በኢትዮጵያ ሱዳን ድንበር የህወሓት ልዩ ኃይል ጦር በወረርሽኝ በመጠቃቱ ወደኋላ እንዲያፈገፍግ ተገደደ፡፡
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር አቅራቢያ ስናር መቅሪ ጨው ላይ ሰፍሮ የቆየው የህወሓት ልዩ ኃይል ጦር በወረርሽኝ በሽታ በመጠቃቱ ወደኋላ እንዲያፈገፍግ ተገደደ፡፡ ህወሓት የልዩ ኃይል ጦሩን ስናር ላይ ያሰፈረው በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ሲሆን በጦር ካምፑ ውስጥ ወረርሽኝ በመግባቱ እና ሁሉም አባላት በመታመማቸው በያዝነው ህዳር ወር ወደ ሆር ሁመር እንዲመለሱ ሆኗል፡፡
የልዩ ኃይል ጦሩ አባላትን ለወረርሽኝ ያጋለጣቸው የምግብና የንፁህ መጠጥ ውሃ እጥረት መሆኑ ተረጋግጧል፡፡የልዩ ኃይል ጦሩ አባላት የቀለብና የአልባሳት እንዲሁም የህክምና አገልግሎት ችግር ከአካባቢው መልከዓምድር አስቸጋሪነትና ቆላማነት በተጨማሪም ከሰፈነው ኢ፡ፍህታዊ አስተዳደር ጋር ተደማምሮ ከፍተኛ ምሬትና ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ስለከተታቸው አብዛኞቹ መሽሎኪያ ቀዳዳ በመፈለግ ላይ መሆናቸውን ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡የህወሓት አገዛዝ አብዛኛውን የጦር ኃይሉን በኢትዮጵያ ሰሜናዊና ምዕራባዊ ጠረፎች ያከማቸ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡
