ያልተዘመረላቸው ጀግና ወ/ሮ እማዋይሽ አለሙ !


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Eskedar Alemu Gobebo's photo.

ቀኑ ዓርብ ሚያዝያ 16/2001 ዓ.ም ነበር ። ብዙ ሲቪል የለበሱ እና የፌድራል ልብስ የለበሱ ፖሊሶች መሳሪያቸውን አቀባብለው ወደቤት በመግባት <<ስልካችሁን አጥፉ ወደማንም እንዳትደውሉ >> በማለት ለወ/ሮ እማዋይሽ ቤተሰቦች ትእዛዝ ይሰጣሉ ።

ቀጥሎም ቤቱን ለመፈተሽ የተፈቀደላቸውን ወረቀት እያሳዩ << ቤት ለመፈተሽ ነው የመጣነው ወ/ሮ እማዋይሽ በቁጥጥር ስር ውለሻል >> በማለት የመጡት ደህንነቶች እና የፌድራል ፖሊሶች ወ/ሮ እማዋይሽን አሳወቋቸው ። ቀኑ ዓርብ ስለነበረ ወ/ሮ እማዋይሽ ሰለሚፆሙ ገና ከስራ ገብተው የሚበላ እየጠየቁ ነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት ምግብ አፋቸው ላይ ሳያደርጉ ይዘዋቸው ወጡ ።
ወ/ሮ እማዋይች ከቤታቸው ከተወሰዱ ለ4 ወር ከማንም ባለመገናኘታቸው በህይወት ይኑሩ ወይም አይኑሩ የሚያውቅ አልነበረም ። አንድ ቀን ከወ/ሮ እማዋይሽ ጋር አብራ ታስራ የነበረች አንዲት ሴት ትፈታና ከወ/ሮ እማዋይሽ ለልጃቸው ለናርዶስ መልእክት ይዛ ትመጣለች ። መልእክቱም << አንቺ ደህና ከሆንሽ ሽሮና ጎመን ሰርተሽ ላኪልኝ ። እኔ ደግሞ ደህንነቴን የባናና ማስቲካ ወረቀት እልክልሻለሁ ። ደህና ካልሆንኩኝ ግን ያ ነገር ይቀራል ። >> የሚል ነበር ። በዚህ መንገድ ወ/ሮ እማዋይሽ ከልጃቸው ከናርዶስ ዘሪሁን ጋር ግኑኝነታቸውን ቀጠሉ ።


ወ/ሮ እማዋይሽ ሕገ – መንግስቱን በሃይል ለመናድ በህቡዕ ሰርተዋል በሚል በእነ ብ/ጄ ተፈራ ማሞ መዝገብ የተከሰሱት ናቸው ። 25 ዓመት እስር የተፈረደባቸው ወ/ሮ እማዋይሽ አለሙ ዛሬም በእስር ይገኛሉ ።

Menbere Kassaye