በረሃብ ጠኔ ኣደጋ የሟቾች ቁጥር አየጨመረ ነው፥ በሁመራ ሰዎች አየሞቱ ነው።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ረሃብ የወለደው መርዶ
*************
ዛሬ እሮብ 15 / 03 / 2008 ዓ/ም ከቀኑ ኣምስት ሰዓት ኣከባቢ ከሑመራ ኣደባይ ቀበሌ የደረሰኝ የስልክ ጥሪ እጅግ የሚያሳዝን ረሃብ የፈጠረው መርዶ ነበር።
ዛሬ ረፋድ የኣደባይ ከተማ ህዝብ ኣንዲት በረሃብ የሞቱት እናት ቀብር መዋሉን ከቦታው ተደውሎ ተነገረኝ።
የሞቱት እናት ስማቸው በመግለፅ ከነገረኝ በኋላ ሰሞኑን በረሃብ የሞቱት ሌሎች ተጨማሪ የሁለት ሰዎች ስም ዝርዝርም ሰጠኝ።
ኣስከትሎም በኣሁኑ ሰዓት በረሃብ ጠኔ ተይዘው እግራቸው ያበጠና በሞት ኣፋፍ የሚገኙ በርካታ ኑዋሪዎች ዝርዝር ስም ሊሰጠኝ እንደሚችል ከነገረኝ በኋላ ቤቶቻቸው ዘግተው ለስደት ከሄዱትና ሱዳን ድንበር ከደረሱ በኋላ ወሬያቸው የታጣ 63 ቤተ ሰቦች ህልውና እንዳጡ ገልፀውልኛል።
ህዝቡ ከመንግስት ምንም እርዳታ እንዳልቀረበለት፣ ተስፋ ቆርጦ ወደ ስደት እግሩ ኣምርቶ ኣለማቀፍ ገባሬ ሰናይ ድርጅቶች እርዳታ እንዲያደርጉለትና የስደተኞች ካምፕ እንዲያዘጋጁለት እንደሚጠብቅና እንደሚፈልግ ገልፀውልኛል።
በምዕራባዊ ዞን ሰቲት ሑመራ ከተማ ጨምሮ 7 ቀበሌዎች በከባድ ድርቅ መመታታቸው ይታወቃል።
በተለይ በማይካድራ ቀበሌ በመስከረም ወር 3 ኑዋሪዎች በረሃብ ሙተው እንደተገኙ ተገልፆ ነበር።
የትግራይ ክልል መንግስት ረሃቡ በመደበቅና ህዝቡ እንዳይሰደድ በማገድ በርካታ ሰዎች ቤታቸው ዘግተው በረሃብ እያለቁ እያደረገ ነው።
እርዳታ ማከፋፈል በተጀመረባቸው ኣከባቢዎችም የመዳበርያ፣ የጋዜጣ፣ የማሕበራት ዕዳ ወዘተ እየተባለ እርዳታው እየተቆረጠ ተመልሶ ወደ መንግስት ካዝና እንዲገባ እየተደረገ ይገኛል።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።
IT IS SO………! Amdom Gebreslassie
