገር አጥፊ ቡድን ስልጣን ላይ ወጥቶ ኢትዮጵያን የማጥፋት መንገድ መከተሉ አላማዉን ከግብ ማድረስ ካልሆነ ምን ሊባል ይችላል፡፡

በደቡብ ኦሞም በታዛዦች የወያኔ አሽከሮች ይህ ቢፈጸም ሊደንቀን አይገባምና ብንታሰር፣ ብንገደል፣ ብንሰደድ፣ብንራብ፣ ከስራ ብንፈናቀል፣ወ.ዘ.ተ. ሊደንቀን አይገባምና የሀሰት ወረቀት በመበተን መወንጀል ቀርቶ የተለየ እርምጃ ቢወስዱ በርግጠኝነት የምንገልጸዉ ታጋይ ይሞታል ትግል አይሞትም !!!!ነዉ፡፡እናሸንፋለን !! ይልቁንስ ተላላኪዎች ከህዝብ ትግል ተደባለቁ አልያም ተስፋ ቁረጡ !!