ወያኔ ትግሬ ስጋ እንጂ ነብስ የለውም ( ኄኖክ የሺጥላ )


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ወያኔ ትግሬ ስጋ እንጂ ነብስ የለውም ( ኄኖክ የሺጥላ )

የፍገራ ፖለቲከኛ ፣ ወያኔና ትግሬ አንድ አይደሉም ይላል ።
ይህ የሞግዚት ፖለቲካ ነው፣ ይህ ቀላዋጭነት ነው ፣ ይህ ስቃይን በአንቀልባ መሸከም ነው ፣ ይህ ራስን መካድ ነው ። እውነቱ ግን ላለፈው 40 ዓመት ላይለያዩ አንድ ሆነው እየኖሩ ነው ! እውነቱ እያንዳንዱ ትግሬ ፣ የህወሓት ነገር በደም ስሩ ውስጥ ይዞራል ። እያንዳንዱ የትግራይ ሰው ወያኔ ሲባል የሚንዝረው ነገር አለ ። እርግጥ ነው እርስ በእርሳቸው ይጠላሉ ይሆናል ፣ ይጣሉ ይሆናል ( ይሄ ደሞ ተፈጥሯዊ ነው !) ። አድዋ ከ ሽሬ የተሻልኩ ነኝ ሊል ይችላል ፣ አክሱም ከስልጣን ጠረፔዛው በከፊልም ይሁን ተገፍቶ የበይ ተመልካች ሆኖ ሊሆን ይችላል ። የነ ስዬ አብረሃም ይሁን የአቶ አስገደ ገ/ስላሴ ከስርዓቱ ጋ ያላቸው ችግር የወያኔን ክሽፈት ከመቃወም የመነጨ አይደለም ፣ መሪዎቹ ስርዓቱን አደጋ ላይ ይጥሉታል ከሚል ተቆርቋሪነት የሚመነጭ እንጂ ( የምለውን ለመረዳት በአቶ አስገደም ይሁን በሌላ ቀደምት ተጋዳላይ የትግራይ ተወላጆች የተጻፉትን በእርጋታ አንብቡ !) ። በዚህ ደረጃ እንደ ገብረመድህን ( ገብርዬ ) አንድም ስለ ህውሃት መሰረታዊ ክሽፈት ከሥርዓት አንጻር የተናገረ ያለ አይመስለኝም ። ስለዚህም አመሰግነዋለሁ ! “አንድ እንኳ ቢኖር እምርልሃለው” ላለው ምናልባት ገብረመድህን የመማሪያ ሰብ ይሆን ይሆናል ! ማን ያውቃል ? የሚዲያ እና የድረ-ገጽ ባላባቶቹም ከመለስ ጋ ያላቸውን ተቃርኖ የሚያሳዩበት ኩርፊያ እንጂ ፣ ትግራይ ክልሏ ተቆረሰ ፣ ድንበሯ ተማሰ ከሚል የአዞ እንባ ተነስተው እንጂ ፣ ስለ ሌላ ክልሎች/ ህዝቦች ቁብ ኖሯቸውም አይደለም ! እነሱ እና እነሱ ብቻ ናቸው ልክ ፣ እርግጫውም አኅያ ቢራገጥ የሚለውን ተረት የሚያስታውስ ነው !

አብዛኛው የትግራይ ሕዝብ ወያኔን ( ህወኃትን ) አይደግፍም ለምትሉ ። የተማረው ፣ ክፉና ደግ የለየው ፣ ስለ ረሃብ የሚሰማው ፣ የሚያነበው ፣ ከሀገሩ የወጣው ፣ በሰው ሀገር ለመረጃ ቅርብ ሆኖ የሚኖረው ፣ ከማንኛውም አይነት አካላዊ አደጋ ርቆ የሚኖረው ትግሬ ወያኔን ይደግፋል ! አይደግፍም ? ምናልባት እንደነሱ ለመመለስ < ስለ ምንም አያገባንም ብሏል > ይህ ደሞ ( silent vote ) በዝምታ መምረጥ የሚባለው አይነት ነው ። እሱ የህዝቦቹን በደል እያየ ፣ ክፉና ደግ መለየት እየቻለ ፣ የስርዓቱን ጥፋት እየተረዳ ፣ ስርዓቱን የሚደግፍ ከሆነ ፣ በጨለማ ፣ ከእውቀት እና ከመረጃ ርቆ ፣ የምገል ጥይት ፣ የሚያስር ካድሬ አጠገቡ የቆመበት ትግሬ ፣ ምን አይቶ ነው የማይደግፋቸው ? መቃወም በሚቻልበት ማንኛውም አይነት ምድራዊ ሁኔታ ላይ ያለ ትግሬ መቃወም ሳይችል ( ሳይፈልግ ) መቃወም ዋጋ በሚያስከፍልበት ቦታ ላይ ያለ የትግራይ ገበሬ ለምን ይቃወማል ? ከዚህ የምንረዳው ትግሬ በሙሉ ወያኔን ይደግፋል ።

ትንሽ ታሪክ
አርማጮ በነበርኩበት ጊዜ ፣ ድንበር ላይ በችግር የጠቆሩ ፣ የገመድ አልጋ ላይ የሚተኙ ፣ በወባ በሽታ የሚሰቃዩ ና ይህ ነው የሚባል ጥቅም የማያገኙ የቀድሞ ታጋዮች ፣ ከወያኔ ወታደሮች በተሻለ ፍቅር እና <ቆራጥነት> በኤርትራ በኩል የሚመጡ የአርበኞች ታጋዮችን የሚዋጉት እነሱ እንደነበሩ አይቻለሁ ። እነዚህ ሰዎች የትግራይ ገበሬዎች ናቸው ፣ እነዚህ ሰዎች የጎንደርን መሬት ቀምተው የሚያርሱ ባለግዜዎች ናቸው ፣ እነዚህ ይህንን እውነት በማያውቀው የፍገራ ፖለቲከኛ < ወያኔን አይደግፉም > የሚባሉት ናቸው ። እውነታው ግን ሌላ ነው ! የተወሰኑ ትግሬዎች መለስን ይጠሉ ይሆናል ፣ የተወሰኑት ስዬ አብረሃን ይጠሉ ይሆናል ፣ የተወሰኑት አባይ ወልዱን አይወዱ ይሆናል ፣ የተወሰኑት በሀየሎም መገደል ይቆጩ ይሆናል ፣ የተወሰኑት የክንፈ ገ/መድህን መገደል ያንገበግባቸው ይሆናል ፣ የተወሰኑት ዔርትራዊው ጀሚል ያሲን መሐመድ ( ጄሚያስ ፎር ካርስ ፣ የሃየሎም ገዳይ ) መለስ የሰጠውን የቤት ሥራ ነው የሰራው ብለው ያምኑ ይሆናል ፣ የሆነው ሆኖ ግን ሁሉም ስለ ህወሓት ( ወያኔ ) ያላቸው አቋም አንድ ነው ! ሁሉም ወያኔን እስከ ሞት ድረስ ይደግፋል ። እስከ ሞት ድረስ ወያኔን የሚጥል እስካልመጣ ድረስ ፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋ መቸም ቢሆን አይቆሙም ! አስታውሱ አብዛኛዎቹ የባንዳነት ታሪክ ያላቸው ሰዎች ናቸው ። ባንዳ እና ሹምባሽ ደሞ ሆድ እንጂ ሀገር የለውም ፣ ስጋ እንጂ ነብስ የለውም !