በብድር እና እርዳታ የተገኙ የውጪ ምንዛሬዎች የት እንደገቡ አይታወቅም::ረሃቡ የኢኮኖሚ ቀውስ ፈጥሯል::‪ (ምንሊክ ሳልሳዊ)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በሓገራችን የተከሰተውን ድርቅ እና ያስከተለውን ረሃብ ለመቋቋም በሚደረጉ ጥረቶች በአቅርቦት እና በፍላጎቶች መካከል እጅግ ሰፊ ልዩነት ከመኖሩም በላይ ግልጽነት የጎደለውና በፖለቲካ ላይ የተመሰረተ አድልዎ እንዲሁም ከፕሮፓጋንዳ ውጪ ፈጣን እና የተቀናጀ ስራ በተግባር ስለማይታይ በድርቅ የተጠቁ ወገኖች ቤትና ንብረታቸውን ጥለው ወደ ከተማዎች እየፈለሱ ነው::ይህ ደግሞ ብዙሃኑን ስራ አጥ እና ጥቂቱ ሰራተኛ የሆነውን በከተማ ለሚኖረው ሕዝብ እጅግ ፈታኝ እና አደጋ እየሆነ በመምጣቱ የገብያው መናጋት የዋጋ ግሽበቱን አባብሶታል:: የክረምቱ ዝናብ እንደሚስተጓጎል የበልጉም እንደማይመጣ በቂ መረጃ ያለው አገዛዙ እጁን አጣጥፎ በመቀመጥ የፈጠረው ድርቅ ከሶሪያ ጦርነት በላይ ሰብኣዊ ቀውስ አስከትሏል::ጉራውን ሲቸረችር የነበረው አገዛዝ እርዳታ ከነጮች ቢለምንም ሊያገኝ ባለመቻሉ ከፍተኛ ሆድ ቁርጠት እና ራስ ምታት ላይ ይገኛል::

Minilik Salsawi's photo.

የዋጋ ግሽበት በእጥፍ ከመጨመሩም በላይ ሕግን እና ስርኣትን ያልተከተለ ግብይት የመንግስት ሰራተኛው የደሞዝ እርከን አለማደግ ከፍተኛ የስራ አጥ መጨመር በድርው እና በፖለቲካ ባለስልጣናት ጫና ወደ ከተማ የሚፈልሰው የገጠር ነዋሪ ካለምንም ምክንያት የሚደረገው የገበሬዎችን መሬት ነጠቃ ኢኮኖሚን ከፖለቲካ ግብኣት መጠቀም ሙስና በስልጣን መባለግ የመሳሰሉት የአገዛዙ የቁም ሽባነት እና ሬሳነት የዋጋ ግሽበት አስከትለዋል:: ከአገዛዙ ሚዲያ የፕሮፓጋንዳ ስብከት እጪ አገዛዙ ራሱ የሚያስጠናቸው የስታስቲክ መረጃዎች በግልጽ እንደሚያሳዩት በሃገሪቱ ያለው የኑሮ ውድነት ከሸክም በላይ እየከበደ መሆኑን በገሃድ ያሳያል::ሕዝቡ በድርቅ የተጎዳውን ወገኑን እንዳይተባበር አገዛዙ በቂ መረጃ እንዳይገኝ እየሸፋፈነ ቢሆንም አለም አቀፍ ሚዲያዎች እስከዛሬ በሰፊው እየተናገሩት ይገኛሉ::

ያሽቆለቆለው ኢኮኖሚ የተናጋው ገበያ መልሶ የማይስተካከል በፊትም በነበረው ላይ ተጨማሪ የዋጋ ግሽበት አስከትሏል::ድርቁን አያይዞ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ፈጥሯል::የሃገሪቱ ካዝና ባዶ ሲሆን በብድር እና እርዳታ የተገኙ የውጪ ምንዛሬዎች የት እንደገቡ አይታወቅም::በየባንኩ የሚታየው የውጪ ምንዛሬ የለም እጥረት ገጥሞናል የሚሉ ምላሾች ለባንኮች እና ለገንዘብ ተቋማት ትልቅ ራስ ምታት ሆኗል::በአገሪቱ የተከሰተው ድርቅ ወያኔ ከመደብኩት በጀት ለልማት ካሰብኩት ገንዘብ ቀንሼ ረሃቡን አስወግዳለሁ ቢልም ከውጪ እህል ለመግዛት የውጪ ምንዛሬው ከየት ይምጣ ለላምት በጀት ይዣለሁ የሚለው ወያኔ እንደ ቻይና ካሉ ሃገሩን በብድር ካገኘው በእጁ ካልገባው በተዘዋዋሪ ወደ ቻይና ከሚመለሰው ገንዘብ ምን እየተሰራ እንደሆነ ዘንግቶታል::አለ የሚባለው ግን ከቁጥር የማይገባው ልማት እኮ በእጅ ላይ በሚገኝ ገንዘብ ሳይሆን ትውልድ በማይከፍለው የወለድ እዳ እየተሰራ መሆኑ አይካድም::