የተባረሩት የዲላ ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ደጋፊዎች በጎሳ ተደራጅተው ለአመጽ እየተዘጋጁ ነው::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የዲላ ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ስለሺ ኮሬ በቀረበባቸው ከፍተኛ ክስ በሙስና ሴቶችን በማማገጥ እና ሌሎች የመልካም አስተዳደር ችግሮች ከስልጣናቸው መነሳታቸው ሲታወስ ይህን አስታኮ ፕሬዚዳንቱ አስቀድመው ያዘጋጁትና በዘር የተደራጁ ደጋፊዎቻቸው ጥቅማችን ተነካ ወገናችን የጌድዎ ልጅ ተባረረ በማለት በምክትል ፕሬዚዳንቱ በአቶ ሰለሞን ኃይሉ የሚመራ ቡድን በዩንቭርስቲውም ሆነ በከተማው ውስጥ የጌድዎ ተወላጆችን አመጽ ለማነሳሳት ውስጥ ውስጡን እየቀሰቀሱና እየሰሩ እንደሆነ ታውቋል::
በተነሳው ፕሬዝዳንት ምክንያት ለምን ተነሳ ያሉ ፕሬዝዳንቱ ያደራጀው በዘር ላይ የተመሰረተው መዋቅር “አንድ ሲዳማ መጥቶ” የትምህርት ሚንስቴሩን አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ማለት ነው የማይሆን ወሬ ሰምቶ ልጃችንን ( ዶክተር ስላሺ ኮሬን ) አባረረብን በማለት በምክትል ፕሬዝዳንቱ በአቶ ሰለሞን ኃይሉ የሚመራ ቡድን ከፍተኛ የወስጥ ለውስጥ እስከ ገጠር የሚደርስ ፕሮፖጋንዳ እየተሰራ በመሆኑ ወጥረቱ በከተማውም ሆነ በዩንቭርስቲው ውስጥ በሰፊው ነግሷል:: እንዲሁም የዲላ ዩንቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል በዶክተር ስለሺ ኮሬ አባት እናት ወንድሞች እህቶች እና ዘመድ አዝማድ በጥቂት የጌድዎ ሰዎች በዘር ማንዘር በመጥለቅለቁ ሕዝቡ መንግስት ጉዳዩን እንዲመለከትለት በጥብቅ እየጠየቀ መሆኑ ተጠቁሟል::