ከአለም ኢኮኖሚዋ በቁጥር ቁልል የሚያድግ በምግብ ራሷን ያልቻለች ብቸኛ አገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት:: ‪(ምንሊክ ሳልሳዊ)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ከአለም ኢኮኖሚዋ በቁጥር ቁልል የሚያድግ በምግብ ራሷን ያልቻለች ብቸኛ አገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Ethiopiafamine‬ ‪#‎EthiopiaEconomy‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የድርቁ እና የረሃቡ ጉዳይ የተፈጥሮ አደጋ ጀምሮት ወያኔ እንዳባባሰው ልንዘነጋው አይገባም:: 50 ሊትር የመኪና ነዳጅ ወይም ባዮፊዩል ለማምረት 200 ኪሎግራም በቆሎ ያስፈልጋል። ይህ ደግሞ “አንድን ሰው ለአንድ ድፍን ዓመት ለመመገብ ይበቃል!””ልማታዊው” የወያኔ አገዛዝ ከ1999-2007 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከ23 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት (ከሀገሪቱ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት 20 ከመቶ የሚሆነውን) ባዮፊዩል ለሚያመርቱ 80 ኩባንያዎች ሸጧል፤ኩባንያዎቹም 1.8 ቢሊዮን ሊትር ባዮፊዩል አምርተው ወደ ሰሜን አሜሪካና አውሮፓ ልከዋል። በዚህ መሠረት 7.2 ሚሊዮን ኪሎግራም በቆሎና ሌሎችም ለምግብነት የሚያገለግሉ የሰብል ዓይነቶች ለነዳጅ ማምረቻ ውለዋል። እነዚህ ባዩ ፊዩል የተመረተባቸው መሬቶች ለምግብ ምርት አገልግሎት ቢውሉ በእያንዳንዱ ዘርፍ 36 ሺህ ሰዎችን ለአንድ ድፍን ዓመት ለመመገብ ይበቃል፤ የወገን ጉዳይ ግን ለወያኔ ቁብ ስለማይሰጠው ለውጪ ኩባንያዎች ቅድሚያ በመስጠት ወገንን መግፋት ስራዬ ብሎ ተያይዞታል::

“የልማታዊው” የወያኔ አገዛዝ የውጭ ዕዳ መጠን (External debt) 30 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይም 1.2 ትሪሊዮን የኢትዮጵያ ብር ደርሷል። የዕዳው መጠን አገዛዙ ከአገር ውስጥ ባንኮች የተበደረውን አይጨምርም፤ ሃገሪቱ ብድርን በተመለከተ አሳሳቢ መንፈል የማትችልበት ደረጃ ላይ መሆኗን የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይናገራሉ::ይህን ወያኔ በደመነብስ የሚበደረውን እና በዘረፋ ላይ የዋለው ብድር በጣም አሳሳቢ ብለው የሚፈርጁት የአለም ባንክና አይኤምኤፍ ናቸው ። ምክንያቱን ፡በጥቂት ዓመታት ውስጥ፣ የውጭ እዳ፣ በፍጥነት እየተገዘፈ መምጣቱ እና የብድሩ ዓይነት፣ ለከፍተኛ የወለድ ክፍያ የሚዳርግ መሆኑ ደግሞ፣ አሳሳቢ እና ተጨማሪ ስጋት እንደሆነ ይጠቅሳሉ። እዳ በፍጥነት ሲከማችና ወለዱ ከፍተኛ ሲሆን፣ የእዳ ክፍያው፣ እየከበደ ይመጣል።

ራሱን ልማታዊ፤ የዲሞክራሲ ፈርቀዳጅ ወዘተ እያለ የሚያንቆለጳጵሰው የወያኔ/ኢህአዲግ አገዛዝ ከ1995-2004 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ዕድሜያቸው ከስድስት ወር እስከ 2 ዓመት የሆነ ከ32 ሺህ በላይ ህጻናቶችን 9.8 ሚሊዮን ዶላር ሸጧል፤ከተለያዩ የውሽ ሃገር ደላሎች ጋር በመመሳጠር ሕጻናትን በጉዲፈቻ ስም መሸጥ እንዲሁም ታዳጊ ሴቶችን ለወሲብ ኢንዱስትሪ ማቅረብ የወያኔ አና መለያ ተግባሩ ነው::በተለያዩ ሃገራት በጉዲፈቻ ስም የሄዱ ኢትዮጵያውያን ሕጻናት ከከባድ ቶርቸው እና የጉልበት ስራ ጀምሮ እስከ ሞት ድረስ መድረሳቸው በማስረጃ ያየነው የሰማነው ሲሆን ሕገወጥ የሆነ ይህ አገዛዝ ለዜጎቹ ውርደት ከመስራት ቦዝኖ አያውቅም::የወያኔ አገዛዝ ስራዎቹ ሁሉ ሕገወጥ እና ሃሰተኛ በመሆናቸው በሃገሪቱ ከወንጀል እና ድህነት ውጪ ምንም አይነት ልማት የለም:: ኢኮኖሚዋ በየዓመቱ በቁጥር ብቻ አሥራ አንድ በመቶ የሚያድግ ነገር ግን በምግብ ራሷን ያልቻለች ብቸኛ አገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.