ክሕወሓት ብኣዴን ተፋጩ እስከ ሰማያዊ ፓርቲ የስልጣን ማግለል አጀንዳ በማህበራዊ ድረ ገጽ ሲፈተል (ምንሊክ ሳልሳዊ)
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ቁጭ ብሎ የማህበራዊ ድረ ገጽ ፉጨቶችን ልትሚያዎችን ጡዘቶችን እያዩ መታዘብ ደስ ይላል::የረሃቡን እና የድርቁን አጀንዳ ለመደበቅ ካርታውን ለመፐወዝ በወያኔ የተደረጉ ጥረቶች ከሞላ ጎደል ተሳክተዋል ቢባልም ወያኔ አስቻ ሰአት እየጠበቀ የሚጫወተው ሚና ስሜታውያን እና ያልበሰሉ ፖለቲካኛ ነን ባዮች በተከማቹበት የማህበራ ድረ ገጽ በተለይ በፌስ ቡክ በበላይነት እያሾረ ይገኛል::አንፍሶ ማስነፈስ ኮርኩሮ ዘራፍ ማሰኘት አንዱን ጥሎ አንዱን ማንሳት ቁም ነገርን አንከባሎ የማይረቡ ጉዳዮች ላይ ማፏጨት እንዲገን ማድረግን ተክኖበታል::ይህንን እውነት ላለመዋጥ የሚፈልጉ ብዙዎች ቢሆንም ራሳችን ግን አንቅተን የወያኔን አጀንዳዎች ተበልቶባችኋል ብንል ለመስመራችን ጠቃሚ ሆኖ ይታየኛል::
የለውጥ ሃይሎች ለወገን ያላቸውን ተቆርቋሪነት በሚያሳዩበት በማንኛውም ወቅት ላይ ወያኔ ደግሞ ይህን አደናቅፎ በራሱ ማእቀፍ ለማድረግ ደፋ ቀና ይላል ለዚህ ደሞ አጀንዳ ይፈጥራል::ይህ የሚራገብ አጀንዳ ደሞ እንዴት እንደሚቀጣጠል ወያኔ ያውቅበታል እነማንን ወደነማ እንደሚያዘምትም ተገልጾለታል ከዛ ስሜታውያንን እና እንጭጮችን በነፈሰበት አንፍሶ ማስጮህ ብቻ ነው::ዛሬ የሚባለው ነገር ቢኖር እንንቃ በራሳችን የቴክኒክ ጉድለት የራሳችንን አጀንዳ እያጠፍን ለወያኔ ድራማዎች ትኩረት እየሰጠን መሆኑን አንዘንጋ::የለውጥ ሃይሎች አንድነት ማጣት እየገረመን የአጀንዳ ማራመጃ መሆን እንዲሁም አጨብጫቢ እና አሽቋላጭ መሆን ያለውን ወያኔን የማስወገድ ትግል እንደሚያዘገየው ማወቅ አለብን::
ወያኔ ካድሬዎቹ እና ጭፍሮቹ በሃሳብ ፍጭት በውይይት በማስረጃ ማጣቀሻ ክርክር አያምኑም::ይህንን ማወቅ አለብን::ወያኔ ራሱን የሚያዋርደው ዜና ሁሉ ፈጥሮ አጀንዳ እና ማስጨፈሪያ ያደርገዋል::ወያኔ ግን ከገባበት አጣብቂኝ ለመውጣት ጊዜ ይገዛና ተፍጨርጭሮ ወደ ነበረበት ቦታ ይመለሳል::ወያኔ አጣብቂኙ ሲበረታበት ደሞ የራሱን ጭፍሮች ከመዋጥ ጀምሮ እስከ አደገኛ የማፊያ ድርጊቶች ላይ ይሰማራል ለዚህም ተባባሪዎቹ ከጎረቤት አገሮች ጀምሮ እንስከ ተለያዩ አህጉሮች በሃገሪቱ አንጡረ ሃብት በረዣዥም እጆች ይቆጣጠራቸዋል::በሃገሪቱ ያለው ድርቅ እና ረሃብን ለመሸፋፈን በትግል ጀግንነት የታሪክ ሽሚያ ውስጥ የገቡ ለማስመሰል በተፈጠረ አጀንዳ የሕወሓት እና ብኣዴን ካድሬዎች በሃስት ዱላ ሲኮራኮሙ ከርመዋል ::ይህ አጀንዳ በሕወሓት የተዘጋጀ አጀንዳ ስለነበር ሊደንቀን አይገባም ከዚህ በላይ ገና ስለሚጠብቅ ይህንን በትንሹ ለመማሪያነት ልንወስደው ይገባል::
ሌላው ደሞ በአስተሳሰብ ፍጭት ሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ የተከሰተው የስልጣን ማግለል አጀንዳ ነው::ይህ አጀንዳ እርግጥ ወያኔ ባይፈጥረውም ብዙዎች ሲሳሱለት የነበረ ግለስብ በራሱ ሰአት በሃሳብ ልዩነት ከፓርቲው መለየቱ ተሰምቷል::በሃሳብ ልዩነት ከፓርቲው መለየቱ መብቱ ነው::ማናችንም የምንታገልለት ጉዳይ የመብት እና የሃሳብ መከበርን ጉዳይ እስከሆነ ድረስ ውሳኔዬ ነው ያለውን ልናከብርለት እና እውቅና ልንሰጠው ይገባል::በሚሻው መስመር የሄደበት የራሱ መልስ ያገኘበት የፖለቲካ እምነት እስካለው ድረስ ለሃገርም ይሁን ለሌላ ጉዳይ ይታገል እስካመነበት ድረስ መብቱ ነው::በአንድ አይነት አስተሳሰብ እንጓዝ የሚለውን ትተን በአንድነት እንታገል የሚለው ላይ ማተኮር ይገባል ልዩነት ውበት ነው::ከልዩነት ደሞ በሂደት በሃሳብ ፍጭት የዳበረ እውነት በፖለቲካ ውስጥ ይወለዳል::ልብ ልንለው የሚገባ ጉዳይ ግን ወያኔ የምንዋጋበትን ምክንያት እናውቀዋለን ካወቅነው ደግሞ የወያኔ ድርጊቶች ማንጸባረቅ አይጠበቅብንም::መብሰል ፖለቲካዊ ይሁን ድርጅታዊ ዲሲፕሊን እና መከባበር መደማመጥ ያስፈልጋል::የሆያሆዬ እና የጥላቻ ፖለቲካ በመጣ አጀንዳ ላይ የመርገብገብ ስሜተኝነት በዘል ልጓም የመጋለብ ጭፍንነት ወንዝ አያሻግርም ወያኔንም አያስወግድም::ምንም ጊዜ አቋም ሊኖረን ይገባል::የራሳችንን አቋም ለማሳካት በጋራ በአንድነት ከአምሳያዎቻችን ጋር እንዝመት እንጄ ስለሌሎች እያነሳን እየጣልን ጊዜ አንግደል:: #ምንሊክሳልሳዊ