የዓዲ ግራት ኣገር ሽማግሌዎች ቁጣ ህወሓትን ክፉኛ ኣስደንግጠዋል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የዓዲ ግራት ወይም የዓጋመ ኣገር ሽማግሌዎች ቁጣ ህወሓትን ክፉኛ ኣስደንግጠዋል። Amdom Gebreslassie

የኣገር ሽማግሌዎቹ ሰሞኑ የምስራቃዊ ዞን ኣስተዳዳሪ ወይዘሮ ያለም ፀጋይና ከክልል የመጡ ባለስልጣናት ያደረጉት ስብሰባ በዓጋመ ብሎም በትግራይ ኣጋጥሞ ያለው ምስቅልቅሉ የወጣው ዘርፈ ብዙ ችግር ለመፍታት ያለው ብቸኛ ኣመራጭ ስር ነቀል ልውጥ ( ራዲካል ቸንጅ ) ማካሄድ መሆኑ ኣመላክተዋል።

ያገር ሽማግሌዎቹ የዞኑ ሃላፊዎችና ካድሬዎች ማፈናፈኛ ኣሳጥተው ዓፍነው እየገዙት እንዳሉ ኣምርረው ገልፀዋል።

“እንደ ኣጋጣሚ በተገኘንባቸው ስብሰባዎች የተለየ ሃሳብ ስንሰጥ ‘ዓረና’ እንባላለን። በጣም የሚያስገርመው የሚባል ሲያጡ ደግሞ ‘ኦነግ’ የሚል ቅጥያ በመለጠፍ ፈርተን ዝም እንድንል ያስገድዱናል ” ሲሉ ተናግረዋል።

ልጆቻችን እያስጠሩ “ወላጆቻቹ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የዓረናና ኦነግ ኣባላት መሆናቸው ኣረጋግጠናል። ታፍነው ከመጥፋታቸው በፊት ኣርፈው እንዲቀመጡ ምከሯቸው” እየተባለ ሽብር ይለቁብናል።

የዓድግራት ተወላጅ የሆኑትና ከውጭ ኣገር መጥተው ኢንቨስት ለማድረግ የሞከሩት 9 ባለ ሃብቶች ምክንያቱ ባልታወቀ መንገድ ስራቸው እንድያቋርጡ ተደርገው ተባረዋል” ሲሉ ስም እየጠቀሱ ገልፀዋል።

ፍትህ የሚባል ነገር ገንዘብ ከሌለህ ኣይታሰብም። ሙስና፣ የመሬት ወረራ፣ ባጠቃላይ ያለፉት ዓመታት መንግስት ነበረ ለማለት እንደሚዳግታቸው ገልፀዋል።
እነ ወይዘሮ ያለም ፀጋይ መስተዳድሩ የሰራቸው ጥፋቶች በሙሉ እንደሚቀበሉና ለህዝቡ ይቅርታ የጠየቁ ሲሆኑ ችግሮቹ ለመፍታት ጠንክረው እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል። የህዝቡ ሃሳብ ለማድመጥም በየ ሶሶት ወሩ የውይይት መድረክ ይዘጋጃል ብለዋል።

ያገር ሽማግሌዎቹ ” ለውጥ መምጣት የሚቻለው ሱር ነቀል ለውጥ ( ራዲካል ቸንጅ) እርምጃ ሲወስድ ነው። ኣለበለዝያ ሁሌ እንደምታደርጉት ኣዳራሽ ውስጥ ይቅርታ ጠይቃቹ ደጃፍ እንደምትረሱትና ችግሩ እንደምታባብሱት እናውቀዋለን” ሲሉ ይቅርታው እንደማይቀበሉትና የተገባው ቃል ፋይዳ ቢስ መሆኑ ገልፀዋል።

የዓጋመ ህዝብ በሃገራችን ኣጋጥሞ ያለው ዘርፈ ብዙ ችግር ሱር ነቀል ለውጥ ( ራዲካል ቸንጅ ) እንጂ የህወሓት ጥገናዊ ለውጥ ለማምጣት መታገል ከንቱ ነው እያሉ ነው።

እናንተስ የዓጋመ ህዝብ ሃሳብ ትጋራላቹ ወይስ ጥገናዊ ለውጥ ብቻ በቂ ነው ትላላቹ?

ነፃነታችን በእጃችን ነው…!

IT IS SO ……!

‪#‎ዘበን_ኣካሒዳ‬

‪#‎Ethiopian_Famine‬

Amdom Gebreslasie's photo.