የመጨረሻዋ የለውጥ ሂደት ላይ ነን መሆናችንን አውቀን ጊዜውን እንጠቀምበት::(ምንሊክ ሳልሳዊ)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የመጨረሻዋ የለውጥ ሂደት ላይ ነን መሆናችንን አውቀን ጊዜውን እንጠቀምበት::(ምንሊክ ሳልሳዊ)
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎EthiopianOppostionParties‬ ‪#‎Change‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ከ1997 ምርጫ ጀምሮ በተለያዩ አጋጣሚዎች ወያኔን በሕዝባዊ እንቅስቃሴ ለመጣል የነበሩ እድሎችን በአንድነት ቆመን ስላልተጠቀምንበት አገዛዙ እድሜውን ሊያስረዝም ችሏል::ልብ በሉ ሕዝቡ አደባባይ ተማሪው ተቃውሞ ወጥቶ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ይፋ የሚደረግበትን እቅድ እስከማሰረዝ ተፅእኖ አድርጓል::ወያኔ የውስጥ አደረጃጀቱ ለመፈረካከስ የሚያስችል እንዲሁም በሕወሓት አካላት እና በሌሎች የፖለቲካ አጋር ድርጅቶች በሚባሉት መካከል የጠለቀ አንድነት እና መተማመን ባለመኖሩ የደህንነቱ እና የመከላከያው እንዲሁም ቁልፍ የሆኑ ቦታዎች በአንድ አካላት ስር መሆናቸው በቂ ማረጋገጫ ነው::ኢሕኣዴግ እና አጋር በሚባሉ ድርጅቶች ውስጥ ትክክለኛ መተማመን ቢኖር ኖሮ በአንድ ብሄር የበላይነት ስልጣኖች ይሁኑ የውሳኔ አካላቶች በሞኖፖል አይያዙም ነበር::

በኢሕኣዴግ መሃል ያለውን አለመተማመን እና አንድነት አለመኖር በጥርጣሬ መተያየት እና በጥቅም መተሳሰው ተቃዋሚው ሃይል/የለውጡ ሃይል እንደ አንድ ስትራቴጂ ተጠቅሞ ድርጅቱን ለመበታተን የፖለቲካ ታክቲክ አልተጠቀመም:: የለውጥ/የተቃዋሚው ሃይል በደህንነቱ እና በመከላከያው ውስጥ ዘልቆ መግባት ባለመቻሉ እንዲሁም በየለውጥ ፈላጊ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ ያለው ክፍተት ሌላኛው የወያኔ እድሜ ቀጥል ችግር ነው::ወያኔ ውስጡ ተቦጥቡጧል::ጠንካራ እና ስትራቴጂ ያለው ከስድብ እና በፍረጃ የነጹ አባላት ያሉት በስልት እና በትግል ጽናት የተደራጀ የለውጥ ሃይል የሆነ ስብስብ ቢገኝ አሊያም በአሁን ወቅት ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ነጻ እናወጣለን ብለው የሚያስቡ የፖለቲካ እና የድርጅት ሃይሎች በአንድ በጋራ መነጋገር ቢችሉ የመጨረሻዋ ሰአት ድምቀት ይኖራት ነበር::ወያኔ ውስጡ እየበለጠ በተቦረቦረ ሰአት ሮጦ የተቃዋሚ ሃይሎችን ለማዳከም ገንዘብን እና ጠበንጃን በመጠቀም ጊዜ መግዛትን ይፈልጋል::የዚህን ወቅት ጠንካሮች ወያኔን በገባበት አጣብቂኝ ገብተው አንቀው መግደል ግን አልቻሉም::

ወያኔ ሌላው የመፈረካከሱ ምልክት በነፈሰበት ሁሉ ስለሚደናበር አባሎቹን አሰማርቶ ይለፈልፋል::ልፍለፋ ስድብ እና ፍረጃ የሽንፈት እና የባዶነት ምልክት ነው::ይህ በተቃዋሚዎችም አከባቢ የምናየው በሃሰት የተለበጠ የፕሮፓጋንዳ ጡዘት አጉል እንቅፋት መሆኑንም አንዘንጋ::በቅርቡ ፕሮፌሰር ብርሃኑ በአውሮፓ ፓርላማ ጽ/ቤት ስለረሃቡ እና ስለሃገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ በተደረገው የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት ወያኔ ም ያህል እንደደነገጠ በተግባር ያሳያል::በወያኔ አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀ ግለሰብ በምእራባውያን ኢንስቲቲዩሽን ውስጥ ተገኝቶ ትንታኔ መስጠቱ የወያኔ መቀበሪያ መድረሱ አንደኛው ምልክት ነው::ለዚህም የወያኔ ሰዎች በኦታው ተጠርተው አለመገኘታቸው እንዲሁም በውስጥ መስመር የአዲስ አበባው የአውሮፓ ሕብረት ጽ/ቤትን ማብራሪያ መጠየቃቸው ብሎም በየራዲዮ ጣቢያዎች እና በየማህበራዊ ድህረገጹ መንጫጫታቸው ምን ያህል እንደተርበተበቱ እና እንደፈሩ እንደደነገጡ ያሳያል::

ልጥላው የተማሪው እንቅስቃሴ የሕዝቡ ጉርምርምታ እንዲሁም የዲያስፖራው የጎላ ፖለቲካ በመጨረሻው የለውጥ ሂደት ላይ መሆናችንን አውቀን ልንጠቀምበት ይገባል::በተለያዩ ወቅቶች በሃገር ቤት የተነሱ ሕዝባኢ እንቅስቃስዎች በማደራጀት እና በመምራት ለለውጥ ልንጠቀምበት ሳንችል ቀርተን በዛ ያሉ እድሎችን አቃጥለናል::ወጣቱ ክፍል ለውጥ ይፈልጋል::የወያኔ አገዛዝ አንገሽግሾታል ::ይህ ደግሞ በተግባር እየታየ ነው::ታዲያ የለውጥ ሃይሎች ም እየሰራን ነው ቆም ብለን እናስብ በአንድነት እንቁም::24 አመት በስልታን ያሳለፈው ወያኔ እኛ በጋራ መነጋገር በጋራ መቆም በእኩልነት መስራት ከቻልን በ24 ሰአት ልንደመሥእው እንችላለን::በጋራ ሳንቆም ክፍተት በመሃላችን ፈጥረን እርስ በእርስ መፈራረጅ እና የስድብ ፖለቲካ ደግሞ ለወያኔ እድሜ መርዘም መሆኑን አንዘንጋ::የመጨረሻዋ የለውጥ ሂደት ላይ ነን መሆናችንን አውቀን ጊዜውን እንጠቀምበት::

Minilik Salsawi's photo.