መምህር ዘበነ ለማ ማወናበዱን ቀጥሎብታል፣ የመንግሥት (ወያኔ) አቋም በኃይማኖት ውስጥ የለም አለ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


መምህር ዘበነ ለማ የተባለው ግለሰብ በተደጋጋሚ ለወያኔ የሚያሳየውን ወገንተኝነትና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በወያኔ በመድረስ ላይ ስላለው መከራ ደንታ ቢስነቱን በዛሬው ዕለትም አስታውቋል። ወያኔ ኢትዮጵያን በባዕዳን እርዳታ ወሮ ከያዘበት ጊዜ አንስቶ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከሚባለው እየሰለጠኑ የሚወጡት ምሩቃን አብዛኛዎቹ ለሃገር ፍቅር ደንታ የሌላቸውና ለቤተክርስቲያኒቷ ተቆርቋሪነት የጎደላቸው መሆናቸው በተለያየ ጊዜ ሲጠቆም እንደነበር የሚታወቅ ነው። እነዚህ መምህራን ከካድሬነት ያልተለየ ቅስቀሳና ድጋፍ ለወያኔ ሲሰጡ በየጊዜው የሚታይ ነው። በዚህም መሠረት መምህር ዘበነ በቅርቡ በሊቢያ ውስጥ ሰማዕትነትን በክብር የተቀበሉትን ኢትዮጵያዊያን ለመዘከር ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ የተደረገውን ወያኔ የሚወገዝበት የኢትዮጵያዊያን ዝግጅት ላይ ሳይሳተፍ በአንጻሩ ለወያኔ አመቺ የሆነና እውነቱ የሚደበቅበት የማደናገሪያ ዝግጅት በግሉ ቨርጂኒያ ውስጥ ማካሄዱ የሚታወስ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ከጥቂት ዓመታት በፊት የሰማዕቱን የአቡነ ጴጥሮስ መስቀል በስጦታ ተበርክቶልኛል ብሎ አውደ ምሕረት ላይ አውጆ የነበረ ቢሆንም የማይገባውን መስቀል በእጁ ማስገባቱ ትልቅ ጥፋት በመሆኑ ከፍተኛ ተቃውሞ ስለደረሰበት የተናገረውን ቃል አጥፎ እንዳልተሰጠው መካዱ የሚዘነጋ አይደለም።
በዛሬው ዕለትም መመህር ዘበነ በቀጥታ በሚያስተላልፈው ሬዲዮ ላይ በቀረበው የጥያቄና መልስ መርሃ ግብር ላይ አንድ የኦርቶዶክስ ምዕመን ስልክ ደውለው ዋልድባ ገዳምን ወያኔ ማፍረሱን በመቃወም ሰልፍ ላይ መሳተፋቸውን ጠቁመው መምህር ዘበነ ለማ የሚያገለግልበት ቤተክርስቲያን ማስታወቂያዎችን ለምን በመንግስት (በወያኔ) ሬዲዮኖች ያስተላልፋል? ማለትም ለምን ከወያኔ ጋር ይተባበራል? ለምን ገዳማትን ከሚያፈርሱ ጋር አብሮ ይቆማል? በማለት ላቀረበው ጥያቄ መምህር ዘበነ መልስ ሲሰጥ በመጀመሪያ ምንም እንኩዋን እራሱ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆኖ እያለ ተገቢውን መልስ መስጠት ሲገባው የቤተክርስቲያኑን ቦርድ አነጋግሩ በማለት አምታቶ ሊያልፍ ቢሞክርም ጠያቂው የሚበገሩ ሆነው ስላላገኛቸው በመጨረሻ ሽምጥጥ አድርጎ በመካድ ኃይማኖትን አስመልክቶ የመንግስት አቋም የሚባል የተቃዋሚ አቋም የሚባል የለም በማለት መልሷል። ወያኔ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተወህዶ ቤተክርስቲያን ለማጥፋት ፖሊሲና ዕቅድ ነድፎ በመስራት ላይ እንደሆነ ከድርጅቱ ቁንጮዎች ከስብሓት ነጋና ከአባይ ጸሀዬ የተረጋገጠውን እውነታ መምህር ዘበነ በመካድ እንደዚህ ዓይነት ተራና የወረደ መልስ መስጠቱ ግለሰቡ በመምህርነት ካባ የተሸፈነ ካድሬ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ወንጌል የሚያስተምረን እውነቱንና ሀቁን ብቻ እንድንናገር ሲሆን፣ በተለይም ክህነት ያለው ሰው እንደዚህ ሲቀል መመልከት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የገባችበትን አዘቅት የሚጠቁም ነው የሚሉ በርካታ ምዕመናን ናቸው።

ቃለ ምልልሱን ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ።  open?id=0B7KetREHX_CgUVhUd2hCSWc1Rm8