ክሃገር ውስጥ በረሃብ ለተጎዱ ወገኖች ለእርዳታ ተለግሰዋል የተባሉ እህሎች በተዘዋዋሪ እየተዘረፉ ነው።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Minilik Salsawi – ከሃገር ውስጥ ነጋዴዎች ተገዝተው በተለያዩ ግለሰቦች አና የግል ተቋማት በኩል በድርቅ አና በረሃብ ለተጎዳው ሕዝብ በኣገዛዙ በኩል እንዲደርሱ የተለገሱ እህሎች በኣገዛዙ የደህንነት ሰዎች አና በስግብግብ ነጋዴዎች በተደረገ ስብጥር በተዘዋዋሪ አየተዘረፉ ለገበያ አንደሚቀርቡ ታውቋል።
የእርዳታ አህሎቹ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ሊከፋፈሉ ነው በሚል ተጭነውና ተዘጋጅተው ኣስፈላጊ ፎርማሊቲ አና የካሜራ ቀረጻ ከተደረገላቸው በሗላ መንገድ አንዲጀምሩ ቢደረገም የታለመላቸው ቦታ ሳይደርሱ ለድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ኣቅራቢያ በሆነ በሌላ መጋዘን ከተራገፉ በሗላ በደላሎች ኣማካኝነት ለሚመጡ ነጋዴዎች አንደሚከፋፈሉ ጉዳዩን በቅርበት የተከታተሉ ወገኖች ተናግረዋል።
ኣገዛዙ በሃሰት ፕሮፓጋንዳ ተወጥሮ በረሃብ የተጎዱ ወገኖችን አየረዳሁ ነው ቢልም በኣዲስ ኣበባ ከቀያቸው ተፈናቅለው የፈሰሱ ወገኖች ምንም ኣይነት አርዳታ አንዳላገኙ ሲናገሩ ተደምጧል።
